TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መከላከያ ሰራዊት🔝

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር #ከዛሬ ጀምሮ እንደሚሠማራም ተገልጧል፡፡

በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችን በተመለከተ የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጎንደር ላይ የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ መግለጫውን የሰጡት የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል #አለምነው_አየነ እና የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር #ዘላለም_ልጃለም ናቸው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር ከዛሬ የካቲት10/2011 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሠማራም በመግለጫው ይፋ ተደርጓል፡፡

በፀጥታ ኃይሉ አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ የተከለከለከሉ ተግባራትም በመግለጫው ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከጎንደር-መተማ መስመር ከመንገድ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፤ በሁመራ መስመርም በተመሳሳይ #ክልከላ ተደርጓል፡፡ በጎንደር ከተማ ከፀጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ሰው መሣሪያ ታጥቆ መንቀሳቀስ እንደማይችልም ታውቋል፡፡

ማንኛውም በፀጥታ መደፍረስ ተሳትፎ ያደረገ ኃይል እርምጃ እንደሚወሰድበትና ‹‹ሰላም ለማስከበር›› በሚል ሰበብ ማንኛውም ግለሰብ ከኮሚሽኑ ፈቃድ ውጭ መሣሪያ ይዞ #እንዳይንቀሳቀስ እገዳ ተላልፏል፡፡

በመግለጫው የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የጎንደር ወጣቶችና አክቲቪስቶች በጎንደር እና በአካባቢው ሰላም እንዲሰፍን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር እንዲሠሩ ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሊቀመንበርነታቸው ወረዱ‼️

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሺር ከገዥው #ናሽናል_ኮንግረስ_ፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው መውረዳቸው ተገልጿል። በምትካቸውም የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አህመድ ሞሃመድ ሃሩን ፓርቲው አጠቃላይ ጉባኤ እስከሚያካሂድ የአልበሺርን ቦታ መረከባቸው ነው የተነገረው። ሀሩን በዚህ ሳምንት የሱዳን ገዥ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

በሱዳን ከታህሳስ ወር 2018 ጀምሮ እስከዛሬ ያልተቋረጠው የዜጎች ተቃውሞ አልበሺር ከፓርቲ ሃላፊነታቸው እንዲለቁ ማስገደዱን ተንታኞች እየገለጹ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ቀደምበተቃውሞ ፍራቻ ሳይሆን በምርጫ ብቻ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ መናገራቸው ይታወሳል። ሱዳን በ2020 ምርጭ እንደሚታካሂድ ይጠበቃል።

አልበሺር ባሳለፍነው ሳምንት ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጡ ሲሆን እሰተዳደራዊ መዋቅሩን በመበተን አዳዲስ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ሹመት ሰጥተዋል። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ #ክልከላ ቢደረግም #ተቃውሞው እስከዛሬ ድረስ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ፦ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የግብረ ሰዶማውያኑ ጉብኝት...

ከኢትዮጵያ ባህልና ልማድ #የተቃረነ ነው ተብሎ በህግ #ክልከላ የተጣለበት፣ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪያን ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት የሚያደርጉት ዝግጅት፣ የሚያወጡት መግለጫ የተቃውሞ መልስ እየተሰጠው ነው፡፡ ይህንንም የማይገባ ግብር የሚያደርገው ቡድን ወደ #ኢትዮጵያ መግባት እንደሌለበት እና ወደ ቅጣትም እንደሚገባ በዚሁ ጉዳይ ላይ ወደ ኋላ እንደማይል የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እወቁልኝ ብሏል።

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#እንድታውቁት #ሀዋሳ #ክልከላ

በሀዋሳ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ ባለ ሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና የሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር #ተከለከለ

ሰሞኑን በሀዋሳ ከመዝናኛ መልስ እየደረሰ ያለውን የመንገድ ላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ሲባል ከምሽቱ 3:00 በኃላ ባለሦሰት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) እና ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የተከለከለ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪው ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ፦
°  ምክንያት ?
°  ክልከላው ለምን አስፈለገ ?
° በማህበረሰቡ የእለት ተእለት ህይወትስ ላይ የሚያሳድረዉ ጫና አይኖርም ? ወይ ስንል ኢንስፔክተሩን ጠይቋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት ኢንስፔክተር ተስፋዬ ፤ " ሁሉንም ያደረግነው ለማህበረሰቡ ደህንነት ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ የትራፊክ አደጋ እየተስተዋለ ነው " ሲሉ ገልጸው ከአደጋዎቹ አብዛኛዉ በባለሦሰት እግር ባጃጅና በባለሁለት እግር ሞተር ሳይክል የሚደርስ እንደሆነ አስረድተዋል።

" በዚህ አመት ብቻ በምሽት በሞተር ሳይክል የደረሰዉ አደጋ የሚያስገርም ቁጥር ያለው ነው " ያሉት ኢስፓክተር ተስፋዬ በቁጥር ስንት ? የሚለውን ወደፊት ዳታውን አጠናቅረዉ ለማህበረሰቡ የማሳየት እቅድ እንዳለቸዉ ጠቁመዋል።

ከአደጋዎቹ ውስጥ በአብዛኛው የሚከሰቱት በምሽት መሆኑን ጠቅሰው ፤ " ጠጥቶ ሞተር ሳይክል ማሽከርከር  ትልቁ ምክኒያት ሆኖ ተገኝቷል። በተለይም በመንግስት ሞተር ሳይክሎች ሳይቀር ሶስትና ከዚያ በላይ ሆኖ መንቀሳቀስ አደጋ እየፈጠረ ነው ይህን ችግር ለመቀነስ ሲባል #ክልከላው ወጥቷል " ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፤ " የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ የወንጀል መፈጸሚያ እየሆኑ ነው " ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ " ለአብነት ኮንትራት ተብለዉ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው አደጋ እና የሌሎችም ወንጀሎች ምንጭ ሆነው ተገኝተዋል " ብለዋል።

" ጥንቃቄ ለራስ በመሆኑ ማህበረሰቡ ለራሱ ሲባል የወጣዉን ክልከላ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ " ሲሉ አሳስበዋል።

" እለት ተእለት የሚከሰተው ዘግናኝ የትራፊክ አደጋ እንዲቆም የሁላችንም ትብብር ያስፈልጋል " ብለዋል።

ክልከላው የሚያበቃበትን ጊዜን በተመለከተ ምንም የተባለ ነገር የለም።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia