TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Hawassa

" ተማሪው ላይ ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሟል " በሚል #የተጠረጠረው ርእሰ መምህር በቁጥጥር ስር እንዳሚገኝ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በሀዋሳ ከተማ ታቦር አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወስጥ አንዲት ተማሪ ርእሰ መምህሯን " ጾታዊ ትንኮሳ ፈጽሞብኛል " በሚል ክስ መመስረቷን ተከትሎ ፖሊስ ተጠርጣሪዉን ግለሰብ ከስራ ገበታዉ ድረስ በመሄድ በቀን 20/05/2016 ዓ/ም በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለማወቅ ተችሏል።

የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ሀላፊዋ ወይዘሮ ፍሬህይወት ወልደጻዲቅ ጉዳዩን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጽያ የሀዋሳው አባል ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ፤ " የተጠቂዋ ቤተሰቦች ጉዳዩን ይዘዉ ቅድሚያ ለማመልከት የመጡት ወደእኛ ቢሮ ነበር " ያሉ ሲሆን ጉዳዩን ወደ ህግ እንዲወስዱት በማድረግ ማንኛዉንም የህግ ከለላና አስፈላጊ ድጋፎችን ሊሰጡ እንደሚችሉ ቃል ገብተው አንዳበረታቷቸው ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ ክሱ ተመስርቶ ተጠርጣሪዉ በህግ ጥላ እንደዋለና ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የገለፁት ኃላፊዋ " አሁን ላይ የሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ መረጃዎችን አጠናክሮ የክስ ሂደቱን ከኛ ጋር ለመደገፍ እንቅስቃሴ ላይ ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዉ በትምህርት ቤት ውስጥ ሲያዝ የነበረዉን ሁኔታ እና ድርጊቱን በተመለከተ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የሚያውቀዉ ነገር እንዳለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የትምህርት ቤቱ ምክትል ርእሰ መምህር አቶ ሀንዳሞ ፈይሳ ፤ በወቅቱ ተጠርጣሪው ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብለዉ መሄዳቸውን ፤ አሁን ላይ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ሳምንት እንዳለፋቸው ገልጸዋል።

ክስ አቅራቢዋ ተማሪ ከትምህርት ገበታዋ ደጋግማ በመቅረቷ ምክንያት " ወላጅ አምጭ አታምጭ " በሚል ከሚመለከታቸዉ መምህራኖቿ እና ከተጠርጣሪው ርእሰ መምህር ጋር ስትጨቃጨቅ እንደነበር የሚያስታዉሱት አቶ ሀንዳሞ ፤ ይህ ጉዳይ ለእርሳቸውም ሆነ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ #አስደንጋጭ እና ግራ ያጋባ መሆኑን አስረድተዋል።

ፖሊስ አስፈላጊዉን ማጣራት አድርጎ እዉነቱ ላይ እስኪደርስ እየጠበቁ መሆኑንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የሐዋሳዉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia