TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትዊተር

ለጥንቃቄ ...

የትዊተርን አዲስ አሰራር ተከትሎ የበርካታ ታዋቂ ሰዎች እና ተቋማት #የማረጋገጫ_ምልክት ከትላንት ጀምሮ ተነስቷል።

ታዋቂው ቱጃር ኤሎን መስክ በ44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን ከገዛው በኋላ በመተግሪያው ላይ የመጡ ለውጦች በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ እየሆኑ ይገኛል።

ከዚህም ውስጥ አንዱ ትዊተር ታዋቂ ግለሰቦች የሚሰጠውን የማረጋገጫ መልክት (Twitter verification) በክፍያ መጀመሩ ዋነኛው ነው።

ለግለሰብ በወር 8 ዶላር ለድርጅት ደግሞ 1000 ዶላር ማስከፈል የጀመረው መተግበሪያው ከትላንት ጀምሮ ክፍያ ያልፈጸሙ ያላቸውን አካውንቶች የማረጋገጫ ምልክታቸውን አንስቷል።

የማረጋገጫ ምልክታቸው የተነሳው በሀገራችን ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ታዋቂ ሰዎች ፣ የሚዲያ ተቋማት ፣ ትልልቅ የመንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤቶች ነው።

በርካቶች ይሄንን ውሳኔ  በተመሳሳይ ስም የሚከፈቱ " የማረጋገጫ ምልክት " የሚኖራቸው አካውንቶች እንዲኖሩ እድሉን ይከፍታል በሚል የተቃወሙት ቢሆንም ውሳኔው ግን ተግባራዊ ተደርጓል።

ይህም ሀሰተኛ መረጃን ያባብሳል ተብሎ ተሰግቷል።

በተለይ አሁን ላይ የማረጋገጫ ምልክቱን በቀላሉ ማግኘት መቻሉ ለአጭበርባሪዎች (Scammers) በር በመክፈት በርካቶችን ሊጎዳ ይችላል።

የገጾችን ትክክለኛነት ለማሳየት የምንጠቀምበት ይህ የማረጋገጫ ምልክት ከዚህ በኋላ ለማረጋገጫነት ብዙም ጥቅም የሚኖረው አይመስልም።

የገጹ ተከታይ ብዛት እንደ ማረጋገጫ መውሰድ ብንችልም እንደ ሀገራችን የሀሰተኛው ገጽ ተከታይ ቁጥር ከትክክለኛው በሚበልጥበት ሁኔታ የገጹን ትክክለኛነት ለማረጋገጥም አዳጋች ያደርገዋል።

ከዚሁ ከትዊተር ማረጋገጫ ምልክት መነሳት ጋር በተያያዘ ጦርነት ውስጥ ባለችው ሱዳን የሆነ አንድ ጉዳይን እናጋራችሁ።

በጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) የሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ (RSF) የትዊተር አካውንት ያለው ሲሆን አካውንቱም 82.7K ተከታይ እና የሰማያዊ ማረጋገጫ ምልክት ነበረው።

ትዊተር ትላንት ይህንን የማረጋገጫ ምልክት ባነሳበት ሰዓታት ውስጥ የሰማያዊ ምልክት #የገዛ በተመሳሳይ በRSF ስም የተከፈተ 26 ሺ ተከታዮች ያሉት ገፅ ጄነራል መሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄሜቲ) በጦርነቱ ላይ #እንደተሞቱ አድርጎ አንድ ፅሁፍ አስራጭቷል።

የዚህን የማረጋገጫ ምልክት ከትዊተር የገዛ ገፅ ያወጣውን ሀሰተኛ ፅሁፍ 1.7 ሚሊዮን ሰዎች አይተውታል ፤ ይህን ሀሰተኛ ፅሁፍ ያመኑም አልጠፉም።

ውድ ቤተሰቦቻችን በትዊተር አዲስ አሰራር ሁሉም ሰው ሰማያዊ የማረጋገጫ ምልክት እየገዛ በመሆኑ የሰማያዊ ምልክት ያላቸው አካላት ናቸው የሚያሰራጩት በማለት ሁሉንም የምታዩትን መረጃዎች አትመኑ፤ መረጃዎችን መርምሩ፣ አጣሩ። እናመሰግናለን !!

#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine