TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መንገዱ ተከፍቷል!

#ቦርደዴ ላይ ተዘግቶ የነበረው #መንገድ ከትላንት ለሊት ጀምሮ #ተከፍቷል። ለመንገዱ መዘጋት ምክንያት የሆነው በአካባቢው የተፈጠረው የፀጥታ መደፍረስ እንደሆነ አይዘነጋም፤ በዚህም የ7 ዜጎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መንገድ

" የመንገዱ ስራ በመጓተቱ ችግር ላይ ወድቀናል " - ነዋሪዎች

የጎሬ - ማሻ - ቴፒ አስፓልት መንገድ ስራ በመጓተቱ ችግር ላይ ወድቀናል ሲሉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ገልጹ።

የአካባቢዉ ነዋሪዎች ከሸካ ዞን አስተዳዳሪና ከፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ኢንጅነር ደጀኔ ፈቃዱ ጋር ባደረጉት ወይይት " ስለምን ይቀለድብናል ? " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ መንገዱ ከተጀመረ ወዲህ በክረምት መንቀሳቀስ እንደተቸገሩና አምቡላንሶች እንኳን ስራ ማቆማቸዉን በመግለጽ የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቀዋል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በበኩላቸዉ ችግሩ የተከሰተዉ ከአራት አመት በፊት ከፌደራል መንገዶች ባለስልጣን ጋር ተፈራርሞ ወደስራ የገባዉ " ሀይወንዳይ ዲቨሎፕመንት " የተባለ የቻይና ድርጅት በዉሉ መሰረት መስራት ባለመቻሉ መሆኑን በመግለጽ የፌደራል ባለስልጣናት ክትትል እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የማህበረሰቡን ቅሬታ የሰሙት የፌዴራል መንገዶች ባለስልጣን ምትክል ዳይሬክተር ኢንጅነር ደጀኔ ፈቃዱ በሰጡት ምላሽ  ችግሩ መኖሩን ቢያዉቁም ማህበረሰቡ ባነሳዉ ልክ ይሆናል ብለዉ እንዳልገመቱ በመግለፅ በልዩ ክትትል መንገዱን እንደሚጨርሱና ያለዉን ችግር ለመቅረፍም የመንገድ እድሳቶችን እንደሚያከናዉኑ ገልጸዋል።

የጎሬ ማሻ ቴፒ አስፓልት መንገድ ከ138 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተመድቦለት ከአራት አመት በፊት ቢጀመርም ያልቃል በተባለበት በዚህ ወቅት ግን 40 በመቶ ላይ ቆሟል።

ከሰሞኑን የመንገዱ ስራ ያለበት ደረጃ በሚመለከታቸው አካላት ተጎብኝቷል።

መረጃውን ያደረሰን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#መንገድ

ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ ሌላ አማራጭ ነው የተባለው የአሳይታ- አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራው ተጠናቆ ለትራንስፖርት ክፍት ሆነ።

ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኘው የጋላፊ መስመር በተጨማሪ ለወደፊቱ ሌላ አማራጭ ሆኖ የሚያገለግለው የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳውቋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ፤ የቀልም ቅብ ስራዎች እና ሌሎች ጥቃቅን ስራዎች ተገባደዋል ተብሏል።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በትራንስፖርት  እጦት ምክንያት በእግር እና በግመል ከመጓዝ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።

መንገዱ በዋናነት ኢትዮጵያን በአሳይታ በኩል ከጅቡቲ ጋር በቅርበት ያስተሳስራል። የኢትዮጵያን የገቢ እና ወጪ ንግድ በማቀላጠፍ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም አሳይታ ከተማን ከአፋምቦ ወረዳ ብሎም በርካታ ቀበሌዎችን በማገናኘት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን ይበልጥ ያጠናክራል ተብሏል።

ይህ አካባቢ የአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ የሚገኝበት በመሆኑ በርካታ ምርቶች የሚመረትበት መስመር ነው። ከእነዚህ ምርቶች መካከል ፦
* ከፍተኛ የጨው ምርት፣
* ጥጥ፣
* ቴምር፣
* ሰሊጥ፣
* ቲማቲም፣
* ሽንኩርት፣
* ብርቱካን፣ ሃባብ እና በርካታ ፍራፍሬዎች ይጠቀሳሉ።

የመንገዱ መገንባት እነዚህን ምርቶች በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ብሎም ወደ ጀቡቲ ለማድረስ ይበልጥ ያግዛል ተብሎለታል።

ከዚህ ባሻገር በመስመሩ የትምህርት ፣ ጤና እና መሰል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶችን በአፋጣኝ አንዲስፋፉ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተጨማሪም ይህ መስመር አሁን ላይ ያለውን ሚሌ - ዲቼ ኦቶ-ጋላፊ-ጅቡቲ ወደብ ያለውን መንገድ በ30 ኪሎ ሜትር ያሳጥረዋል።

ወደፊት በአካባቢው ሊመረቱ የሚችሉ የፋብሪካ ውጤቶችን (ስኳር ፣ የስንዴ ዱቄት) ወደ ውጪ ገበያ ለማቅረብ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

አጭር መረጃ ስለ መንገድ ፕሮጀክቱ ፦

- የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበው 1,600,901,379 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።

- የመንገዱ ርዝማኔ 50.34 ኪሎ ሜትር ነው። የጎን ስፋቱ ትከሻን ጨምሮ በገጠራማ ሥፍራዎች 10 ሜትር ፣ በወረዳ ከተሞች 19 ሜትር እና በዞን 21.5 ሜትር ስፋት አለዉ።

- ፕሮጀክቱ የ3 ድልድዮች ግንባታንም ባካተተ መልኩ ነው የተካሄደው።

- ግንባታውን ያካሄደው ሀገር በቀሉ የስራ ተቋራጭ አሰር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው። የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ይዲዲያ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንትስ አከናውኗል።

Via ERA

@tikvahethiopia
#መንገድ

“ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት 4 ጊዜ ያንን አስፓልት ያሰራል ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መሰል ሜጋ ፕሮጀክቶች የግንባታ ግብዓቶች ፣ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ፣  ዘይት እና ሌሎች ኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ግብዓቶችን የምታከናውንበት የጂቡቲ መንገድ ጥገና ካሻው ከ10 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም ባለመጠገኑ በተሽከርካሪዎች ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማህበሩ ምን አለ ?

- “ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ውስጥ እያለች ጂቡቲ ድረስ መጥታ መንገዱን አይታ የተፈራረመችው ሰነድ ነበር ከ4 ዓመታት በፊት። ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም። ከውሃ ልማት ዲኬል እስከሚባል ቦታ ድረስ ያለው መንገድ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ፣ የአገሪቱ ንብረት የሚወድምበት ነው። ”

- “ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት አራት ጊዜ ያንን አስፓልት ይሰራል። መንገሥት ያን መንገድ እንዲጠገን ማድረግ አለበት። ”

- “ ስምምነቱ ያለው በኢትዮጵያም ሆነ በጂቡቲ መንግሥት በኩል መንገዱ መጠገን እንዳለበት ነው፣ የተሰራው 20 ኪ.ሜ ብቻ ነው። በቀሪው 80 ኪ.ሜ ብዙ ኤክስፖርት የያዙ ተሽከርካሪዎች ይወድቃሉ። ለኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክት ማሽን የጫኑ ተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ ሆኖባቸው አንዳንዴ ማሽኑ የሚወድቅበት ሂደት አለ። ”

- “ የመንገዱን መፈራረስ ተከትሎ በከፍተኛ Currency የሚገቡ Spare parts በቶሎ ይበላሻሉ ይህም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አለው። የዚህ ችግር ዋነኛ ምክያት ደግሞ የመንገዱ አለመጠገን ነው። ”

-  “ የ80 ኪ/ሜ መንገድ #ከ10_ሰዓታት_በላይ ጉዞ ይወስዳል። ከዓመት ወደ ዓመት ችግሩ እየተባባሰ ነው የመጣው። መንገዱ የተቆፋፈረ፣ አቧራማ፣ አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ ከተጠቀሱት ችግሮች በተጨማሪ ለጤናም ጠንቅ ነው። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑትን ዶክተር ቶሎሳን አነጋግሯል። እሳቸውም ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

ዶ/ር ቶሎሳ ፦

° “ ግንባታው የዘገየገው ከዚህ በፊት በጂቡቲ በኩል በነበረ አለመግባባት ነበር፡ በኋላ ላይ ግን መግባባት ላይ ተደርሶ ጥገናው ተጀምሯል። ”

° “ የጩኸቱ መንስኤ ስላላቀ ነው እንጂ አሁን መግባባት ላይ ተደርሶ መንገዱ እየተሰራ ነው ለ2 ኮንትራክተሮች ተሰጥቶ (በእኛ እስከተወሰነ ድረስ በእነርሱ እስከተወሰነ ድረስ ያለው) ። ”

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ እውነትም አሁን በመሰራት ላይ ያለ አለ ? ብሎ ጠይቋል።

° “ Exactly አሁን በመሰራት ላይ ነው ያለው። ከጋላፊ እስከ ዲኬሌ ድረስ (ወደ ጂቡቲ ማለት ነው) ለቻይና ኮንትራክተር ተሰጥቶ እርሱ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። በሳዑዲ መንግሥት ነው የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገው። ከዲኬሌ እስከ ጂቡቲ ድረስ ደግሞ በእኛ (በኢትዮጵያ) በኩል አንድ የእኛ አገር ኮንትራክተር ይዟል። ”

° “ ትንሽ ችግሩ ያለበት እርሱ ላይ ነው። ለችግሩ መንስኤው የፋይናንስ አጥረት ነው። በአጠቃላይ የግንባታውን ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል። ”

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia