TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ➡ " ታጋቾቹ ተለቀው በሰላም #አዲስ_አበባ ገብተዋል " - የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ➡ " ለማስለቀቂያ መጀመሪያ ከከፈልነው 4 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በእያንዳንዱ መኪና (4 መኪናዎች) 500 ሺህ ብር ከፍለናል " - ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ➡ " አንድም ገንዘብ አልተቀበልንም " - ፋኖ ማርሸት ፀሀይ በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ታግተዋል የተባሉ የቀን ሰራተኞች ከእገታው ተለቀው በሰላም…
" 271 ዜጎችን ከእገታ አስለቅቄያለሁ " - ኮማንድ ፖስት
ላለፉት 25 ቀናት በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ውስጥ በታጣቂዎች እገታ ላይ እንደነበሩ የተነገረላቸው የቀን ሰራተኞች ከእገታ ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የጎጃም ኮማንድ ፖስት አንድ ኮር ፤ ታግተው የነበሩ 271 ዜጎችን ማስለቀቁን አሳውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ በአራት አውቶብስ ተጭነው ሲጓዙ የነበሩት 273 ዜጎች እንደሆኑ እና " በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ እና በኤሊያስ ከተማ መካከል ሲደርሱ ነው በጽንፈኛኞች ታግተዋል " ብሏል።
ታጣቂ ቡድኑ ከ3 ሰዓት በላይ ወደማይታወቅ ቦታ አስገድዶ ከወሰዳቸው በኋላ ሁለቱን #በመረሸን ለቀናት ደብቆ ሲያሰቃያቸው መቆየቱን ገልጿል።
በኃላም " ኮሩ ወደ አካባቢው በመሠማራት ከበባ በማድረግ ምቹ ሁኔታ ሲጠባበቅ መከበቡን የተረዳው ፅንፈኛ ለቋቸው ሊሸሽ ችላል " ሲል አመልክቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጋርዱላ ዞን ባገኘው መረጃ በእገታ ላይ የነበሩና ከዞኑ ተመልምለው ለደን ምንጣሮ ስራ ወደ ህዳሴው ግድብ ሲያቀኑ የነበሩ 246 ሰራተኞች ትላንት ምሽት ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ ገብተዋል።
ዞኑ ለሰራተኞቹ ከእገታ መለቀቅ ላለፉት ቀናት የፌዴራል መንግሥት ፣ የአማራ ክልል በየደረጃው ያሉ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ቀይ መስቀል ትብብር ማድረጋቸውን እና የባለሃብቶች ጥረት እንዳለበትም ጠቁሟል።
የኧሌ ዞንም ፤ " ለጉልበት ስራ ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሲሄዱ በአማራ ክልል በታጣቂዎች የታገቱ ዜጎች ተለቀዋል " ብሏል።
ዞኑ ፤ መንግሥት እና ባለሃብቱ አድርገዋል ባለው ጥረት ነው ታጋቾች ነፃ የወጡት።
በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል አማካኝነትም ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን ነው ያመለከተው።
ከዞኑ ተመልምለው የሄዱት 38 የቀን ሰራተኞች ናቸው።
ከላይ ያሉት የሰራተኞች ቁጥር ድምር 284 ሲሆን ቀጣሪው ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ይህን ቁጥር አይቀበለውም ታግተው የነበሩትም 272 ናቸው ነው የሚለው። ለዚህም በቂ የሰነድ ማስረጃ እንዳለው ይገልጻል።
ላለፉት ቀናት ወደ ስፍራው ከፍተኛ የድርጅቱን ኃላፊ በመላክ ሰራተኞቹ ደህንነታቸው ተጠብቆ ምንም ሳይሆኑ እንዲለቀቁ ጥረት ሲያደርግ የቆየው ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ታጣቂዎቹ በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር ወስደው ልጆቹን እንደለቀቋቸው ገልጿል።
መጀመሪያ 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ በሶስት ሰው ስም ከተከፈለ በኃላ ሰራተኞቹ ተለቀው በ4 መኪና ጉዞ ጀምረው ለዋናው አስፓልት ትንሽ ሲቀራቸው አማኑኤል አቅራቢያ ሌላ የቡድኑ ክንፍ ይዟቸው 6 ሚሊዮን ብር ሲጠይቅ እንደነበር ድርጅቱ ገልጿል።
በኃላ ግን ለእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በመክፈል በድምሩ አጠቃላይ በ6 ሚሊዮን ብር እንዲለቀቁ መደረጉን ተናግሯል።
እንደድርጅቱ መረጀ ከተለቀቁት 271 ሰዎች አንዱ ሾልኮ የጠፋ ሲሆን በኃላም በስልክ ከቤተሰቦቹ ጋር መነጋገሩ ተገልጿል።
@tikvahethiopia