TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የሰራተኞችድምጽ

" የደመወዝ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በፖሊስ መደብደባችንን እና መታሰራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን !! " - የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች

" ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ችግር እና ቅሬታቸውን ለመግለጽ ወደዞን መምሪያ በመሄድ ላይ ሳሉ በፖሊስ ተደብድበው መመለሳቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

" ሰራተኞቹ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ካየን ይሄው ሶስተኛ ወራችን ቢሆንም የሆስፒታሉ አመራሮችም ሆኑ ዞኑ ለጥያቄያችን ምላሽ መስጠት እንኳን አልፈለጉም " ብለዋል።

" ይህንም ተከትሎ ለሆስፒታሉ አመራር ከዚህ በላይ መታገስም ሆነ ችግሩን መቋቋም እንደማንችል በደብዳቤ አሳዉቀን ሁኔታውን በተጨማሪ ለሀድያ ዞን አስተዳደር ለማሳወቅ ስናቀና የዞኑ  ፖሊስ ደብድቦ መልሶናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በህዝብ ትራንስፖርት ተሳፍረን ስንሄድ የዞኑ ፖሊስ ዱራሜ ላይ አስቁሞ በሀይል በማስወረድና በመደብደብ  ወደመጣንበት እንድንመለስ አደረገን " የሚሉት ሰራተኞቹ ወደ ሾኔ ሲመለሱ መሪዎች ናቸው የተባሉ ጥቂት ሰዎች ለሰአታት ታስረው መፈታታቸው ገልጸዋል።

" ከችግራችን በላይ እየደረሰብን ያለውን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ይስማልን " ያሉት የሆስፒታሉ ሰራተኞች " በዚህ አመት ከተከለከልነው ደሞዝ ባለፈም በ2015 ዓ/ም ያልተከፈለ  ውዝፍ ገንዘብ ነበረን " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን የደረሰባቸውን ነገር እና ቅሬታቸውን ይዞ የሾኔ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተእ ዶ/ር መሀመድን አህመድ አነጋግሯል።

እሳቸውም ሰራተኞቹ በደብዳቤ ስራ ማቆማቸውን ገልጸው ወደስራ መመለስ የሚፈልግ ደብዳቤ በማስገባት ስራ መጀመር እንደሚችልና የአንድ ወር ደመወዝም እንደሚከፈለው ገልጸዋል።

ሌሎች ቀሪ ክፍያዎችን በተመለከተ ወደፊት ለመክፈል መታቀዱን የገለጹት ኃላፊው ይህም ጉዳይ በክልልና በከተማ አስተዳደሩ የተያዘ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደምም የዚህ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ከደመወዝ እና ከጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ እየደረሰባቸው ስላለው ችግር ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የሰራተኞችድምጽ

° " ሰበብ እየተፈለገ ከስራ እየተባረርን ነው " - የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሰራተኞች

° " ከህግና ስርአት ውጭ የተሰናበተ አንድም ሰራተኛ የለም " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ


" የደቡብ ክልል መንግሥት ፈርሶ ሰራተኛዉ ሲበተን ደቡብ ኢትዮጵያ ቢደርሰንም እንደ ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ መብታችን ተከብሮ መስራት አልቻልንም " ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቢሮ ሰራተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

" ቢሮው መቀመጫውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ  ካደረገና ስራ ከጀመርን ጀምሮ በርካታ ግፍ እየተፈጸመብን ነው "  የሚሉት ከቢሮው የተባረሩ እና ያለጥፋታችን በከባድ ማስጠንቀቂያ ውስጥ ነን ያሉ  ሰራተኞች " ቅጣቶች እና ክሶች ያለህግና ስርአት የቢሮው ዲስፕሊን ኮሚቴ እንኳን በማያዉቀዉ መልኩ እየተተገበሩ ናቸው " ሲሉ ከሰዋል።

" በዚህ አመት ብቻ ስራ ከጀመርነዉ ዉስጥ ወደ 5 ሰራተኞች ያለማስጠንቀቂያ እና ህጋዊ ስርአት ከቢሮዉ ተገፍትረን ተባረናል " በማለት ገልጸዋል።

" ከቢሮ ተገፍትረን ከተባርንና ደሞዝ ከተቋረጠብን በኋላ ከስራ ገበታ መቅረታችን የሚገልጽ ደብዳቤ ይለጠፍብናል " የሚሉት ሰራተኞቹ  ጉዳዩን ለክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ  ብናሳውቁም መፍትሄ አላገኘነም ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን ቅሬት ይዞን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊን ዶክተር ኦንጋዮ ኦዳን አነጋግሯል።

እሳቸው ፥ " ከህግ እና ስርአት ውጭ አንድም ሰራተኛ አልተሰናበተም " ብለዋል።

" በደል ደርሶብኛል የሚል ካለም ለመነጋገርና ስህተት ተሰርቶ ከሆነ ለመጠየቅ ዝግጁ ነን " ሲሉ ቃል ገብተዋል።

" በብዛት ከቢሮዉ የለቀቁ ሰራተኞች ፦
- ከስራ በተደጋጋሚ የሚቀሩ
- መቀመጫቸውን ሀዋሳ ያደረጉ
- ተመላልሶ መስራትን ካለመፈለግ ነው " የሚሉት ኃላፊው " ቢሮ ሳይቀመጡ ስራ መስራት ደግሞ አግባብ አይደለም " ብለዋል።

ከዚህ ውጭ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ብዙ ጥረቶች ሲያደርጉ መቆየታቸውንም ገልጸዉ አብዛኞቹ ሰራተኞች ከስራ መቅረታቸውን ተከትሎ ህጋዊ ደብዳቤ መጻፉን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ሰራተኞች " ተበድለናል " ብለዉ ለቢው አቤቱታ ሲያስገቡ ምላሽ ለምን አለተሰጣቸውም ? ብለን ጠየቀናል።

ቢሮው ፥ ምንም እንኳን ተበዳዮች ማመልከቻ አስገብተናል ቢሉንም " በጉዳዩ ላይ መረጃዉ የለኝም " ሲል ምላሽ ሰጥቶናል።

ይሁንና እንዲህ አይነት ችግሮች ያሉባቸዉ ሰራተኞች ጥያቄና አቤቱታ ይዘዉ ከመጡ እንደሚያስተናግድና ለዚህም በአካል ወላይታ ሶዶ በሚገኘዉ ቢሮዉ ሊቀርቡ እንደሚገባ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የሰራተኞችድምጽ

" ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን

በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ።

ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም።

" ከፍተኛ የሆነና እስካሁን ያልተፈታ ቅሬታ አለን " ያሉት የተቋሙ ሰራተኞች ሰሞኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ምን አሉ ? ምንድነው እንዲህ አማሮ ወደ ህዝብ ያስወጣቸው ጉዳይ ?

➡️ ተቋሙ ይኸው ከ10 ዓመት በላይ ቢሆነም ዛሬም እጅግ ብዙ ነገሮቹና ክፍተቶች አሉበት።

➡️ ተቋሙን ከውድቀት መታደግ ያስፈልጋል።

➡️ ዘንድሮ ጥቅምት ላይ ከላይ አመራሮች አንስቶ ሪፎርም ተደርጎ ነበር። ፋይናንስ ላይ ሪፎርም አልተደረገም።

➡️ ምንም እንኳን በሪፎርሙ ብዙ ለመስራት ቢሞከርም ትልቅ ችግር የነበረው የፋይናንስ ስርዓቱ በዛው ነው የቀጠለው።

➡️የፋይናንስ ስርዓቱ በዛው በመቀጠሉ ከክፍያም ሆነ ከሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ትልቅ ችግር ነው ያለው።

➡️ የፋይናንስ ችግሩ ለመምህራን ፈተና ሆኗል። ይህ ሁኔታ በተማሪዎች ትምህርት ላይም የሚያሳድረው ተጽእኖ ከፍተኛ ነው።

➡️ አካዳሚክ ስታፎች ምንም አይነት የአቅም ማጎልበቻ የሚያገኙበት እድል የላቸውም። በሪሰርች፣ በሶፍትዌር ስልጠና ፣ በመማር ማስተማርም ...ይሁን በሌላ ምንም እየተሰጠ አይደለም። ለዚህ ጉዳዮች እቅድ ወጥቶ ፋይናንስ ላይ ይደውቃል።

➡️ ከመምህራን ክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር ነው ያለው።

➡️ በጫና ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ሰራተኞች በአግባቡ ከፍያ አያገኙም።

➡️ ከሌላ ዩኒቨርሲቲ ተጋብዘው የሚያስተምሩ መምህራን ለክፍያ ስቃይ ነው። መጀመሪያ ተጋብዞ የመጣ " ድጋሚ ወደዚህ አንመጣም ነው " የሚሉን።

➡️ ከክፍያ ጋር በተያያዘ ተጋባዦች ስለሚቸገሩ አንዳንዴ ኮርሶች ወደ ሌላ ጊዜ ይዞራሉ ይህ ደግሞ በተማሪዎች ላይ ጫና ያሳድራል።

➡️ ብዙ ላብራቶሪ ግቢው ስለሌለው ተማሪዎች የግድ መማር ስላለባቸው ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ ይላካሉ በዚህ ወቅት ከክፍያ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ መጓተት አለ። በመምህራን ክፍያም ላይ ችግር አለ። በዚህ ምክንያት ብዙ ትምህርቶች የላብራቶሪ የሚፈልጉ ትምህርቶች ድሮፕ ይደረጋሉ።

➡️ ኢተርንሺፕ የሚወጡ ተማሪዎች ክፍያም ችግር ነው። ተማሪዎች በዚህ በጣም ነው የሚጎዱት።

➡️ ተማሪዎችን ጠብቀው አጅበው የሚወስዱ የሴክዩሪቲ ሰዎችም ክፍያ ቶሎ አይፈጸምም ይጓተታል።

➡️ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን የሚመጡ መምህራን የሚያዙበት መንገድም ጥሩ አይደለም። ህግና ደንብ ተከትሎ ባለመስራት  ምክንያት ይጎዳሉ። እጅግ በጣም የክፍያ መጉላላት አለ።

➡️ የመንግሥት ተቋም መሆኑ እስኪያስጠረጥር ድረስ ነው የፋይናንስ ችግር ያለው።

➡️ በአግባቡ ስራ ስለማይሰራ የበጀት ችግር አለ። መከፈል ያለበት አይከፈልም።

➡️ ተቋሙ ችግር በበዛባት ቁጥር ውጤታማ ተማሪ ፍራት አይችልም። ይህም ባለፉት የመውጫ ፈተናዎች ታይቷል። በዘንድሮው አመት ከአምናው ያነሰ (29%) ተማሪዎችን ነው በመውጫ ፈተና ያሳለፈው።

.... ሌሎችንም አሉ ያሏቸውን ችግሮች በዝርዝር አሳውቀዋል።


የአካዳሚክ ጉዳይ ሰራተኞች፣  መምህራንና ሌሎች ከዚህ ቀደም ሪፎርም ሲደረግ የፋይናንስ ዘርፉ ማታለፉን አመልክተው ባለው ችግር የሚቀጥል ከሆነ ስራ ለመስራት እንደሚቸገሩ አሳስበዋል።

" ካልሆነ የአካዳሚክ ጉዳዩን እነሱ የፋይናንስ ሰዎች ይስሩት አናስረክባቸዋለን " ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።

ጉዱዩን በመለከተ ከሰሞኑን የፋይናንስ ስርዓቱ እንዲቀየር ፒቲሽን ፈርመው በ72 ሰዓት መልስ እንዲሰጣቸው እንዳስገቡ  ነገር ግን ምንም ምላሽ ሳይገኝ ሰዓቱ ማለቁን ጠቁመዋል።

" ያለው ችግር በውስጥ እንዲፈታ ጥረናል " ያሉት ሰራተኞቹ " ቢብስን ነው ወደ ህዝብና ሚዲያ የቀረብነው " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴፍ ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ አይተው ማስተካከያ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በዚህ አይነት የትምህርት ስርዓት ውስጥ የሚያልፉ ተማሪዎችን ነገ መውቀስ ስላማይቻል ዛሬ ያሉ ችግሮች ይፈቱ ብለዋል።

(መምህራኑና ሰራተኞቹ በፋይናንስ ሴክተር አሉ ያሏቸውን ችግሮች ዘርዝረው ፈርመው ያስገቡት ፒቲሽን ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተቋሙን ጉዳይ እስከመጨረሻ ይከታተላል። የተቋሙን አመራሮችና ኃላፊዎችንም ያነጋግራል።

#GambellaUniversity

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

° " በየጊዜዉ የደመወዝ መዘግየቱ ህይወትን ከባድ አድርጎብናል " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰራተኞች

° " አሁን ላይ ችግሩ ተቀርፏል ከዚህ በኋላ የደሞዝ መዘግየት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " -ምላሽ የሰጡን አመራር


" የደመወዝ መዘግየት ፈተና ሆኖብናል " ያሉ የደቡብ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ሰራተኞች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ደመወዝ በየወቅቱ ሳይከፈል አይደለም እየተከፈለን እንኳን ኑሮ ከባድ ሆኖብናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በተለያዬ ምክኒያት በ25 ወይም በ26 የሚገባዉ ደሞዝ እስከሁለት ሳምንት እየዘገዬ መግባቱ ችግር እየፈጠረብን ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ የሀምሌ ወር ደሞዛችን ባለመግባቱ ቤት አከራዮቻችን ሽሽት ላይ ነን " የሚሉት ሰራተኞቹ " ኑሮን ደግሞ የምታዉቁት ነው " በማለት የሚመለከታቸዉ አካላት ለችግራቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ ስሜ አይጠቀስ ብለዉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የድርጅቱ አመራር " አሁን ላይ ከሶስቱ ክልሎች ማለትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያና ከመእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የበጀት መልቀቅና ገንዘብ የማዘዋወር እንቅስቃሴ ተጀምሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሶስቱ ክልሎች በተጨማሪ የሲዳማ ክልል ገና ዉሳኔ ላይ አለመድረሱን የገለጹት ኃላፊው ከነሱም ጋር ያለው ሁኔታ ቀስ ብሎ በውይይት መፍትሄ እንደሚፈለግለትና ከዚህ በኋላ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የዚሁ ተቋም ሰራተኞች ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሰማታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

" ክፍያችን ከኑሮ ውድነት አንጻር በጣም የወረደ በመሆኑ ህይወት አስቸጋሪ ሆኖብናል " - በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ሰራተኞች

" በ1000 ብር ደሞዝ ኑሮን መቋቋም አቃተን "  ያሉ የሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ሰራተኞች የሚከፈለን ገንዘብ ከቤት ኪራይ የማያልፍ በመሆኑ በረሀብ እየተሰቃየን ነው በማለት ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰጥተዋል።

የረከሰ ቤት ፍለጋ ከከተማ ወጣ ያሉ ሰፈሮች በመምረጥ ሶስት አራት ሆነዉ እንደሚከራዩና ጠዋት አንድ ሰአት ለመድረስ ከአስራ ሁለት ሰአት በፊት ተነስተዉ ያውም በባዶ ሆድና በእግር እንደሚመጡ የሚናገሩት ሰራተኞቹ " አሁን ግን ኑሮ ጣሪያ በመንካቱ በዚህ መልክ እንኳን መቀጠል አልቻልንም " ብለዋል።

" ምንም እንኳን የምሳ ድጋፍ ቢደረግልንም በአንድ ከተማ በአንድ የኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ያለዉ ልዩነት ያሳዝናል " በማለት በፓርኩ ውስጥ እንኳን ልዩነት መኖሩን ይገልጻሉ።

አንዳንድ ሼዶች የትራንስፖርት አገልግሎትን ጨምሮ የትርፍ ሰአት ስራ የሚያመቻቹ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ ከአንድ ሽህ ብር ደሞዝ ውጭ ምንም ትርፍ ነገር አይሰጡም።

" በዚህም ኑሮን መግፋት ተራራ ሆኖብናል " በማለት ያሉበትን የስቃይ ህይወት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

ሰራተኞቹ " በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አይደለም የቤት ኪራይ ከፍለንና የምግብ ወጭ ሸፍነን ለመኖር ይቅርና ሰርተዉ ይረዱናል ብለዉ በማሰብ ወደላኩን  ቤተሰቦቻችን ለመመለስ እንኳን አስቸጋሪ ሆኖብናል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን የሰራተኞች እሮሮ ይዞ ምላሽ ለማግኘት የሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክን ደጋግሞ ቢያናንኳኳም ለጊዜዉ ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።

ይሁንና በቅርቡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚው አቶ ዘመን ጁነዲን " የሰራተኛውን ምቹ ከባቢ መፍጠር የኛም ፕራይወሪቲ ነው " ብለው ነበር።

አሁን ላይ ከሚመለከታቸዉ አካላት በተለይም ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር እየተነጋገርሩ መሆኑን የገለጹት አቶ ዘመን ከክፍያ በተጨማሪ ትራንስፖርት ምግብና መሰል ድጎማዎች እያቀረቡ መሆኑን አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

" ኑሮን መቋቋም አቃተን ! " - ሰራተኞች

በተለይ በተለይ አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነታቸውን ያደረጉና ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ በተለያዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ኑሮን መቋቋም ፈተና እንደሆነባቸው ገልጸዋል።

ቃላቸውን ከሰጡት ውስጥ የልጆች እናት መሆናቸውን የገለጹ አንዲት እናት " መሃል ከተማ ያለውን የማይቀመስ የቤት ኪራይ ሽሽት ከከተማ ጥግ ብገባም በየጊዜው በእያንዳንዱ ነገር ላይ በሚታየው ጭማሪ ኑሮን መቋቋም አልቻልኩም " ብለዋል።

" እኔ የዛሬ አመት ይከፈለኝ የነበረ ደመወዝ ዛሬም እዛው ነው ትምህርት ቤት፣ የምግብ ግብዓት፣ አልባሳት፣ ትራንስፖርት ሌሎችም ነገሮች ጨምረዋል ፤ ነገር ሁሉ ነው ግራ ያጋባኝ " ሲሉ በሃዘን ስሜት ያሉበትን ሁኔታ ገልጸዋል።

ሌላኛዋ ወጣት በአንድ የግል ድርጅት ውስጥ ተቀጥራ የምትሰራ ፥ " ከተመረቅኩ ይኸው 5 ዓመቴ ነው ፤ ደህና ደመወዝ የለኝም። የምሰራው ቀን ሙሉ ነው ደመወዜ እዛው ሆኖ ያልጨመረ ነገር የለም " ብላለች።

" ቤት ኪራይ ብቻዬን መክፈል ስለማልችል ከጓደኛዬ ጋር ነው የምኖረው ፤ እንደዛም ሆኖ የወር ጊቢዬን ምኑን ከምን እንደማደረገው አላውቅም ይኸው ልክ እንደ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ አንዳንዴ ቤተሰቦቼ ገንዘብ ይልኩልኛል ፤ ሁኔታዎች እንዲህ ከሆኑ እዛው ቤተሰቤ ጋር ሄጅ ሻይ ቡናም ቢሆን እየሰራው ብኖር ይሻለኛል " ስትል ተናግራለች።

ሌላ ቃላቸውን የሰጡ አንድ አባት ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየአገልግሎቱ ላይ የሚታዩት ጭማሪዎች እሳቸውና ሌሎችም ሰራተኛ ዜጎች ቼይ ከፍተኛ ጫና እንደሚያሳድር ገልጸዋል።

" አንዳንድ የመንግሥት ተቋማት ሳይቀሩ ለአገልግሎት የሚያስከፍሉትን ጭማሪ አድርገዋል ፤ ትራንስፖርት ዋጋው ጨምሯል እኔም ሆንኩኝ ሌላው ሰራተኛ ወርሃዊ ደመወዙ እዚህ ግባ የማይባል ነው ፤ ታዲያ ኑሮ የሚኖረው  ፤ ልጆችን ማሳደግ የሚቻለው እንዴት ነው ? " ሰሉ ጠይቀዋል።

አዲስ አበባ ከተማ በርካታ ዜጎች የሚኖሩባት ሲሆን የቤት ኪራይ ዋጋ የማይቀመስባት በመሆኑ በርካቶች ከሚሰሩበት ርቀው ከከተማ ዳር ዳር ተከራይተው ለመኖር ይገደዳሉ።

በርካቶች ጥዋት ማታ ለፍተው ተንከራተው የሚያገኙት ገቢም እዚህ ግባ የማይባል ፤ ያሰቡትን ለማሳካት ይቅርና ኑሮን ለመግፋት የማያስችል ነው።

በተለይ ወርሃዊ ደመወዝ የሚያገኙ ዜጎች በኑሮ ውድነቱ እጅግ በጣም ነው የሚፈተኑት።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ወጣቶች በክልል ከተሞች ያለው ብሔር እየመረጡ ፣ በትውውቅ በሙስና ሰዎችን ስራ መቅጠር ፣  አስተማማኝ የሆነ ሰላምና ደህንነት ሁኔታ አለመኖር ፣ ብዙ ድርጅት እና ተቋማት አለመኖር ፣ የሰፋ የስራ እድል አለመኖር ፣ በአንዳንድ ከተሞችም ያለውን እንቅስቃሴ እጅጉን መዳከም ሳቢያ በአንጻራዊነት አዲስ አበባን ለኑሮና ስራ እንዲመርጧት እንዳደረጋቸው ጠቁመዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

" የምንሰራው ስራና የሚከፈለን ወርሃዊ ደመወዝ አይመጣጠንም ፤ ድካማችንን የሚመጥን ክፍያ አናገኝም " - ሰራተኞች

በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራው ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ድርጅት አንዱ በሆነ መስፍን ኢንዳትሪያል ኢንጅነሪነንግ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የመብት ጥያቄ እንዳላቸው ገለጹ።

ሰራተኞች ዛሬ ስራ በማቆም ወደ ትእምት ( ትግራይ መልሶ ግንባታ) ዋና ቢሮ በመጓዝ " የመብት ጥያቂያችን ይመለስ " ብለዋል።

ብዛታቸው ከ150 በላይ የሆኑ ሰራተኞቹ ፦

➡️ የሚሰሩት ስራና የሚከፈላቸው ወርሃዊ ደመወዝ እንደማይመጣጠን፤

➡️ በድርጅቱ በቀን አስከ 20 ሰዓታት የሚሰሩ ሰራተኞች ቢኖሩም የሚያከፈላቸው ከፍያ እጅግ አነስተኛ መሆኑ፤

➡️ ደርጅቱ አትራፊ ቢሆንም ለሰራተኞቹ የሚከፍለው ደመወዝ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ፤

➡️ ከጥቅማጥቅም ፣ ያልተከፈለ ውዙፍ ደመወዝና የሰራተኛ ቅጥር ጋር የተያየዘ ጥያቄ እንዳላቸው ገልጸዋል።

" ለረጅም ጊዜ የመብት ጥያቄያችንን የሚመጥን አስቸኳይ መልስና መፍትሄ እንፈልጋለን " ብለዋል።

ለሰራተኞቹ ዘግይተው መልስ የሰጡት የትእምት የሰው ሃይል አስተዳደር ተኽለወኒ ገ/መድህን ፥ " ቀጣዩ አርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም ከትእምት ኢንደውመንት አመራሮች በጋራ በመሆን ጥያቄያችሁ እናደምጣለን " በማለት ሸኝተዋቸዋል።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪነንግ በብረታ ብረትና ሞደፊክ ስራዎች የተሰማራ ከትእምት (EFORT) ግዙፍ ካምፓኒዎች አንዱ ነው።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM