TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ያሬድ ዘሪሁን‼️

ፖሊስ በያሬድ ዘሪሁን ላይ ያቀረበውን የክስ ማመልከቻ ለፍርድ ቤት አሰምቷል።

ፖሊሲ እንዳለው አቶ ያሬድ ዘሪሁን አሁን በቁጥጥር ስር ካልዋለው የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት የቀድሞ ኃላፊ #ጌታቸው_አሰፋ ጋር #በመመሳጠርነ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በመቀበል በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል፡፡

ዜጎችን አፍነው በመውሰድና በማሰር ብልታቸው ላይ ውሃ በማንጠልጠል ራቁታቸውን ቆሻሻ ውስጥ በመጣል ጉንዳን እንዲበሉ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ፡፡

መርማሪ ፖሊስ እንዳለው በተፈፀመባቸው ድብደባ ብዛትም የሞቱ ዜጎችም አሉ፡፡ ግለሰቦች ወደ ኤርትራ ሄደው ህገ ወጥ መሳሪያ እንዲያስገቡ በማቀነባበር ህዝብ እንዲሸበርና ተጠርጣሪዎች ላይ እንዲሳበብ ማድረግ
በሚል ወንጀል እንደጠረጠራቸውም ፖሊስ አስታውቋል። ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ 14 ቀን እንዲሰጠው ፍርድቤቱን ጠይቋል ፡፡

ተጠርጣሪው አቶ ያሬድ በበኩላቸው ከህግ አማካሪያቸው ጋር መገናኘት እንደሚፈልጉ በመግለፅ ለሚቀጥለው ማክሰኞ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲሉ ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

በተጨማሪም ከማንም ጋር እንዳልገናኝ እየተደረኩ ነው፤ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው የታሰርኩት ሲሉም ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ አቅርበዋል።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪው ከማንም ጋር እንዳልገናኝ እየተደረኩ ነው፤ አንድ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ነው የታሰርኩት ሲሉ ያቀረቡትን ያስተባበለ ሲሆን፥ ተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲፈቀድለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የግራ ቀኙን የተመለከተው ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪው ከህግ ባለሙያ ጋር እንዲገናኙና የተጠየቀው የ14 ቀን ቀጠሮ ላይ ብይን ለመስጠት ለፊታችን ማክሰኞ 8 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia