TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba " ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢውም ክፍያ አልተከፈለንም " ያሉ በአዲስ አበባ የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራ ካቆሙ ቀናት አልፈዋል። እነዚህ አውቶብሶች በከተማይቱ ያለውን የትራንስፖርት ችግር እንዲያቀሉ ድጋፍ እንዲሰጡ ተመድበው ከአመት በላይ አገልግሎት የሰጡ ሲሆን ካለፈው ሚያዚያ 30 ጀምሮ ግን " ከሁለት እና ሶስት ወር በላይ ውል አልታደሰልንም፤ ተገቢ…
#አዲስ_አበባ

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድርስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አካላት #በነባሩ_ክፍያ_ታሪፍ በሙሉ አቅም ሊሰሩ ይገባል ተብሏል።

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሁሉም ተቋማት፣ የታክሲና ሀይገር ባለንብረቶች ማህበራትና ግለሰቦች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ይፋ እስኪደረግ ድረስ በነባሩ የክፍያ ታሪፍ መሰረት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።

ከነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን በተገቢው መንገድ የማይሰጡና ህብረተሰቡን ለተለያዩ እንግልቶችና አላስፈላጊ ወጪዎች የሚዳርጉ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ አካላት ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡና ወደ ስራ እንዲገቡ፤ በማይገቡትም ላይ ቢሮው አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ቢሮው ፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታና በህጋዊ መንገድ ለተቋሙ ሳያሳውቁ ከስራ ገበታቸው የወጡት የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶቡስ አገልግሎት ሰጪ ማህበራት በገቡት ውል መሰረት መብታቸውን እየጠየቁ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስቧል።

የሸገር ድጋፍ ሰጪ አውቶብሶች ስራቸውን ካቆሙ ቀናት የተቆጠረ ሲሆን ባለንብረቶች በሰጡት ቃል ስራ ያቆሙት ከሁለትና ሶስት ወር በላይ ውል ስላልታደሰለቸው እና ተገቢ ክፍያ እየተከፈላቸው ስላልሆነ መሆኑን መግለፃቸው ይታወሳል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/70126?single

@tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች !

እሁድ ግንቦት 28/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ " በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል " በሚል መሪ ቃል ለፖሊስ አመራር እና አባላት የምስጋና እና የእውቅና ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል።

ይህን ተከትሎ ስነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ፦

➤ ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር (ኦሎፒያ አደባባይ)

➤ ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ በላይና በታች

➤ ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ

➤ ከቸርችል ጎዳና በሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፖስታ ቤት

➤ ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

➤ ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር

➤ ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና አካባቢ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር

➤ ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሜክሲኮ አደባባይ

➤ ከሚክሲኮ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር መብራት

➤ ከሰንጋ ተራ በቴሌ ባር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች በድሉ ህንፃ አካባቢ

➤ ከንግድ ማተሚያ ቤት በውስጥ ለውስጥ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦርማ ጋራዥ አካባቢ

➤ ከሸራተን ወደ አምባሳደር ለሚመጡ ፍል ውሃ አካባቢ

➤ ከካዛንቺስ በኩል ወደ ፍል ውሃ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10፡30 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት መሰረት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርድ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመኪና ዝርፊያ ! ከጥቂት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ወገኖች ላይ የሚፈፀመው ዝርፊያ አሳሳቢ መሆኑን አመልክተን ነበር። በወቅቱ አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት መግለፁ አይዘነጋም። ትናንት አርብ ምሽት 4:00 ላይ ደግሞ ሌላ አንድ ወንድማችን ከፍየል ቤት ወደ ሀያሁለት…
#አዲስ_አበባ

አዲስ አበባ ውስጥ የቀጠለው ዝርፊያና ጥቃት !

ከሰሞኑን የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወገኖች ላይ እየደረሰ ስላለው ወንጀል መረጃ መለዋወጣችን አይዘነጋም።

ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ማመልከታችንም የሚታወስ ነው።

ለማስታወስ ፦

👉 አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራበትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት : t.iss.one/tikvahethiopia/71682?single

👉 ባለፈው አርብ ምሽት አንድ ወንድማችን ከፍየል ቤት ወደ 22 ከመገድ ላይ ሰው ጭኖ አውራሪስ አካባቢ ሲደርስ አንገቱን አንቀው እራሱን እንዲስት በማድረግ ከመኪናው አሰወጥተው በመወርወር መኪናውን ይዘው መሰወራቸውን አሳውቀን ነበር : t.iss.one/tikvahethiopia/72020?single

የአሁኑ ግን ከዝርፈያም ባለፈ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ነው።

ከላይ በፎቶ የምትመለከቱ ሳላዲን ሐሰን ይባላል።

የምትመለከቷት መኪናም የእሱ ነበረች።

ትናንት ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ተገድሎ መኪናው ተዘርፏል።

ሳላዲን የራሱን እና የቤተሰቦቹን ኑሮ ለማሻሻል ሲል ይተዳደርበት በነበረው የመኪና እጥበት ስራ ከሚያገኘው ገቢ በመቆጠብ ነው መኪናዋን ገዝቷት የነበረው።

ሳላዲን በጩቤ ተወግቶ ተገድሎ መኪናው ከመዘረፉ በፊት የመጨረሻ አገልግሎት ለመስጠት የተደወለበት አካባቢ ገርጂ 24 ልዩ ቦታ ኤርትራ ቆንጽላ ጽ/ቤት አካባቢ መሆኑን የሚሰራበት ድርጅት እንደነገራቸው ጓደኞቹ ገልፀዋል።

ቤተሰቦቹ ከባድ በሆነ መሪር ሀዘን ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ጓደኞቹም በተፈጠረው ሁኔታ እጅግ መደናገጣቸውንና ከባድ ሀዘን ውስጥ እንዳሉ ነግረውናል።

ለበለጠ መረጃ፦ 0944322244 (አብዲ ሰይድ) ፤ 0967803785 (ካሊድ አብዱልቃድር)

@tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል የተባለው ዝርፊያ !

በአዲስ አበባ ከተማ በከፍተኛ ወጪ በተሠሩ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ እየተፈፀመ ያለው ዝርፊያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን " በምሽት የሚኖረውን የህብረተሰቡን እና የትራፊክ እንቅስቃሴ ደህንነትና ምቾት ለማስጠበቅ አይነተኛ ሚና ያላቸው የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል " ብሏል።

ባለስልጣኑ ፤ መንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች ጎን ለጎን የመንገድ ዳር መብራት ተከላና ጥገና ስራዎችን በስፋት እያከናወነ መሆኑን ገልጾ ነገር ግን በከፍተኛ ወጪ በተሠሩ የመንገድ ዳር መብራቶች ላይ በተደጋጋሚ እየደረሰ በሚገኘው የስርቆት ወንጀል የተነሳ በተለያዩ አካባቢዎች የመንገድ መብራት የአገልግሎት መቆራረጥ እያጋጠመ ይገኛል ብሏል።

የመንገድ ዳር መብራት አገልግሎት መቆራረጥ በምሽት ክፍለ ጊዜ የሚኖረውን የትራፊክ ፍሰት ከማስተጓጎሉ በተጨማሪ ለወንጀል ድርጊቶች እና ለአደጋዎች መጨመር አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል ሲል ገልጿል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝም የገለፀው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ይህንን ህገ-ወጥ ተግባር ለማስቆም ዋነኛው የመንገድ ባለቤት ሕብረተሰቡ በመሆኑ የመንገድ ዳር መብራቶችን ከጉዳት እንዲከላከልና እንዲጠብቅ መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Peace ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምን አሉ ? የፕሪቶሪያ ስምምነትና የዛሬው ናይሮቢ ስምምነት ተፈፃሚ እንዲሆን ለማድረግ በሙሉ ቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል። ጀነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ? የዛሬው ስምምነት በትግራይ ውስጥ በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ያስወግዳል የሚል ተስፋ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። ኡሁሩ ኬንያታ ምን አሉ ? ኡሁሩ ኬንያታ በዛሬው መግለጫ ስምምነቱ በጦር…
#Update

በደቡብ አፍሪካ ፤ ፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግስትን ወልክለው ፊርማቸውን ያኖሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዛሬው የናይሮቢው ስምምነት በኃላ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አምባሳደር ሬድዋን ፤ ከዛሬው የቀጠለ ውይይት (በወታደራዊ ኃላፊዎች መካከል) የዛሬ ወር ገደማ (mid-December) በትግራይ ክልል መዲና #መቐለ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ዋናውና የውይይቶቹ ፍፃሜ ደግሞ በፈረንጆቹ አዲስ አመት #አዲስ_አበባ ላይ ሊደረግ እንደሚችል ገልፀዋል።

የናይሮቢው ውይይት በተጀመረበት ዕለት ኡሁሩ ኬንያታ ፤ " በፕሪቶሪያ ጀመርን፣ መንገዳችን እየተጠጋ ፤ አሁን ናይሮቢ ነን ፣ በሚቀጥለው ጊዜ ስብሰባችን መቐለ እንደሚሆን ተስፋ አድርጋለሁ ፤ በመጨረሻም አዲስ አበባ ላይ አብረን እናከብራለን። ይህ ጸሎታችን ፣ ተስፋ የምናደርገው እና የምንፈልገው ነው። " ማለታቸው አይዘነጋም።

በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ፤ የናይሮቢው ውይይት የተደረገው በፕሪቶርያ የተደረገውን ስምምነትን መሰረት አድርጎ መሆኑን ገልፀዋል።

ነገር ግን በዚህ ውይይት የውጭ ኃይሎች ጉዳይ " sticking point " እንደነበር እና ውይይቱ በዛ ሁኔታ የተካሄደ እንደነበር አስረድተዋል።

(አምባሳደር ሬድዋን እና አቶ ጌታቸው ቃላቸውን የሰጡት በዛው ኬንያ፣ ናይሮቢ ለሚገኘው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ነው )

@tikvahethiopia
" ሸገር ከተማ ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው "

በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ስድስት (6) ከተሞች የተዋቀረው ሸገር ከተማን የማደራጀት ሥራ መጀመሩን የከተማው ኃላፊዎች እንደገለፁ ሪፖረተር ጋዜጣ አስነብቧል።

የከተማው ምክትል ከንቲባ እንደሆኑ የተነገረላቸው አቶ ጉግሳ ደጀኔ ፤ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ 6 ከተሞች በአንድ ከተማ አስተዳደርና በአንድ ከንቲባ እንዲመሩ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

ከተሞቹ ፦
• ሰበታ፣
• ቡራዩ፣
• ለገጣፎ ለገዳዲ፣
• ሱሉልታ፣
• ገላንና መናገሻ በሥሩ የሚገኙ ከተሞች እንደሆኑ ተገልጿል።

አቶ ጉግሳ ደጀኔ ለጋዜጣው በሰጡት ቃል ፦

- አዲሱ የሸገር ከተማ በ12 ክፍላተ ከተሞች፣ በ36 ወረዳዎች፣ 40 የገጠር ቀበሌዎች የተደራጀ (የተዋቀረ) ነው።

- የከተሞች ዕድገት ወደኋላ የቀረ በመሆኑና በከተሞች መስፋፋት ሳቢያ አርሶ አደሮች ከመኖሪያ ቀዬአቸው በመፈናቀላቸው ነው ከተማው የተመሰረተው።

- ስድስቱ ከተሞች በጋራ የሚያከናውኑት ሥራ ተፎካካሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ሲሆን ዋና ጽሕፈት ቤታቸው #አዲስ_አበባ፤ ሳሪስ አካባቢ ነው።

- ዋና ጽሕፈት ቤቱን ለመምረጥ (አ/አ) የራሱ የሆነ መነሻ ተቀምጦለታል ፤ ይህም ለሁሉም ከተሞች አማካይ መሆን የሚያስችል ቦታ ታሳቢ በማድረግ ነው።

- ሸገር ከተማ ተጠሪነቱ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ነው። እንደማንኛውም መንግሥታዊ አስተዳደር ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈጻሚና የዳኝነቱ ሥርዓትን የሚመሩ አካላት ይኖሩታል።

- ለአዲሱ የሸገር ከተማ በቅርቡ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) ከንቲባ ሆነው ተሹመዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Reporter-12-19

Credit : ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle #EthioTelecom

" በአጭር ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው ? ስንት ነው ? " - የመቐለ ነዋሪ

" ... በሌሎች ከተሞች ይደርሳል፣ ይመጣል ሳይባል መጥቶ እንዳስደሰትናችሁ ይህንኑ እናደርጋለን " - ፍሬህይወት ታምሩ (የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ)

ዛሬ ወደ #መቐለ ሄደው የነበሩ የፌዴራሉ መንግስት ልዑካን ከክልሉ አመራሮች እና ከመቐለ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በውይይቱ ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ የቴሌኮም አገልግሎት በአጠረ ጊዜ ለማስጀመር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህም ወቅት ፤ የመድረኩ አንድ ተሳታፊ እንዲህ ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል ፦

" የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት መዘርጋት ነው ወሳኙ መብራት ኃይል ቀድሞ ስለተዘረጋ ብዙ ነገሮችን የፈታ ይመስለኛል።

የቴሌ በአጭር ጊዜ መፍትሄ ያገኛል የሚል ነገር ሰምተናል ፤ በአጭር ጊዜ ማለት ምን ማለት ነው ? ስንት ነው ?

አጭር ጊዜ የሚለው ወሳኝ ነው ፤ የትግራይ ህዝብ ለሁለት ለሶስት አመታት በተለያዩ ችግሮች ሲጠቃ የቆየ ለብዙ ችግሮች የተዳረገ ነው ፤ ስለዚህ የታመቀ ህመምና ጉዳት አለው ከዚህ ጉዳት ለመውጣት አሁን የደረስንበት ነገር ዛሬ መሆን የሚችል ከሆነ ለምን ነገ እናደርገዋለን ?

ዛሬ መደረግ ያለበትን ነገር የምናደርግ ከሆነ አጭር ጊዜ ማለት ስንት ነው ? የሚለውን መግባባት አለብን።

እናውቃለን መሰራት ያለባቸው ነገሮች አሉ ፤ አሁንም መልስ ማግኘት ይፈልጋል የትግራይ ህዝብ አጭር ጊዜ ማለት ስንት ነው ? "

ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ፦

" ... በመቐለ ላይ ያሉ ልጆቻችን ከዚህ ስብሰባ በኃላ ልናገኛቸው ነው (ይሄን ያሉት ቀን ላይ ከነዋሪዎች ጋር በነበረው ስብሰባ ነው) እነሱ በሰጡን መረጃ እየዋለን፤ ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንዳልደረሰበት ገልፀውልናል (በመቐለ ያለው መሰረተ ልማት) ፤ ነገር ግን ወደ #አዲስ_አበባ መገናኘት ስላለበት ፋይበሮች መጠገን አለባቸው።

የሆነው ሆኖ ግን ያ የቤት ስራ የእናተ ሳይሆን የኛ ሆኖ በአጠረ ጊዜ ውስጥ ያልነው የትኛውንም አጋጣሚና አማራጮችን ተጠቅመን አገልግሎት እናስጀምራለን።

በዛ በኩል ያለውን ጥገና ስናከናውን ስለቆየን ይሄ የሚፈጥን ይመስለኛል። አንድም ሁለትም ቀንም ሊሆን ይችላል ፤ ከመቐለ ወደ አብዓላ መንገድ ያለው ወደ 50 ኪ/ሜ 1.4 ነው ትላንት ባለኝ መረጃ የቀረን ከመቐለ ያለው ቡድናችን እየሰራ ስላለ በአጠረ ጊዜ ብዬ የተናገርኩበት ምክንያት ዛሬ ያልቃል ብለን በጣም በጉጉት የሚጠበቅ አገልግሎት እንደመሆኑና ለረጅም ጊዜ ግንኙነት ሳያዳርግ የቆየ ማህበረሰብ ከመጓጓቱ የተነሳ ዛሬ ይደርሳል ብለን ባይደርስ ከፍተኛ disappointment ይፈጠራል ያ እንዲሆን አንፈልግም።

ስለዚህ በሌሎች ከተሞች ይደርሳል፣ ይመጣል ሳይባል መጥቶ እንዳስደሰትናችሁ ይህንኑ እናደርጋለን ብለን እየሰራን ነው። "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ምስጋና በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ በኩል በየዓመቱ የመማሪያ መፅሀፍት ሲሰባሰብ 5 ዓመታትን ደፍኗል። (በኮቪድ ወረርሽኝ እና ጦርነት ምክንያት የተቋረጡትን አይጨምርም) ባለፈው ክረምት ላይ በጀመረው 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሀፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (በአዲስ አበባ) መፅሀፍት ተሰብስበው ለት/ቤቶች ተሰጥቷል። የዚሁ ቀጣይ የሆነ ሁለተኛ ዙር የማሰባሰብ ስራ ከቅዳሜ አንስቶ እየተካሄደ ነው። ስራው ከመፅሀፍ…
#የቀጠለ

ዛሬ እሁድ፦

- ካሌብ ጌትነት 10 መደበኛ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ወ/ሮ ሀሊማ ሙዘሚል ሀሰን እና አቶ አብድላዚዝ አህመድ ከልጃቸው ነሂማ አብድላዚዝ መሀመድ ጋር 31 መደበኛ መፅሀፍ ፣ 2 የግል ት/ቤት መፅሀፍ አበርክተዋል።

- መቅደስ ደረጀ መደበኛ 55 መፅሀፍ አበርክታለች።

- ናታን ደመቀ 8 አዲስ አጋዥ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬ ከልጆቻቸው ፀጋ ተመስገን፣ ሜሎና ተመስገን፣ ናርዶስ ተመስገን ጋር በመላው ቤተሰባቸው ስም 7060 ብር ወጪ አድርገው 45 መፅሀፍ ገዝተው አስረክበዋል።

- ወ/ሮ ህይወት እንድርያስ ከልጃቸው ቤዛዊት ነጋሽ ጋር 10 አጋዥ ፣ 3 መደበኛ መፅሀፍ አስረክበዋል።

- ሀዊ ጨምዴሳ 20 አጋዥ መፅሀፍት፣ 34 መደበኛ መፅሀፍት አስረክባለች።

- ወ/ሮ ፀጋ ለማ፣ ከልጆቻቸው በእምነት ወንደሰን፣ ያሬድ ወንደሰን እና እድላዊት ወንደሰን 25 መደበኛ እና 5 አጋዥ መፀሀፍት አበርክተዋል።

- አሚር መኑር 48 አጋዥ ፣ 14 መደበኛ መፅሀፍ አበርክቷል።

- አንድ የቤተሰባችን አባል ከለቡ 28 መደበኛ መፅሀፍት ፣ 29 አጋዥ መፅሀፍት፣ 4 ልብወለድ መፅሀፍት አበርክቷል።

- ኤግዞም የፋርማሲ እቃዎች አከፋፋይ 3000 ብር ወጪ የሆነባቸው መፅሀፍት አስረክቧል።

- አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የቤተሰባችን አባል የ2000 ብር መፅሀፍ ገዝቶ አስረክቧል።

ሁላችሁንም ቤተሰቦቻችንን እናመሰግናለን።

በዚሁ አጋጣሚ ጃፋር መፅሀፍት ቤትን እያደረገ ላለው ቀና ትብብር ምስጋና ለማቅረብ እንወዳለን።

የትላንት ቅዳሜ እና የዛሬ እሁድ #ድምር ብቻ ፦

👉 1,089 መፅሀፍት
👉 2 ላፕቶፕ
👉 2 ሞኒተር
👉 1 ፕሪንተር

#አዲስ_አበባ

#ይቀጥላል
#አዲስ_አበባ #የሚዘጉ_መንገዶች

የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዕለቱ በ #ምኒሊክ_አደባባይ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የአከባበር ስነ ስርዓቱ እንደሚጀምር ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ከዚያ በመቀጠል ወደ አድዋ ድልድይ የእግር ጉዞ እንደሚደረግና ዋናው ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑም ፦

👉 በምኒሊክ አደባባይ በሚከናወነው የአከባበር ስነ ስርዓት ምክንያት ፦

• ከሰሜን ሆቴል ትራፊክ መብራት ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከዮሀንስ መብራት ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከጊዮርጊስ ቴሌ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከሀገር ፍቅር መታጠፊያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከብሪቲሽ ካውንስል ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከሲኒማ አምፒር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከእሪ በከንቱ ( እሪ በስራ) ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአራዳ ህንፃ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከሰባራ ባቡር ቶታል ወደ ጊዮርጊስ ቴሌ መስቀለኛ
• ከዳትሰን ሰፈር መገንጠያ ወደ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡

👉 ከምኒሊክ አደባባይ ወደ አደዋ ድልድይ የእግር ጉዞ በማድረግ በአድዋ ድልድይ የሚከናወነው ስነ ስርኣት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

• ከእንግሊዝ ኤምባሲ ትራፊክ መብራት ወደ አድዋ ድልድይ
• ከፈረስ ቤት ኮንደሚኒየም መታጠፊያ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከምስራቅ መገንጠያ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከሴፍቲ መብራት ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከ22 አደባባይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከቺቺኒያ ወደ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከካዛንቺስ ቶታል ወደ አቧሬ
• ከድሮው ሰንደይ ማርኬት ወደ ሴቶች አደባባይ
• ከሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከአቧሬ ጀርመን አደባባይ ወደ ሴቶች አደባባይ ያሉት መንገዶችን ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ #ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

👉 በመስቀል አደባባይ የሚከናወነው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፦

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከፒኮክ ትራፊክ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ባምቢስ
• ከጥላሁን አደባባይ( መሿለኪያ) ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር
• አልሳምጨለለቅ ህንፃ ወደ ለገሀር
• ከገነት መብራት ወደ ለገሀር
• ከጠማማ ፎቅ (ገነት ሆቴል) ወደ ሜክሲኮ
• ከሱዳን ኤምባሲ (ጠማማ ፎቅ) ወደ ሜክሲኮ
• ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ወደ ሜክሲኮ
• ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ
• ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም ወደ ለገሐር
• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቲያትር
• ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት መብራት
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን መብራት
• ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኢምግሬሽን መብራት(ፖስታ ቤት)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ
• ከሚያዚያ 27 አደባባይ (4 ኪሎ) ወደ ፓርላማ መብራት
• ከጥይት ቤት ወደ ግቢ ገብርኤል
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ አሽከርካሪዎች #ሌሎች_አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።

ከነገ እሮብ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሸከርካሪን #አቁሞ_መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#AAU

አንጋፋው የ " #አዲስ_አበባ_ዩኒቨርሲቲ " በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ሆነ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የራስ ገዝ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ተወያይቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው  ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ እንዲሆን ወስኗል።

ውሳኔው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ነጻነት እንዲረጋገጥ፣ ከፖለቲካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆነው የመማር ማስተማር እና የምርምር ሥራዎችን በላቀ መልኩ መፈጸም እንደሚያስችላቸው የታመነበት በመሆኑ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ መሰረትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ሆኖ አካዳሚያዊ እና አስተዳደራዊ ነፃነቱ ተጠብቆ መንቀሳቅስ እንዲችል፣ በትምህርት ዘርፍ ለተጀመረው የሪፎርም እንቅስቃሴ ፈር ቀዳጅ ሆኖ እንዲወጣ እድል ይፈጥርለታል ተብሏል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ ስርዓትን በቀዳሚነት ተግባራዊ እንደሚያደርግና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተምሳሌት እንደሚሆን ይጠበቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ ከፍለናል ሰነዱ በእጄ አለ፤ ከለቀቋቸው በኃላ ድጋሜ በመያዝ 6 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል " - ቀጣሪ ድርጅቱ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ በግል ድርጅት ተመልምለው ወደ ስፍራው በአማራ ክልል፣ በምስቅው ጎጃም ፣ ጎዛመን በኩል አቋርጠው ሲጓዙ የካቲት 18/2016 ዓ/ም " በፋኖ ታጣቂዎች " ታገቱ የተባሉ ሠራተኞች እስካሁን ከእገታ አልተለቀቁም ሲል…
#Update

" ታጋቾቹ ተለቀው በሰላም #አዲስ_አበባ ገብተዋል " - የጋርዱላ ዞን አስተዳደር

" ለማስለቀቂያ መጀመሪያ ከከፈልነው 4 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በእያንዳንዱ መኪና (4 መኪናዎች) 500 ሺህ ብር ከፍለናል " - ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን

" አንድም ገንዘብ አልተቀበልንም " - ፋኖ ማርሸት ፀሀይ

በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ታግተዋል የተባሉ የቀን ሰራተኞች ከእገታው ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ፤ " በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሐይቅ የሚያርፍበት ስፍራን ለመመንጠር ከዞኑ 246 ተመልምለው ሲጓዙ የነበሩና በአማራ ክልል የታገቱ ሠላማዊ ዜግች ተለቀዋል " ብሏል።

ታጋቾቹ ትላትን ምሽት መለቀቃቸውን ያሳወቀው የዞኑ አስተዳደር ዛሬ በሠላም ተጉዘው አዲስ አበባ መድረሳቸውን አሳውቋል።

ወደ ህዳሴው ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ ሲሄዱ የታገቱት 272 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጾ የነበረው ቀጣሪ ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ታጋቾች መለቀቃቸውን አረጋግጧል።

የተለቀቁት ግን 271 ሰራተኞች እንደሆኑና 1 ሰው ሾልኮ መጥፋቱን ነገር ግን ከቤተሰብ ጋር መደዋወሉን አመልክቷል።

ድርጅቱ በመጀመሪያ #ለማስለቀቂያ 4 ሚሊዮን ብር ከፍሎ እንደነበር ተለቀው ሲሄዱ አማኑኤል አካባቢ ድጋሚ በሌላ የቡድኑ ክንፍ ተይዘው ለማስለቀቂያ 6 ሚሊዮን ብር መጠየቁን በኃልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር ተከፍሎ ሰራተኞቹ መለቃቃቸውን አሳውቋል።

' የአማራ ፋኖ ምስራቅ ጎጃም ቃል አቀባይ ' ፋኖ ማርሸት ፀሀይ " ' ሰራተኞች ' የተባሉት ወደ ብርሸለቆ ሲያመሩ የነበሩ ምልምል ወታደሮች ናቸው ፤ ይመሯቸው የነበሩትም ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች ነበሩ ፤ ምርኮኞች እንጂ ታጋቾች አይደሉም፤ ቁጥራቸውም 246 ነው " ብለው ነበር።

ትላንትና በሰጡት ቃል ፤ የግለሰቦቹን መለቀቀ አረጋግጠው ፤ " የተለቀቁት 240 ናቸው። አንድም ብር አልተቀበልንም " ብለዋል።

"ልጆቹን እንዲረከበን የቀይ መስቀል ማህበረን ጠይቀን ቀርቷል ፤ ሊቀበለንም አልቻለም። እኛ ከልጆቹ ጋር ባደረግነው ስምምነት የትራንስፖርት ወጪያቸውን ብንሸፍን በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚሄዱ ስለተነጋገርን እነሱም ስላመኑበት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሸኝተናቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፤ " ፋኖ ገንዘብ አይቀበልም። ገንዘብ መቀበል ብንፈልግ ኖሮ እኮ ከሁሉም እንቀበል ነበር። ከአንዱ ተቀብለን ከአንዱ የማንቀበልበት ምክንያት የለም። በስነስርዓት ለመከላከያ ስልጠና የሚመጡ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ገንዘብ ተጠይቀናል ወደ ሚል ስም ማጥፋት ገብተዋል ምክንያቱም አላማቸው ስለተስተጓጎለ " ብለዋል።

" ገንዘብ ከማንም አልጠየቅንም " የሚሉት ማርሸት " እንደውም ለተሽከርካሪ ነዳጅ ሞልተናል፣ የሹፌሮች አበል ሰጥተናል እውነቱ ይሄ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ታግተው የነበሩ ሰራተኞች ለማስቅለቅ በቅድሚያ 4 ሚሊያን ብር በሶስት ሰዎች ስም የገባበት ማስረጃ በእጁ እንዳለና በቀመጠልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር መክፈሉን አሳውቋል።

የጋርዱላ ዞን እንዳሳወቀው 246 ታጋቾች ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል። ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች፣ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ የአማራ ክልል የመንግስት አካላት በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች የሃይማኖት ተቋማት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ትልቅ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ከጋርዱላ ዞን ኮሚኒኬሽን እንዲሁም ከቪኦኤ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Ethiopia

ትላንትና ማክሰኞ #ከሀዋሳ ወደ #አዲስ_አበባ በመብረር ላይ እያለ የደኅንነት ችግር ሊያስከትል የሚችል ክስተት በገጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር #ET154 ላይ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጥልቅ የሆነ የደኅንነት ምርመራ ሊያደርግ እንደሆነ ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ትላንት ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ከፍተኛ ጭስ መከሰቱን፣ ነገር ግን በመንገደኞች ላይም ሆነ በአውሮፕላኑ ላይ ምን ዓይነት እክል ሳይፈጠር ቦሌ ኤርፖርት በሰላም ማረፉ መገለጹ ይታወሳል።

አውሮፕላኑ ውስጥ ለጊዜው በምን ምክንያት እንደተነሳ ያልታወቀው ጭስ መንገደኞችን ከፍተኛ ድንጋጤና ፍርኃት ውስጥ አስገብቷቸው ነበር።

የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪ ባስተላለፉት የደኅንነት ጥንቃቄ ዕርምጃ መሠረት ሁሉም ተሳፋሪዎች በአውሮፕላኑ ላይ የተገጠመውን የአየር መሳቢያ የፊት ጭምብል (oxygen mask) እስከማድረግ ደርሰው ነበር።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የበረራ ደኅንነት ክፍል እክል የገጠመው አውሮፕላን ቀጣይ በረራ እንዳያደርግ በማገድ በበረራ ወቅት ያጋጠመውን የደኅንነት ክስተት እንደሚያጣራ ሪፖርተር ጋዜጣ ስማቸው ያልተገለጹ የተቋሙን ምንጮች ዋቢ በማድረግ አስነብቧል።

እኚሁ ምንጮ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አየር መንገዱ በሚሰጠው የአገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት ላይ የደኅንነት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ክስተቶች ደጋግመው መከሰታቸውን አስታውሰው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን አጠቃላይ የደኅንነት ፍተሻ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ባለፈው ጥር ወር 2016 ዓ/ም ላይ ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ ሲበር የነበረ አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባ ነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት ከማረፊያው አስፋልት ውጪ የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ይታወሳል።

ሌላው የመንገደኞች አውሮፕላን በተመሳሳይ በአርባ ምንጭ አውሮፓላን ማረፊያ ከማረፊያ መስመሩ (ራንዌይ) የመውጣት እክል ገጥሞት እንደነበር ተስምቷል።

በአጠቃላይ በአንድ ዓመት 4 የደኅንነት እክሎች የተመዘገቡ መሆኑን ጋዜጣው ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ጠቁሟል።

ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ ከተማ ሲበር የነበረውን ጨምሮ እክል ያጋጠማቸው አውሮፕላኖች ' #Q400 ' በመባል የሚታወቁት አየር መንገዱ በአገር ውስጥ እና ወደ ጎረቤት አገሮች ለሚደረጉ በረራዎች የሚገለገልባቸው ናቸው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካሉት 178 አውሮፕላኖች መካከል 33 የሚሆኑት Q400 በመባል የሚታወቁት ለመካከለኛ ርቀት የሚጠቀምባቸው አውሮፕላኖች ናቸው። #ሪፖርተር

@tikvahethiopia
159_በመንደር_የንግድ_ቁጥጥር_የአሠራር_ሥርዓት_መመሪያ_ቁጥር_159_2016.pdf
436.8 KB
#AddisAbaba

አዲሱን " በመንደር ንግድ ቁጥጥር አሰራር ስርዓት መመሪያ 159/2016 " የተያያዘውን ፋይል ከፍተው በዝርዝር ያንብቡ።

#አዲስ_አበባ_ንግድ_ቢሮ

@tikvahethiopia