TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በፀጋ በላቸው ላይ የጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሰው ኮንስታብል የኋላመብራት ወልደማርያም በ16 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል። የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም በፆታዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰሩት አበባየሁ ጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ውሳኔው የከተማውን ገፅታ የሚያበላሽ እንደሆነ ስለታሰበ ነው መፍትሄ ያገኘው ብለዋል። አበባየሁ ጌታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው…
" ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ሰምቻለሁ " - ጸጋ በላቸው

" ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለኔ አዲስ ነው " - ወ/ሮ ወይንሸት ብርሀኑ

በሀዋሳ ከተማ የዳሽን ባንክ ሰራተኛ ከሆነችዉ ጸጋ በላቸዉ ጋር በተያያዘ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ  የነበረው ኮንስታብል የኃላመብራት ወ/ማርያም " ለብዙዎች አስተማሪ ይሆናል " በተባለ መልኩ የ16 አመት ጽኑ እስራት እንደተፈረደበት ይታወሳል።

ይሁንና ይህ ለሚዲያ የተገለጸው ፍትህ ከተበዳዩዋ እውቅና ውጭ በሆነ መልኩ የእስራት ፍርዱ ከ16 አመት ወደ 10 መቀነሱን እንደሰማች በሶሻል ሚዲያ ባስተላለፈችዉ በዕንባ የታጀበ ቅሬታ ገልጻለች።

ወይዘሪት ጸጋ ፤ ጉዳዩን ለማወቅ ብዙ ድካም እንደነበረዉና በመጨረሻ የሰማችዉ ጉዳይ እጅግ እንዳሳዘናት በመግለጽ አቤቱታዋን አሰምታለች።

ጸጋ ፤ " የፍርድ ሂደቱ በጥሩ ሂደት ሄዶ ፍርድ ቤት 16 ዓመት ተፈርዶበታል በሚል ለኔ ውሳኔ ሰጥቶኝ ነበር ፤ አሁን ግን እኔ በማላውቅበት ሁኔታ የፍርዱ ውሳኔ ይግባኝ ብሎ #እንደተስተካከለ ሰምቻለሁ፤ ይህ ውሳኔ መቼ እንደተላለፈ አልተነገረኝም ለግል ጉዳዬ የውሳኔ ወረቀት እንዲሰጠኝ  በተደጋጋሚ ወደ ፍርድ ቤት በምደውልበት ጊዜ ምላሽ እየተሰጠኝ አልነበረም ጉዳዩን አጥብቄ በተደጋጋሚ ስጠይቅ ውሳኔው በይግባኝ እንደተስተካከለ ተነገረኝ " ስትል አስረድታለች።

ውሳኔው አሁን ላይ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ የገለፀችው ጸጋ ፤ በድርጊቱ እጅግ እንዳዘነችና ካሳለፈችው የስቃይ ሁኔታ ጋር በፍፁም እየሚገባ እንዳልሆነ በእምባ ታጅባ ገልጻለች።

ከዚህ ባለፈ ህዝብ የማያውቀው ብዙ ነገር እንደተፈፀመ ፤ ከጠለፋው እገታ ከተለቀቀች በኃላ በማታውቀው ምክንያት ታስራ እንደነበር አመልክታለች።

ፍርዱ ለሚዲያ 16 ዓመት ከተባለ በኃላ ወደ 10 ዓመት ዝቅ እንዳለ ገልጻ ፤ " ይህ አይነት ተግባር ለቀጣይ ምን እንደሚያስተላልፍ አላውቅም " ብላለች።

ውሳኔው ተግቢና ትክክል እንዳልሆነ ፤ በድብቅ ሊሆን እንደማይገባው፣ እንዲከላከሉም ሊደረጉ እንደሚገባ አስገንዝባለች።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በተመለከተ ጥያቄ ያቀረበላቸዉና የጸጋን ጉዳይ ሲከታተለዉ በነበረዉ የሀዋሳ ከተማ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ ውስጥ የሴቶችና ህጻናት መብትና ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ የሆኑት ወይዘሮ ወይንሸት ብርሀኑ ጉዳዩ ለቢሮዉም ሆነ ለእርሳቸዉ አዲስ መሆኑን ገልጸዋል።

ወይዘሮ ወይንሸት ፤ ጉዳዩን እንደሚከታተሉትና የተፈጠረዉን ጉዳይ እንደሚያጣሩ በመግለፅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃል ገብተዋል።

መረጃዉን አጠናቅሮ የላከዉ የሀዋሳዉ ቲኪቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነዉ።

@tikvahethiopia