TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GondarUniversity

ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ #በተለያየ_ጊዜ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ #አንጋፋ የሚባሉ ምሁራን ፤ መምህራንን ፣ ሰራተኞችን ፣ ተመራቂ ተማሪ እና የዩኒቨርሲቲው ታላቅ #ባለውለታ የሆኑ አባትን በሞት ተነጥቋል።

አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እነማንን #በሞት ተነጠቀ ?

🕯አባሆይ አሰፋ ዘለቀ🕯

የመሬት ርስታቸውን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማስፋፊያ ካበረከቱት 59 አርሷደሮች መካከል አንዱ ነበሩ። በ1963 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው የተማሪው ቁጥር መጨመር እና የሚሰጠውም የትምህርት ዓይነት እየሰፋ በመምጣቱ ግቢውን ወደ ማራኪ አካባቢ ማስፋፋት ሲፈልግ አባሆይ አሰፋ ዘለቀ ከሌሎች ልበቀናዎች ጋር በመሆን በማራኪ ከፍተኛ ቦታ አካባቢ የነበራቸውን የመሬት ይዞታ ለማስፋፊያ እንዲሆን በመፍቀድ ትውልድ እንዲቀረጽበት በማድረግ ዘመን ማይሸረው አበርክቶ አድርገዋል፡፡ በ94 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

🕯ፕሮፌሰር ሞገስ ጥሩነህ🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ መምህር ፣ ተመራማሪ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልጋይ ነበሩ።

🕯ዶ/ር ሰለሞን ይርዳው🕯

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንጋፋ ባልደረባ ነበሩ። ከ1988 ዓ/ም ጀምሮ በህክምናው ሙያ በመተማ ሆስፒታል አገልግለዋል። ከ1992/93 ዓ.ም ጀምሮ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሙያቸው አገልግለዋል። በማስተማርም ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። በጤና እክል ህይወታቸው አልፏል።

🕯መምህር ደመቀ ደሱ 🕯

አንጋፋ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህር ነበሩ። በጡረታ እስከተገለሉበት ድረስ ለ40 ዓመታት ገደማ  በማስተማር ሙያ እንዲሁም በትምህርት ክፍል እና በዲን ኃላፊነት አገልግለዋል።

🕯አቶ ፍስሃ ሞሴ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ተቋም Nutrition & Dietetics Department ውስጥ የChief laboratory Technical Assistant ባለሙያ ነበሩ። ቤተሰብ ለመጠየቅ በሄዱበት በደንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ተቀጥፏል።

🕯አቶ አታለል ምስጋናዉ🕯

በህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በፊዚዮሎጂ ት/ክፍል ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ መምህርና በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪ ነበሩ። በ31 ዓመታቸው በመኪና አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

🕯ተማሪ ኢዩኤል ታዬወርቅ🕯

የኪነህንፃ / #Architecture / ተመራቂ ተማሪ ነበር። የትንሳዔ በዓልን ከቤተሰቦቹ ጋር በአዲስ አበባ ለማክበር ባሄደበት ከፎቅ በወደቀ ብረት በመጎዳቱ በለጋ እድሜው ህይወቱ አልፏል፡፡ ከጥቂት ወራት በኋላ ከሚመረቁት ተማሪዎች መካከል ነበር።

🕯አቶ ሙሉአለም ይትባረክ🕯

በህክምናና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተማሪዎች አገልግሎት ውስጥ የተማሪዎች ምኝታ ቤት አስተባባሪ ነበሩ። በህመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከጥር ወር 2016 ዓ/ም አንስቶ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ አጠቃላይ 8 አንጋፋ ምሁራን ፣ መምህራን ፣ ሰራተኞች ፣ ተማሪ እንዲሁም የተቋሙን ባለውለታ ታላቅ አባት በሞት ተነጥቋል።

የጤና እክል ፣ ድንገተኛ አደጋ ፣ የመኪና አደጋ የህልፈተ ህይወት መንስኤዎቹ እንደሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዩኒቨርሲቲው ካገኘው መረጃ ተረድቷል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia