TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መንገድ

“ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት 4 ጊዜ ያንን አስፓልት ያሰራል ” - የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና መሰል ሜጋ ፕሮጀክቶች የግንባታ ግብዓቶች ፣ ማዳበሪያ፣ ነዳጅ፣  ዘይት እና ሌሎች ኢትዮጵያ ገቢ እና ወጪ ግብዓቶችን የምታከናውንበት የጂቡቲ መንገድ ጥገና ካሻው ከ10 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም ባለመጠገኑ በተሽከርካሪዎች ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ማህበሩ ምን አለ ?

- “ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ውስጥ እያለች ጂቡቲ ድረስ መጥታ መንገዱን አይታ የተፈራረመችው ሰነድ ነበር ከ4 ዓመታት በፊት። ምን ላይ እንደደረሰ አላውቅም። ከውሃ ልማት ዲኬል እስከሚባል ቦታ ድረስ ያለው መንገድ እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ፣ የአገሪቱ ንብረት የሚወድምበት ነው። ”

- “ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ መንገዱ ከፈረሰበት እስካሁን ጊዜ ድረስ እዛ የጠፋው የአገር ንብረት አራት ጊዜ ያንን አስፓልት ይሰራል። መንገሥት ያን መንገድ እንዲጠገን ማድረግ አለበት። ”

- “ ስምምነቱ ያለው በኢትዮጵያም ሆነ በጂቡቲ መንግሥት በኩል መንገዱ መጠገን እንዳለበት ነው፣ የተሰራው 20 ኪ.ሜ ብቻ ነው። በቀሪው 80 ኪ.ሜ ብዙ ኤክስፖርት የያዙ ተሽከርካሪዎች ይወድቃሉ። ለኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክት ማሽን የጫኑ ተሽከርካሪዎች አስቸጋሪ ሆኖባቸው አንዳንዴ ማሽኑ የሚወድቅበት ሂደት አለ። ”

- “ የመንገዱን መፈራረስ ተከትሎ በከፍተኛ Currency የሚገቡ Spare parts በቶሎ ይበላሻሉ ይህም የአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አለው። የዚህ ችግር ዋነኛ ምክያት ደግሞ የመንገዱ አለመጠገን ነው። ”

-  “ የ80 ኪ/ሜ መንገድ #ከ10_ሰዓታት_በላይ ጉዞ ይወስዳል። ከዓመት ወደ ዓመት ችግሩ እየተባባሰ ነው የመጣው። መንገዱ የተቆፋፈረ፣ አቧራማ፣ አካባቢው ሞቃታማ በመሆኑ ከተጠቀሱት ችግሮች በተጨማሪ ለጤናም ጠንቅ ነው። ”

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቅሬታው ምላሽ እንዲሰጡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑትን ዶክተር ቶሎሳን አነጋግሯል። እሳቸውም ምላሽ ሰጥተዋል።

ምን አሉ ?

ዶ/ር ቶሎሳ ፦

° “ ግንባታው የዘገየገው ከዚህ በፊት በጂቡቲ በኩል በነበረ አለመግባባት ነበር፡ በኋላ ላይ ግን መግባባት ላይ ተደርሶ ጥገናው ተጀምሯል። ”

° “ የጩኸቱ መንስኤ ስላላቀ ነው እንጂ አሁን መግባባት ላይ ተደርሶ መንገዱ እየተሰራ ነው ለ2 ኮንትራክተሮች ተሰጥቶ (በእኛ እስከተወሰነ ድረስ በእነርሱ እስከተወሰነ ድረስ ያለው) ። ”

Q. ቲክቫህ ኢትዮጵያ እውነትም አሁን በመሰራት ላይ ያለ አለ ? ብሎ ጠይቋል።

° “ Exactly አሁን በመሰራት ላይ ነው ያለው። ከጋላፊ እስከ ዲኬሌ ድረስ (ወደ ጂቡቲ ማለት ነው) ለቻይና ኮንትራክተር ተሰጥቶ እርሱ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው። በሳዑዲ መንግሥት ነው የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገው። ከዲኬሌ እስከ ጂቡቲ ድረስ ደግሞ በእኛ (በኢትዮጵያ) በኩል አንድ የእኛ አገር ኮንትራክተር ይዟል። ”

° “ ትንሽ ችግሩ ያለበት እርሱ ላይ ነው። ለችግሩ መንስኤው የፋይናንስ አጥረት ነው። በአጠቃላይ የግንባታውን ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል። ”

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#እንዳትደናገጡ

ነገ የሚከበረውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ከንጋቱ 12:00 ሰዓት ላይ 9 ጊዜ መድፍ እንደሚተኮስ የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዘማሪው ወደ መንፈሳዊው ህይወት ሳይገባ በፊት ለረጅም ዓመታት ዘፋኝ የነበረ ሲሆን በሙዚቃ አድማጮች ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ስራዎች ነበሩት።

ሙሉቀን መለሰ የዘፈንን ህይወት እርግፍ አድርጎ ከተወ እና ዘማሪ ከሆነ በኃላ የተለያዩ የመዝሙር ስራዎችን ለወንጌል አማኞች አቅርቧል።

ዘማሪው ከሀገር ወጥቶ አሜሪካ መኖር ከጀመረ ረጅም ዓመታት ያለፈው ሲሆን በዛው ባለበት ሀገር አሜሪካ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።

ከዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ስራዎች አንዱ ፦

ኢትዮጵያ !

" ኢትዮጵያ #ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ።

አድገዋል አውቀዋል ያልሻቸው #ልጆችሽ
ሁሉም እሾህ ሆነው እየወጉ #አደሙሽ
የአንድነት ማሰሪያው መቀነት ይኑርሽ ይኑርሽ፤
እግዚአብሔር ነይ ይላል ወደእሱ ተመለሽ።

#ጦርነት #ረሃብ #ስደት ደርሶብሻል፤
ችግር በየፈርጁ ተፈራርቆብሻል፤
በመከራሽ ብዛት የአፍረት ማቅ ለብሰሻል፤
የሚታደግ አዳኝ ኃያል ብሩት አጥተሻል።

ኢትዮጵያ ፈጥነሽ እጆችሽን ወደ እግዚአብሔር ዘርጊ፤
በመከራሽ ዘመን የሚረዳሽ አምላክሽ ነውና ወደእርሱ ተጠጊ። "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !

በዓሉ #የሰላም#የአንድነት#የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

መልካም በዓል !

#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopia
አቶ በቴ ኡርጌሳ ተገደሉ።

የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ (ኦነግ) ከፍተኛ አመራር / የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንትና ለሊት በመቂ ከተማ መገደላቸው ከቅርብ ወዳጆቻቸው ተሰምቷል።

" ካረፉበት ሆቴል ውስጥ ትላንት ለሊት ተወስደው ተገድለው ነው አስክሬናቸው መንገድ ላይ የተገኘው " ተብሏል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ሲዳረጉ የቆዩ ሲሆን በቅርቡም " ሁከት እና ብጥብጥ በማስነሳት " ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ታስረው በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር ተለቀው ነበር።

ትላንትና በመቂ ከተማ ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

ፓርቲያቸው እስካሁን ስለግድያው በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዒድ_አልፈጥር ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ ! በዓሉ #የሰላም፣ #የአንድነት፣ #የፍቅርና #የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል ! #TikvahFamily❤️ @tikvahethiopia
#ዒድ_አልፈጥር

1445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን ጥዋት ላይ የዒድ ሶላት ስነስርዓት ተከናውኗል።

በየከተሞቹ ባሉ የዒድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎች ህዝበ ሙስሊሙ በጋራ በመሰባሰብ የዒድ ሶላት ስነስርዓት አከናውኗል።

ከዒድ ሶላት በኃላ ምዕመኑን በየቤቱ ፣ ከዘመድ አዝማዱ፣ ከወዳጆቹ ጋር በመሆን የ1445ኛውን ዒድ አልፈጥር በዓል እያከበረ ነው።

በየከተሞቹ የነበረውን የዒድ ሶላት ስነስርዓት በፎቶ ይመልከቱ @tikvahethmagazine

በድጋሜ መልካም በዓል !

ፎቶ፦ ፎቶግራፈር አቤል ጋሻው (አዲስ አበባ)

@tikvahethiopia