TIKVAH-ETHIOPIA
#አህያ🫏 " ወደፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ አህዮችን ለማረድ ዕቅድ አለኝ " - አሰላ የሚገኘው የአህያ ቄራ አሰላ ከተማ የሚገኘው የአህያ ማረጃ ቄራ " የአህያ ምርቶች በሙሉ ለቻይና ገበያ የሚቀርብ እንጂ አገር ውስጥ የሚቀር ምርት የለም " አለ። " ሮግቻንድ " የተባለው የአህያ ማረጃ ቄራ አስተባባሪ የሆኑት ቺቺ አማን ቄራው በቀን ከ50 እስከ100 አህዮችን እያረደ ቆዳቸውን፣ ሥጋቸውን እና አጥንታቸውን…
#አህያ🫏
ሰሞኑን የአህያ ሥጋ በሆቴሎች ለምግብ እየቀረበ ነው የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ተስተውለዋል። ይህን ተከትሎም ነጋዴዎች የከብት ሥጋ ብናቀርብም የአህያ ሥጋ ነው በሚል የንግድ መቀዛቀዝና ኪሳራ ገጠመን ሲሉ አማረዋል።
በአዲስ አበባ ሆቴል ቤቶች ምግብ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ሥጋ የመመገብ ፍላጎታቸው እንደተዘጋ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ የሆነው የአህያ ሥጋ በአሰላ ሥጋ ቤቶች ተቀላቅሎ ለማኅበረሰቡ እየተሸጠ ተገኝቷል መባሉን ተከትሎ ባደረባቸው ሥጋት ጭምር ነው።
ብሩክ ኢትዮጵያ በእንስሳት ጤና አጠባበቅ ጥበቃና ደኅንነት አለም ዓቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት የማማከርና ልማት ባለሙያ ፍቅር ሽፈራው ከቀናት በፊት ፤ " ኢንፎርማሊ ባደረግነው አሰስመንት ወደ ምግብ ሥርዓቱ እየገባ ነው። ወደ ማኅበረሰቡ ከሥጋ ቤቶች ተቀላቅሎ የአህያ ሥጋ ወደ መሸጥ እየሄደ ነው " ሲሉ አሰላ ስላለው ሁኔታ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
አክለውም ፣ " ባለፈው የዛሬ ሁለት ሳምንት አካባቢ አሰላ ጋ አንድ ሦስት የሥጋ ቤቶች ተገኝተዋል፣ አይደንቲፋይ ተደርገዋል፣ የአህያ ሥጋዎችን መሸጥ የጀመሩ ማለት ነው " ማለታቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተንቀሳቃሽ ምስል ተመልክቷል።
የተቋማቸው ሠራተኛ ስለአሰላ ሥጋ ቤቶች የአህያ ሥጋ አቀላቅለው እየሸጡ መያዛቸውን ስለመናገራቸው ፣ በአሰላ የአህያ ሥጋ ወደ ምግብ ሥርዓቱ እንደገባ የተቋማቸው ሠራተኛ እየመሰከረች ባለበት ሁኔታና የአህያ ቄራ በተፈቀደባት አገር ማኅበረሰቡ የአህያ ሥጋ ከሌሎች ከብቶች ሥጋ ጋር እየተቀላቀለ አይሸጥም ብሎ ማሰብ እንዴት ይቻለዋል ? ለዚህ ማረጋገጫ ምን ዋስትና አላችሁ ? የአህያ ሥጋ ከሌሎች የከብት ሥጋዎች ጋር እንዳይቀላቀልስ በምን መልኩ ነው የምታጣሩት ? ምንስ ዋስትና አለ ? የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያብራሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለድርጅቱ አቅርቧል።
የድርጅቱ ከንትሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ ቃሲም ምን ምላሽ ሰጡ ?
- ብሩክ ኢትዮጵያ የአህያ ሥጋ ወደ ምግብ ሥርዓቱ ገብቷል ብሎ ያጠናው ምንም አይነት ጥናት የለም።
- ይሄን መረጃ ትክክለኛነቱን ነው የምንጠራጥረው። ምክንያቱም ትክክል ከሆነ መረጃውን ያስተላለፉት ግለሰብ ለተናገሩት መረጃ ማስረጃ እንዲያቀርቡ ማድረግ ያስፈልግ ነበር።
- ሆኖ ከተገኘ ደግሞ ሊያስተላልፉት የሚችሉ የጤና መሰል ቀውሶች ከባድ ስለሆኑ እዚህ ያለውን ነገር አንድ ግለሰብ ተናገረ ተብሎ ሚዲያ ላይ ከማውጣት የተናገሩት ግለሰብ ከምን ተነስተው እንደንደተናገሩ፣ ተዘጉ የተባሉ ሉኳንዳ ቤቶች የትኞቹ ናቸው ? እርምጃ የወሰደው አካል ማነው ? የሚሉትን ጥያቄዎች ሁሉ መጣራት ነበረባቸው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ የድርጅቱ የማማከር እና ልማት ባለሙያ ፍቅር ሽፈራውን ምን ማብራሪያ እንዳላቸው ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ #አልተሳካም።
በተያያዘ ፤ አህዮች ታርደው ወደ ውጪ እየተላኩ ያሉት አጥንታቸው ጭምር ሳይቀር ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን የአህያ ቄራ አስፈለገ? የአህያ ቄራ አገር ውስጥ ካለ ሥጋው ተቀላቅሎ ለምግብነት እንዳይቀርብ ለማድረግ ስለሚያስቸግር አህያን የሚፈልጉ አገራት ለምን አህዮቹን ከነነፍሳቸው ጭነው አይወስዱም? የሚሉ ጥያቄዎችም በማኅበረሰቡ ዘንድ ሲሰነዘሩ የተስተዋሉ ሲሆን፣ ለዚሁ ሀሳብ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለብሩክ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
የድርጅቱ ዳይሬክተር በሰጡት ምላሽ ፥ " አህዮች ለቆዳቸው ሲባል መታረድ የለባቸውም የሚል አቋም ነው ያለን። በቁምም ተንድተው ታረዱ፣ አገር ውስጥም ታረዱ ከዚህ ሥጋት ነጻ መሆን አለባቸው። አህዮች መታረድ የለባቸውም የሚል ጠንካራ አቋም ነው ያለው ድርጅቱ " ብለዋል።
ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-29

Telegraph
Tikvah-Ethiopia
#አህያ ሰሞኑን የአህያ ሥጋ በሆቴሎች ለምግብ እየቀረበ ነው የሚሉ መረጃዎች ሲራወጡ ተስተውለዋል። ይህን ተከትሎም ነጋዴዎች የከብት ሥጋ ብናቀርብም የአህያ ሥጋ ነው በሚል የንግድ መቀዛቀዝና ኪሳራ ገጠመን ሲሉ አማረዋል። በአዲስ አበባ ሆቴል ቤት ምግብ ተጠቃሚዎች በበኩላቸው ሥጋ የመመገብ ፍላጎታቸው እንደተዘጋ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ይህ የሆነው የአህያ ሥጋ በአሰላ ሥጋ ቤቶች ተቀላቅሎ ለማኅበረሰቡ እየተሸጠ…