TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፥ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ፕሮጀክት እና ተያያዥ የልማት ሥራዎች ምክንያት በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ መስመር የማዛወር ሥራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጿል። በዚህም ሥራው ሲከናወን ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ እንዲሁም አደጋ እንዳይከስት ሲባል ሥራው በሚከናወንባቸው አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ሙሉ…
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ከተማ ከ4 ኪሎ እስከ ፒያሳ ባለው መስመር የራስ መኮንን ድልድይ እየተሰራ በመሆኑ የመንገድ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ፍጹም መቆም የሚከለክሉ የትራፊክ ምልክቶች ተተክለዋል።

በስራ መግቢያ እና ከስራ መውጪያ ሰዓትም በአካባቢው ላይ በመንገድ መዘጋጋት ህብረተሰቡ እንዳይጉላላ አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ተብሏል።

በዚሁ መሰረት ፤ " ፍጹም መቆም የሚከለክሉ " ምልክት የተተከለባቸው ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ መታሰቢያ የሚወስድ ዋና መንገድ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣ አድዋ ሙዚዬም ዙሪያ እና ማዘጋጃ ዙሪያ ከዛሬ መጋቢት 19/2016 ጀምሮ ጥብቅ ቁጥጥር ይጀመራል ተብሏል።

በአካባቢው በግዜያዊነት ለተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚውል የአድዋ ሙዚዬም "ሰርፌስ ፓርኪንግ" አገልግሎት መስጠት ስለጀመረ አሽከርካሪዎች እንደ አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦

- ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
- ከአራት ኪሎ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ፣ አማራጭ መንገድ ከአራት ኪሎ-አባድር 
- ከደጎል አደባባይ ትራፊክ መብራት ወደ 4 ኪሎ
- ከቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከደጃች ውቤ ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከባሻወልዴ ችሎት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ
- ከቀበና ወደ ፒያሳ የሚመጡ አሽከርካሪዎች መንገዱ ግንባታ ላይ መሆኑን ተገንዘበው ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

በአካባቢው ያለውን የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ለመቅረፍ ፤ አማራጭ #ማስተንፈሻ የሚሆን መንገድ በተለምዶ ከቀይባሕር ኮንደሚንየም ወደ ደጎል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ዛሬ ከሰዓት ለተሽከርካሪዎች ክፍት ይሆናል ተብሏል።

መረጃው የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia