TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

" ... የተኩስ ልውውጡ የነበረው ከሚሊኒየም አዳራች በሰንሻይን በኩል ወደ ቦሌ መድኃኒዓለም በሚያስወጣው መንገድ ነበር " - የአካባቢው ነዋሪዎች

ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቦሌ በፖሊስ እና ፋኖ አባላት መካከል የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚሊኒየም አዳራሽ ጎን በሰንሸይን ቪላ ቤቶች አድርጎ ወደ ቦሌ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ወደ ሚያስወጣው መንገድ ላይ እንደነበር በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት ገልጸዋል።

በተኩስ ልውውጡ ሁለት የፋኖ አባላት እና አንድ መንገደኛ ህይወታቸው ጠፍቷል። ሁለት የፖሊስ አባላት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ አማርኛ በሰጡት ቃል ፥ " ናሁሰናይ አንዳርጌ የሚባለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴ ወቅት እጅ ላለመስጠት ከፍተኛ የሆነ ትግል ነው ያደረገው " ብለዋል።

" ከዚያም አልፎ በዚያ አካባቢ የሚሄድ አንድ ግለሰብ ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል። ሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ ከፍቶ ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃላቸው ፥ ቦሌ በነበረው የፋኖ አባላቱና እና የፖሊስ ተኩስ ልውውጥ ፦
- ናሁሰናይ አንዳርጌ ቆስሎ ወደ ህክምና ከተላከ በኋላ #ሞቷል
- አቤኔዘር ጋሻው በተኩስ ልውውጡ መሃል ተገድሏል፤
- ሀብታሙ አንዳርጌ የተባለ የፋኖ አባል ሳይቆስል በቁጥጥር ስር ውሏል።

ከዚህ ባለፈ ፦
° አቶ እንዳሻው ጌትነት የተባሉ ባለመኪና ‘#አልተባበርም’ ስላሉ መኪና ውስጥ በጥይት መትተውት ገድለውታል።
° የአንድ ግለሰብ ተሽከርካሪ መስታወት በጥይት መተውታል " ሲሉ ተናግረዋል።

በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከፖሊስ በኩል ሳጅን አራርሳ ተሾመ እና ኮንስታብል ማቲያስ ጴጥሮስ ቆስለው ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ታግታ ከተወሰደች በኃላ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታጋዲዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ታግታ ከተወሰደች 20 ቀናት ሆኗታል። ቤተሰቦቿ " ልጃችንን አፋልጉን " ሲሉ በፈጣሪ ስም ተማጽነዋል። መላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና የፀጥታ ኃይል ልጃቸውን እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቅርበዋል። የታዳጊ ተማሪ ማህሌት ቤተሰቦች ከትግራይ ዓድዋ ከተማ ያስተላለፉት የአፋልጉን የተማፅኖ ጥሪ ምን ይላል ?…
 #Update

"...ታጋችዋን ታዳጊ ለማስለቀቅ ከከተማ እስከ ክልል የተቀናጀ የክትትልና ምርመራ ስራ እየሰራን ነው። በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎችም አሉ " - የዓድዋ ከተማ ፓሊስ

የዓድዋ ከተማ ፓሊስ በታጋቿ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ ለመጀመሪያ ጊዜ ማብራሪያ ሰጥቷል።

መጋቢት 10/2016 ዓ.ም በዓድዋ ከተማ ልዩ ቦታ ዓዲ ማሕለኻ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ የተሰወረችው ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ከታገተች 24 ቀናት ተቆጥሯል።

የዓድዋ ከተማ ፓሊስ ዋና አዛዥ ተስፋይ  ኣማረ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም በስልክ በሰጡት መረጃ ፥ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግታ ለማስለቀቂያ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባትን የተማሪ ማህሌት ተኽላይ አጋቾችን በቁጥጥር ስር ለመዋል ፓሊስ ጥረት እንያደረገ እንደሆነ ተናግረዋል።

የታዳጊዋ መታገት በማስመልከት በተሰቦችዋ መጋቢት 10/2016 ዓ.ም ሪፓርት ካደረጉበት ቀንና ሰዓት ጀምሮ ፓሊስ ጉዳዩ ለደቂቃ ያህል ችላ እንዳላለው የገለፁት የፓሊስ ዋና አዛዡ ፥ " ' ፓሊስ ለእገታው ትኩረት አልሰጠውም ' ተብሎ በማህበራዊ የትስስር ገፆችና በሚድያዎች የሚሰራጨው መረጃ ልክ አይደለም " ብለዋል።

" ይህን ያህል ከባድ የውንብድና ወንጀል ተፈፅሞ ፓሊስ እንዴት ችላ ይለዋል ? " ሲሉ የጠየቁት ዋና አዛዡ ተስፋይ አማረ ፥ ከከተማው እስከ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን በመቀናጀት ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ለመያዝ ሌት ተቀን እየተሰራ ነው ብለዋል።

" ታዳጊዋን ያገቱ ሰዎች ከእገታው በፊት ለረጅም ጊዜ ሲከታተሉዋት የቆዩ መሆናቸው ከቤተሰቦችዋ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል " ያሉት ዋና አዛዡ ፥ " የተወሰኑት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውለናል። ለሚድያ መግለጫ ስላልሰጠን ብቻ ስራችን እየሰራን እንዳልሆነ ተደርጎ መውሰድ አግባብነት የለውም " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በታዳጊዋ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ ጉዳይ በተደጋጋሚ መረጃ ያደረሰ ሲሆን ከቀናት በፊት ቤተሰቦቿ በሰጡት ቃል ፥ አጋቾች ለማስለቀቅያ 3 ሚሊዮን ብር እንዲከፈላቸው በጠየቁበት ዕለት ድምጿን ከሰሙ በኃላ ዳግም እንዳላገኟት እነሱም እንዳልደወሉ ፣በምን ሁኔታ ላይ እንዳለች እንኳን እንደማያውቁ ፤ በዚህም መላው ቤተሰብ በከፍተኛ ጭንቅና ሃዘን ውስጥ እንደሚገኝ ተናግረው ነበር።

#TikvahEthiopiaMekelleFamily

@tikvahethiopia
" በህገ-መንግስቱ መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር ወደ ቤታችን መልሱን " - የራያ አለማጣ ተፈናቃዮች

ከትግራይ ደቡባዊ ዞን ወረዳ ራያ አላማጣና አለማጣ ከተማ ተፈናቅለው በመኾኒ ከተማ የመጠለያ ጣብያ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።

ዛሬ ቅዳሜ ሚያዝያ 5 /2016 ዓ.ም በተካሄደውና ከመኾኒ ከተማ እስከ ኩኩፍቶ ፣  በሪ ተኽላይ የተባለ ቦታ በሸፈነው የተፈናቃዮቹ ሰላማዊ ሰልፍ ፦
- የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ይተግበር!!
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ይከበር !!
- ወደ ቄያችን መልሱን !!

... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች መሰማታቸውን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ቦታው ድረስ በመደወል ለማረጋገጥ ችሏል።
                           
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
“ ወደ ትግራይ መልሱን የሚሉ ተፈናቃዮች የሉም ” - የአላመጣና አካባቢው አመራር 

ከራያ አላላማጣ ከተማ ተፈናቅለው መሆኒ ከተማ በሚገኝ መጠለያ የሚኖሩ ተፈናቃዮች፣ ወደ ትግራይ እንዲመለሱ ዛሬ (ሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ/ም) ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።

የአላማጣ ከተማና የአካባቢው አመራር የዛሬውን ሰልፍ በተመለከተ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፣ “ በስም የአላማጣ ተፈናቃይ ከማይጨውና መሆኒ አከባቢ ያሉ የ #TDF አባላትን ሲቪል በማስለበስ ‘ተፈናቃዮች ነን’ ብለው ከመሆኒ ወደ አላማጣ አቅጣጫ ጉዞ በማድረግ ተክላይ በር ድረስ ሰልፍ ወጥተዋል ” ብሏል።

አክለውም፣ “ ሲቪሉ ከተክላይ በር አላለፈም። የታጠቀው ኃይል ግን ከተክላይ በር ወደ ምዕራብ አቅጣጫ ከሚገኘው ጨጓራ ተራራ በመያዝ ቁልቁል ወደ ኮስምና ታኦ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ” ሲሉ ተናግረዋል። 

“ ይህ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የፕሪቶርያውን ስምምነት የሚጥስ ነው። መከላከያ በሰጠን አቅጣጫ የራያ አላማጣና የአላማጣ ከተማ ህዝብ ወደ ግንባር ከመሄድ ተቆጥቧል ” ብለዋል።

“ ሰልፈኞቹ ከያዙት መፎክር መካከል፦
- የትግራይ ሉዓላዊ ግዛት ይከበር
- የራያ ህዝብ ትግራይ እንጂ አማራ ሁኖ አያውቅም 
- የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ የለውም ” የሚል ይገኝበታል ሲሉ ገልጸዋል።

ከአላማጣ ከተማ ተፈናቅለው መሆኒ መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ተፈናቃዮች አሉ ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አመራሩ፣ “ ከራያ አላማጣ ተፈናቅለው የነበሩ በሙሉ ተመልሰዋል። መሆኒ ያሉ ተፈናቃዮች አመራር የነበሩ፣ ወጣት ያሳፈኑ፣ እስከ ሽዋሮቢት ድረስ የዘረፉ #ወንጀለኞች ናቸው ” ብለዋል። 

“ ወደ ትግራይ መልሱን የሚሉ የሉም። መሆኒ ውስጥ ያሉ የትግራይ ኢንቨስተሮች የአከባቢው ማህበረሰብ አላሰራ ስላላቸው ወደ መቐለ የሚሸሹ አሉ። ከዚህ ውጭ ሌላ የለም። 100% የተረጋገጠ ነው ” ሲሉ አክለዋል።

በትግራይ በኩል ያሉ ታጣቂዎች ባለፈው በነበረው ባደረጉት ተጨማሪ ትንኮሳ ተቆጣጥረውት ከነበረው "ጨጓራ" ከተሰኘው ቦታ፣ "ኮስም፣ ቡበ፣ ታኦ እና አከባቢው ተቆጣጥረዋል። መከላከያ ኃይል ለመጨመር ከላይ ካሉት አካላት እየተጻጻፈ ነው። በዚህ ሰዓት በርካታ አከባቢዎች ጦርነት ውስጥ ናቸው " ያሉት አመራሩ፣ " እኛ ፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሄድ እንፈልጋለን። ጦርነትን አማራጭ አናደርግም " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
ገንዘባችንን ከየትኛውም ባንክ ወደ M-PESA ፤ ከM-PESA ወደ የትኛውም ባንክ በመላክ ቀላል እና የተቀላጠፈ ክፍያ እንፈጽም!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ!

🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናውርድ፡ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ  በቴሌግራም   ቻናላችን https://t.iss.one/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA #FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በማቆያ ጣቢያ የሚገኙ ዜጎቿን ከነገ ጀምሮ በተቀናጀ መንገድ የመመለስ ሥራ እንደምትጀምር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የመንግሥት ልዑክ በሳዑዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ እና የጂዳ ቆንስላ ጀነራል ሰራተኞች እና የኮሙኒቲ አስተባባሪዎች ጋር በመወያየት በተመላሾች መለየት እና መመለስ ላይ…
#Update

“ ከሳዑዲ ተመላሾች በመደበኛው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተካተዋል ” - ሴቶች እና ማኀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ዜጎቿ እየመለሰች እንደምትገኝ የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጿል።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር መካላከልና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍና ክትትል ሂደት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጀ ተግይበሉ በሰጡት ቃል ፣ " በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ስራ እየተሰራ ነው " ብለዋል።

ዛሬ እና ትላንት ብቻ 1913 ሰዎች ተመልሰዋል።

ምን ያህል ወገኖችን ለመመለስ ታስቧል ? ሲል ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ያቀረበላቸው አቶ ደረጃ “ በአጠቃላይ ለመመለስ የታቀደው ወደ 70 ሺሕ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንን ነው። በሚቀጥሉት 3 እና 4 ወራት ውስጥ በስምንት 3 ወይም 4 ቀናት በሚደረግ በረራ የማስመለስ ዕቅድ ተይዟል ” ሲሉ መልሰዋል።

70 ሺሕ ወገኖችን ከመመለስ ባሻገር ኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት ለማቋቋም ምን ታቅዷል ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ ፥ “ በተለይ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ትኩረት ሰጥቶ የሳዑዲ ተመላሾች በመደበኛው የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተካተዋል ” ብለዋል።
 
በዚህ ወቅት በመደበኛው ሆነ በኢመደበኛው የሄዱ በአጠቃላይ በሳዑዲ አረቢያ ምን ያህል ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ ? ለሚለው ጥያቄ፣ “ አብዛኛዎቹ መደበኛ ባልሆነ ስርዓት ስለሆነ የሚሄዱት ይህን ይህል ናቸው ተብለው በመንግሥት አይታወቅም ” ብለዋል።

በሳዑዲ በጣም በርካታ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንዳሉ፣ ነገር ግን ሁሉም መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት የሄዱ ናቸው ተብሎ ስለማይጠበቅ ከሳዑዲ መንግሥት ጋር በተደረገ ድርድር እየተመለሱ ያሉት በኢመደበኛ ፍልሰት የሄዱትንና በአስቸጋሪ ሁኔታ ሚገኙትን እንደሆነ አስረድተዋል።

በኢመደበኛ መንገድ የሚሄዱ ዜጎች፦
- የሞት አደጋ፣
- ሴቶች ለፆታዊ ጥቃት፣
- በደላላ ገንዘባቸውን የመበዝዘብ ችግር እንደሚደርስባቸው የገለጹት አቶ ደረጀ፣ “ መደበኛውን የፍልሰት ስርዓት ተከትለው የሚሄዱባቸውን ሁኔታዎች ከመንግሥት አካላት መረጃ ወስደው እንዲጠቀሙ አደራ እንላለን
” ሲሉ አስገንዝበዋል።

#ThikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#ስልክአምባ

" 12 ሰዎች ናቸው የተገደሉት፤ .. ቤቶች ተቃጥለዋል፤ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል " - ነዋሪዎች

" 11 ሰዎች ስለመገደላቸው መረጃ ደርሶናል መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራን ነው " - ኢሰመኮ

️በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ስልክ አምባ ከተማ ባለፈው ሠኞ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ በ5 ቀበሌዎች ጥቃት መፈጸሙን ይህን ያደረጉት ደግመ የሸኔ ታጣቂዎች (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) እንደሆኑ ገልጸዋል።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች መኾናቸውን ተናግረዋል።

ወደ 60 ቤት እህል ጭምር የያዘ መቃጠሉን እና በርካቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገልጸዋል። ከ100 በላይ ከብቶችም እየተነዱ ተወስደዋል።

አንድ ነዋሪ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኃላ ዘግይተው የደረሱት የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከታጣቂዎቹ ጋር ተኩስ ገጥመው እንደነበር አስረድተዋል።

ሌላ ነዋሪ ፤ " ኦነግ ሸኔ ነው የሚባለው ቁጥራቸው የበዛና ከባድ መሳሪያ ጭምር የታጠቁ ናቸው በተኛንበት 12 ሰዓት ላይ መጥተው ነው ጉዳት ያደረሱት " ብለዋል።

" እኛ ገበሬዎች ነን ምንም ኃይል የለን አቅም የለን በጣም ነው ጉዳት የደረሰብን " ያሉ ሲሆን ሴቶችን፣ አዛውንቶችን ከብቶችን በማሸሽ ወደጫካ ማስመለጥ እንደተቻለ አቅም የሌላቸው አዛውንቶች ግን መገደላቸውን እነሱንም ሲቀብሩ እንዳመሹ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፥ በአካባቢው በታጣቂዎች ግጭት ተነስቶ 11 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ከአካባቢው መረጃ እንደደረሰው ገልጾ መረጃውን ለማጣራት ጥረት ላይ መሆኑን አመልክቷል።

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል በነዋሪዎች የቀረበበትን ክስ አስተባብሎ፤ " እኛ እንዲህ ዓይነት ድርጊት ውስጥ እጃችን የለበትም " ብሏል። " ጉዳዩ በገለልተኛ አካል ምርመራ ሊደረግበት ይገባል " ሲልም ገልጿል።

ክልሉ እስካሁን በይፋ የሰጠው መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa ➡️ " እህታችንን የጠለፋት ግለሰብ ወደ ፓሊስ እንዳንሄድ በእህታችን ህይወት እያስፈራራን ነው " - የተጠላፊዋ ውድነሽ ማቲዎስ ቤተሰቦች በእንባ የታጀበ መልእከት ➡️ " ቆየት ብዬ ዝርዝር መረጃ ሰጣችኃለሁ " - ፖሊስ ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ ነው። ስሟ ውድነሽ ማቲዮስ ይባላል። በቀን 28/07/2016 ቅዳሜ ምሽት ከቤት " ሰው ይጠራሻል " ተብላ እንደወጣች አልተመለሰችም። ቤተሰቦቿ…
#Update

➡️ " እንደተባለዉ ጠለፋ አለመፈጸሙን በማወቃችንና ቤተሰቦቿ  ተስማምተዉ ጉዳዩ ከህግ እጅ እንዲወጣ ስለፈለጉ ክትትላችንን አቋርጠናል " - የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ

➡️ " ጉዳዩ በሽምግልና መያዙን እንፈልገዋለን ቢሆንም ህግ አይግባ የሚለዉን የልጄ ቃል ከራሷ የመጣ ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ " - አባት አቶ ማቲዎስ

ከሰሞኑ ነዋሪነቷ በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክ ከተማ የሆነ ወድነሽ ማቲዮስ የተባለች ግለሰብ በድንገት ከቤት ተጠርታ እንደወጣች መቅረቷንና ቆይቶም መጠለፏ መታወቁን ተከትሎ ቤተሰቦች " ፖሊስ አስፈላጊውን ክትትል አድርጎ ልጃችን ይመልስልን " ማለታቸዉን ቲኪቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ  ይታወሳል።

ይሁንና ጉዳዩን እየተከታተለ የነበረው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ " ጉዳዩ ጠለፋ ሳይሆን በገዛ ፍላጎቷ ያደረገችዉ መሆኑን ደርሸበታለሁ " በማለት ክትትሉን ማቆሙን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ለቲኪቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

" ቤተሰቦቿ እንደሚሉት ጠለፋ ሳይሆን በፍላጎት የተደረገ መሆኑንና አሁን ላይ ጉዳዩ በሽምግልና እነደተያዘ " የገለጸዉ የከተማዉ ፖሊስ የሽምግልና ሂደቱ ከልጅቱ በተጨማሪ የቤተሰብ ይሁንታ ማግኘቱንም ገልጿል።

የልጅቱ አባት የሆኑት አቶ ማቲዎስ በበኩላቸዉ ሁኔታዉ በሽምግልና መያዙ ቢያስደስታቸዉም  ልጃቸዉን በስልክ እንጅ በአካል አለማግኘታቸዉ አሁንም ልባቸዉ ዉስጥ ጥርጣሬ እንደፈጠረ ተናግረዋል።

" ህግ አይግባ የሚለዉን የልጄ ቃል ከራሷ የመጣ ስለመሆኑ እጠራጠራለሁ "ብለዋል።

በመሆኑም በሲዳማ ባህል መሰረት ሚያዚያ 17 የሚደረገው ሽምግልና የተደበቀዉን ሚስጥር እንደሚፈታዉና መፍትሄዉንም ያቀርባል ብለዉ እንደሚያስቡ ገልጸዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia