TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የእኛን ምሩቃን ለመቅጠር ስትፈልጉ የትምህርት ማስረጃቸውን #ለማረጋገጥ ጠይቁን ፤ ትክክለኛውን ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ እንሰጣችኃለን " - ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፤ በተለያዩ ጊዜያት በተደረገው የትምህርት ማስረጃ ማጣራት በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ስም የተሠሩ #የሀሰት የትምህርት ማስረጃዎች መገኘታቸውን አሳወቀ።

ተቋሙ ፤ ህገወጥ የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ለማጣራት በተሰራው ስራ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ትክክለኛ ያልሆነውን ውጤት በራሳቸው ጊዜ የራሳቸው አድርገው ውጤት ማሻሸል እንደቻሉ ተደርሶባቸዋል ብሏል።

" ይህ አሳፋሪ ወንጀል ነው " ያለው ዩኒቨርሲቲው ግለሰቦቹ ይህን በመፈፀም በአቋራጭ መንገድ ስራ የመቀጠር እና የሌሎች ሰዎች የስራ እድል ጭምር በማጥፋት ድርጊት መሰማራታቸውን አመልክቷል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን ስም ለመጥፋት እንደሞከሩ ገልጿል።

በእንደዚህ ዓይነት የሀሰት የትምህርት ማስረጃ ላይ መሳተፍ ከዜጎች የማይጠበቅ ተግባር ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲውን ተማሪዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ከዚህ ባለፈ ማንኛውም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ እንዲሁም የግል ተቋማትና ድርጅቶች ከዛሬ ህዳር 01/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሁሉም የትምህርት ፕሮግራሞች የተመረቁ ምሩቃንን ለመቅጠር ሲፈልጉ የተቀጣሪዎችን መረጃ በፖስታ ቁጥር P.O.Box 667 እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ኢሜይል email address: [email protected] በመላክ ማረጋገጥ እንደሚችሉ ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የምሩቃንን ትክክለኛውን የትምህርት ማስረጃ በአንድ ቀን ውስጥ ሰጣለሁኝ ብሏል።

* ከላይ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በሀሰት የትምህርት ማስረጃ ማጣራት የተደረሰባቸው የቀድሞ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ስም የተያያዘ ሲሆን አብዛኞቹ በተለያዩ የሀገሪቱ #ባንኮች ውስጥ እንዲሁም በመንግሥት መ/ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የተገኙ ናቸው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ባንኮች

የአገሪቱ ባንኮች ከአሠራር ጋር በተያያዙ ክፍተቶች በተለያዩ ሥልቶች ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ፣ ይህ ሁኔታም በቀጣይ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የበለጠ እንደሚጨምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትን በመገምገም አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

➡️ የአገሪቱ ባንኮች በበይነ መረብ ማጭበርበርያ ሥልቶች፣ ከባንኮች የውስጥ ሠራተኞችና ከሦስተኛ ወገን በሚደርሱባቸው የምዝበራ ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ እየተጋለጡ ናቸው።

➡️ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ማለትም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በሐሰተኛ ሰነዶችና በሌሎች የማጭበርበር ድርጊቶች ባንኮች 1 ቢሊዮን ብር አጥተዋል። የተመዘበሩት የገንዘብ መጠንም ከቀዳሚው ዓመት በእጥፍ ጨምሯል።

➡️ የባንክ ማጭበርበሮች በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ወደ 1 ቢሊዮን ብር ሲደርሱ፣ ከአምናው በእጥፍ አድጓል። እነዚህ ጉዳዮች የተከሰቱት በዋናነት ፦
° ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችንና ቼኮችን በመጠቀም ገንዘብ በማጭበርበር፣
° ያልተፈቀደ የባንክ ዋስትና በማቅረብ፣
° የተሰረቁ የኤቲኤም ካርዶችን በመጠቀም ገንዘብ በማውጣት ድርጊት
° በሐሰተኛ የስልክ ጥሪዎችና አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን በመጠቀም ነው። በተጠቀሱት የማጭበርበሪያ ሥልቶችም 20 ባንኮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሰኔ ወር 2015 መጨረሻ ላይ 3 ባንኮች 200 ሚሊዮን ብር ተዘርፈዋል።

➡️ ባንኮች አዳዲስ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ሲተዋወቁ በአሠራር ክፍተቶች ሳቢያ በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ እየተጋለጡ ናቸው።

➡️ ባንኮች ከአሠራር ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከልና የመጭበርበር ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ፣ ውጤታማ የቁጥጥር ሥልቶችንና አሠራርችን በመተግበር ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ #ሪፖርተርጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia