TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ተጠንቀቁ

• " የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን ከሚሉ አጭበርባሪዎች ራሳችሁን ጠብቁ " - ብሄራዊ ባንክ

• " ድርጊቱ በህግ የሚያስጠይቅ ነው " - ፖሊስ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ " የአንድ ብሩን ሳንቲም በሺዎች በሚቆጠር ገንዘብ እንገዛለን " ከሚሉ አጭበርባሪዎች ኅብረተሰቡ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠው ቃል ፤ ከሰሞኑ በተለያዩ ማኅበራዊ ድረገፆች " አራት የግዕዝ ፊደላት ያሉትን የአንድ ብር ሳንቲም በ2 ሺህ ብር እና ከዚያም በላይ እንገዛለን " የሚሉ ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች በስፋት ተስተውለዋል ብሏል።

ማስታወቂያዎቹ ኅብረተሰቡን ለማጭበርበር እየተነገሩ ያሉ እና ከእውነት የራቁ በመሆናቸው ፤ ኅብረተሰቡ ራሱን ከአጭበርባሪዎች ሊጠብቅ እንደሚገባ ገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ በበኩሉ፣ ድርጊቱ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጾ በዚህ ማጭበርበር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ግለሰቦች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ ማስጠንቀቁን ቴሌቪዥን ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ተጠንቀቁ

UNICEF 2,800 ሰራተኞችን ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል ?

UNICEF ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወረውን አይነት ምንም የቅጥር ማስታወቂያ #አላወጣም

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምትመለከቱት አይነት ሀሰተኛ የቅጥር ማስታወቂያ በስፋት እየተዘዋወረ ነው።

ማስታቂያው UNICEF በትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለሚገኙ ዜጎች በ3 የስራ መደቦች የተመዘገቡ ሰራተኞችን አሰልጥኖ ለመቅጠር ይፈልጋል የሚል ነው።

በዚሁ ሀሰተኛ የቅጥር ጥሪ ፤ በባችለር ዲግሪ ፣ በማንኛውም ትምህርት መስክ ፣ በ0 ዓመት ፣ በ24,700 ብር ደመወዝ 2,800 ሰራተኞች እንደሚፈለጉ ይገልጻል።

በጣም የሚያስገርመው የስራው አመልካቾች የሚያመለክቱበት ሀሰተኛ አድራሻ የተቀመጠ ሲሆን በዚሁ አድራሻ ተመዝጋቢዎች የማመልከቻ ፎርም ሲሞሉ 1,000 ብር በCBE Birr ወይም በTelebirr ቀድመው እንዲከፍሉ ይጠይቃል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ይህ ፍፁም ሀሰተኛ እንዲሁም በርካታ ወጣቶችን ለማጭበርበር እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ በመሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከUNICEF ተጨማሪ መረጃ ያገኘ ሲሆን በኦንላይን እየተሰራጨ ያለው ሀሰተኛ የቅጥር ማስታወቂያ መሆኑን ገልጿል።

UNICEF የስራ ዕድል የሚያስተዋውቀው በይፋዊ ድረገፁ unicef.org/careers/ ላይ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል። ከዚህም ባለፈ በየትኛውም የቅጥር ሂደት ገንዘብ እንደማያስከፍል እንዲሁም የባንክ መረጃን እንደማይጠይቅ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ተጠንቀቁ⚠️

በምስሉ የተያያዙት በኦንላይን " ቀላል በሆነ ስራ ብዙ ትርፍ ታገኛላችሁ " በሚል #የማጭበርበር ስራ ተታለው ገንዘባቸውን የላኩ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ እና ያጨብረበሯቸውን አካላት የቴሌግራምና የዋትአፕ አድራሻ የሚያሳይ ነው።

" ቀላል ስራ፣ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ " በሚል ከ65 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ።

ምንም እንኳን አጨብረባሪዎቹ በውጭ ሀገር ስልክ የሚያጭበረብሩትን ሰው ቢያናግሩም የገንዘብ ልውውጡ እንዲደረግ የሚያደርጉት እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለ አካውንት ነው።

ገንዘብ የሚያስልኩትም የሚልኩትም እጅግ በጣም በበዙ አካውንቶች ነው። (ይህም በኦንላንይ የክሪፕቶ ግብይት ሊሆን እንደሚችል አንድ ባለሞያ ለቲክቫህ ጠቁመዋል)

ማሳሰቢያ ፦ በተለያዩ የማጭበርበሪያ ግሩፕ ውስጥ ያሉት ሰዎች ለማጭበርበር የተሰማሩ አልያም በሆነ ቡድን የሚመሩ ሲሆን ፕሮፋይል ምስላቸው የታወቂ ሰዎች / ዝም ብሎ ከኢንተርኔት የተገኙ የሴቶች / የወንዶች ፎቶ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጠንቀቁ⚠️ በምስሉ የተያያዙት በኦንላይን " ቀላል በሆነ ስራ ብዙ ትርፍ ታገኛላችሁ " በሚል #የማጭበርበር ስራ ተታለው ገንዘባቸውን የላኩ ሰዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ እና ያጨብረበሯቸውን አካላት የቴሌግራምና የዋትአፕ አድራሻ የሚያሳይ ነው። " ቀላል ስራ፣ ብዙ ትርፍ የሚያስገኝ ስራ " በሚል ከ65 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ምንም እንኳን አጨብረባሪዎቹ በውጭ ሀገር…
#ተጠንቀቁ ⚠️

ከኦንላይ ዘራፊና አጭበርባሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ።

ነገሩ እንዲህ ነው ...

ገንዘባቸውን ኦንላይን ተጭበርብረው የተበሉ ግለሰቦች መጀመሪያ በማያወቁት የውጭ ሀገር ስልክ ቁጥር በ #ዋትስአፕ / በ #ቴሌግራም መልዕክት ይደርሳቸዋል። ስልካቸውን / username እንዴት እንደሚያገኙት ባይታወቅም።

የሚደርሳቸው መልዕክት " ጥሩ የስራ እድል እንደሆነ ፣ በትንሽ ስራም ብዙ ትርፍ እንደሚያገኙ ፣ ይህ እድል ለነሱ የተመቻቸ " እንደሆነ የሚገልጽ ነው።

ቅድመ ክፍያ እንደሌለው ፤ ከ100 ብር አንስቶ እስከ 50 ሺህ ብር በቀን የሚያስገኝ እንደሆነም መልዕክቱ ይገልጻል።

እነዚህ አጭበርባሪዎች የሚያጭበረብሯቸው ሰዎች የሚያናግሩበት መንገድ ፍፁም ትህትና የተሞላበትና ፕሮፌሽናል በሆነ መንገድ ስለሆነ በተበዳይ ዘንድ ጥርጣሬ እንዳይጫር ያደርጋሉ።

ልክ የማግባባት ስራቸውን ከሰሩ በኃላ ትንሽ ተልዕኮ ሊሰጧቸው እንደሆነ በመግለፅ ወደ " ጎግል ማፕ/ ሎኬሽን " ገብተው ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አድራሻ ስር ጥሩ አስተያየት እንዲሰጡ ያዟቸዋል። (ይህ ከማጭበርበሪያ መንገድ አንዱ እንጂ ብቸኛው አይደለም)

የሚጭበረበረውም ሰው እጅግ በጣም ቀለል ያለ ስራ ስለሆነ የተሰጠውን ተልዕኮ መወጣቱን የሚገልጽ screenshot ለአጭበርባሪዎቹ  ይልካል። እነሱም አካውንቱን ይጠይቃሉ።

ከዚህ በኃላ ነው ዋናው ጨዋታ የሚጀመረው።

ሰዎቹ ለተሰራው ስራ ክፍያ በሚል ከ300 - 1,000 ብር ከዚህም ከፍ ያለ ገንዘብ ያስገባሉ። ይህ ሰዎችን የማሳመኛና እንዳይጠራጠሩ ማድረጊያ መንገዳቸው ነው።

ይቀጥሉና ታስክ ይሰጣችኋል ስሩ ይላሉ። በተሰራው ስራ ልክም የተወሰነ ገንዘብ ይልካሉ። ይህ እንደ ሰውየው የመክፈል አቅም እየተገመገመ የሚደረግ ነው።

በዚህ መኃል ላይ " ኮሜርሻል ቤኔፊት " የሚል ነገር ያመጣሉ ይኸውም ከ1,000 ብር እስከ 1,000,000 ብር ሰዎች እንዲያስገቡ የሚጠይቅ ነው። ሰዎች ባስገቡት ብር ልክም በሰሩት ቀላል ስራ በፐርሰንት ትርፍ እንዳለው ይነገራቸዋል።

ለምሳሌ ፦ የሚጭበረበረው ሰው በዚህ ማታለያ ተታሎ 1000 ብር ቢያስገባ ሰዎቹ መልሰው በደቂቃ ውስጥ 1500 ብር አድርገው ያስገባሉ። (ይህ አንዱ የማሳመኛ መንገዳቸው ነው)

በዚህም የሚጭበረበረው ሰው ብሩን ከፍ በማድረግ ብዙ ትርፍ ለማግኘት ሲል በዛ እያደረገ ብር ይልካላቸዋል።

የተጭበርባሪውን ሰው የመክፍል አቅም ገምግመው አጭበርባሪዎቹ የተላከው ብር ላይ 500ም ይሁን 5000 ብር ጨምረውበት መልሰው ይልካሉ። (ይህን እድታምኗቸውና ብዙ ብር እንድታስገቡ ማሳመኛ ነው)

ድጋሚ ሌሎች ስራዎዥ ይላሉ በዚህም ከፍ ያለ ብር እንድታስገቡ ያደርጋሉ። የላካችሁትን ብር እንዳታጡ የሚሳጣችሁን ስራ እንድትወጡ ይጠየቃል። እናተም ብራችሁ ተበልቶ እንዳይቀር የብሩን መጠን ከፍ ወደማድረግ ትሄዳላችሁ። (በዚህ ሁሉ ሂደት ግን ሰዎቹ የምክፈል አቅማችሁን እያጠኑና ከፍ ያለ ብር ከቻሉ እስከ #ሚሊዮን ለመቀበል ጥረት ያደርጋሉ ስለሆነም በመሃል በመሃል የሰራችሁበትን እያሉ ያራሳችሁን ብር መልሰው ይልኩላችኃል)

የመክፈል አቅማችሁንም አይተው ለዚህ ማጭበርበር ስራ ታልሞ ብቻ ወደ ተከፈተው ግሩፕ እንድትገቡ ይደረጋል። (ሁሉም ግሩፑ ውስጥ ያለው አካውንት የአጭበርባሪዎቹ ነው)

እንዲህ እንዲህ እያለ በዛ ያለ ብር ከፈፀማችሁ በኃላ ስህተት ሰርታችኋልና እሱን ለማረም ስራችሁን ቀጥሉ ይላሉ። እናተም ብራችሁን ላለማጣት ውስብሰብ ችግር ውስጥ ትወድቃላችሁ።

በመጨረሻም እየተጭበረበራችሁ እንደሆነ ስታውቁ ታቆማላችሁ። ብራችሁም መና ሆኖ ይቀራል። ሰዎቹ ግን ብር አስገቡ ያኛውን ብር ለማስመለስ ማለታቸውን ይቀጥላሉ።

ብር የሚያስልኩት ኢትዮጵያ ባለ ሰው አካውንት ነው። 

በዚህ መንገድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባጣራው ብቻ ከ150 ሺህ ብር እስከ 600 ሺህ ብር የተበሉ አሉ። ይህም የሰዎችን ህይወት አመሰቃቅሏል።

ለምሳሌ ፦ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሆነው ስማቸውን በይፋ መግለፅ የሚያስፈልግ ሰዎች #የተጭበረበሩት የገንዘብ መጠን እንደሚከተለው ቀርቧል ፦
1. 600 ሺህ ብር
2. 470 ሺህ ብር
3. 300 ሺህ ብር
4. 300 ሺህ ብር
5. 150 ሺህ ብር
6. 150 ሺህ ብር
7. 100 ሺህ ብር
8. 80 ሺህ ብር
9. 80 ሺህ ብር
10. 65 ሺህ ብር

ይህ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነው።

በመሆኑንም ፦

1ኛ. ማንኛውም የቴሌግራም ሆነ የዋትስአፕ የውጭ የማይታወቅ መልዕክት አትመልሱ።

2ኛ. በምንም ተአምር በትንሽ ብር ኢንቨስት አድርጉና ትርፍ አግኙ የሚሉ ሰዎችን አታናግሩ አትመኑ ተጠራጠሩ።

3ኛ. አሁንም በዚህ ውስብስብ ነገር ውስጥ ያላችሁ ተጨማሪ ብር እንዳትበሉ አቁሙ።

በቀጣይ በዘርፉ ያለ የባለሞያ አስተያየት እናቀርባለን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እንደ ባሪያ ነው የምንታየው ፤ እባካችሁ ጭሁልን !! " - በማይናማር የሚገኙ ወጣቶች ማይናማር እና ታይላንድ ድንበር ላይ ከሚገኙ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የበየነ መረብ ማጭበርበር (Online Scam) ተግባራት ከሚፈጸምባቸው አንዳንድ ቦታዎች ቲክቫህ ኢትዮጵያ መልዕክቶችን በቴሌግራም እየተቀበለ ይገኛል። እነዚህ ቦታዎች ላይ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች ያሉ ሲሆን " ታይላንድ እንልካችኋለን " በሚል…
🔈 #ተጠንቀቁ

ወደ ተለያዩ ውጭ ሀገራት " ስራ ነው " በሚል ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ ወጣቶቻችን የትም ሀገር ይሁን የምትሄዱት ስራው ምን እንደሆነ እና ለደህንነታችሁም አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጡ።

" ለስራ ውጭ እንላካችሁ " የሚሉትን ደላሎችንም ሆነ ኤጀንሲዎች ፦
- ስራው ምንድነው ?
- በትክክል ድርጅቱ ያለበት ሀገር የት ነው ?
- የድርጅቱን ህጋዊነት የሚያሳይ ማስረጃ አሳዩን !
- ባለበት ሀገር ሕጋዊ ስርዓት የተመዘገበበትን ፋይል አሳዩን ! ብላችሁ ጠይቋቸው።

ከዚህ ውጭ በተድበሰበሰ ሁኔታ " ጠቀም ያለ ገንዘብ ነው የምታገኙት " በሚል ብቻ መረጃ ፤ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ የሚደረግ የውጭ ሂደት ብታቋርጡ መልካም ነው።

አንዳንድ ስለ ገንዘብ እንጂ ፍጹም ስለ ሰው ህይወት የማያሳስባቸው ደላሎች እና ኤጀንሲዎች በርካታ ወጣቶችን እያታለሉ መጀመሪያ ወዳሉት ሳይሆን ወደ ሌላ ምንም ደህንነቱ ወዳልተረጋገጠ ሀገር እየላኩ ሰዎችን በማጭበርበር ላይ ወደ ተሰማሩ ድርጅቶች እያስገቧቸው ነው።

በነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በሚቆዩበት ወቅት በርካታ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች ይፈጸምባቸዋል።

የወጣትነት ጊዜያችሁ ሳያልፍ ህይወታችሁን ለማሻሻል ብላችሁ እጅግ ተቸግራችሁ ፤ ቤተሰብም አስቸግራችሁ ብዙ ብር ከፍላችሁ ወደ ውጭ ሀገር የምትሄዱ ልጆች ስለምትሄዱበት ሀገር እና ስራ በደንብ አጣሩ አንብቡ።

ዘመኑ  የቴክኖሎጂ  ነውና በስልካችሁ ላይ ገብታችሁ የምትሄዱበት ሀገር ስላለው ደህነት፣  ስላለው የስራ ሁኔታ ፣ እናተም ትስሩታላችሁ ስለሚባለው ስራ በደንብ አረጋግጡ።

በኦንላይን የማያታውቁት ሰው ወይም በማስታወቂያ " ለስራ ወጣቶችን እንፈልጋለን " ሲሉ አትመልሱላቸው።

⚠️ በቀጣይ " ጠቀም ያለ ገቢ የሚያስገኝ ስራ ነው ! " እየተባለ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት በብዛት ወጣቶችን በማዘዋወር አንዳንድ ድርጅቶች እያስገቡ ወጣቶችን የሚያሰሯቸውን የኦንላይን ማጭበርበር  / Online Scam / ድርጊት አይነቶችን በዝርዝር እንዳስሳለን።

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM