#ኢትዮጵያ
በነዳጅ የሚሠሩ እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ውጪ ተገጣጥመው ወደ ሃገር ውስጥ በሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ ተደረገ።
የጉምሩክ ኮሚሽን በነዳጅ የሚሠሩ እና ሙሉ በሙሉ ውጭ ተገጣጥመው ወደ ሃገር የሚገቡ አውቶሞቢሎች ላይ የውጪ ምንዛሬ እቀባ መጣሉን አሳውቋል።
ዕቀባው ያስፈላገበት ዋና ምክንያት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ እና በሃይብሪድ /በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ/ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ ለማበረታት ነው ተብሏል።
አሰራሩ ፥ የአረንጓዴ ልማትን ተግባራዊ ለማድረግ እና ለነዳጅ እና በነዳጅ ለሚሰሩ አውቶሞቢሎች ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጪ ምንዛሬ ለመቀነስ ይረዳል ሲል ኮሚሽኑ አመልክቷል።
ይህ እቀባ #ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚችል ተገልጿል።
በነዳጅ የሚሠሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያስገቡ አስመጪዎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ #ማሳሰቢያ ተላልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከገቢዎች ሚኒስቴር ነው ያገኘው።
@tikvahethiopia