TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች ፦

- ላለፉት 76 ቀናት በሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ ተጥሎ የነበረው እንቅስቃሴ የማድረግ ገደብ ከዛሬ ጀምሮ #ተነስቷል

- በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሆኑ የተገለፀላቸው ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን እስካሁን ከፅኑ ህሙማን ክፍል አልወጡም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁለተኛ ምሽታቸውን በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እያሳለፉ ነው።

- ቱርክ ውስጥ በአንድ ቀን 3,892 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ34,000 በልጧል።

- በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ10,000 በልጧል። ፈረንሳይ ከአሜሪካ፣ ስፔንና ጣልያን ቀጥላ ከ10,000 በላይ ሞት የተመዘገበባት አራተኛ ሀገር ሆናለች።

- በሩሲያ በአንድ ቀን ብቻ 1,154 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰምቷል። በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 7,497 ደርሷል።

- በህንድ፣ ጉጅራት በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠ የ14 ወር ህፃን ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል።

- በዩናይትድ ኪንግደም በ24 ሰዓት ውስጥ 4,344 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው 3,634 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ1.4 ሚሊዮን በልጧል። ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ከ300,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል። ከ81,000 በላይ ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ  የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል። ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል። በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን…
ቅዱስ ሲኖዶስ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ?

ካሁን ቀደም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበትና በመቀጠል አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮምያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው 10ሩ የስምምነት ነጥቦች መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል ፦

- የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሪነት ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ በመምጣት እስካሁን ድረስ በበዓታቸው ጸንተው የቆዩት 3ቱም የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት ማለትም ፦
👉 ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣
👉 ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ
👉 ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ላይ አስቀድሞ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ #ተነስቷል፡፡

- ውግዘቱ የተነሣላቸው 3ቱም ሊቃነ ጳጳሳት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀነ 2015ዓ.ም. ጀምሮ በቀድሞ የሊቀ ጳጳስነት ማዕረጋቸውና ስማቸው ማለትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ሊቀጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዜናማርቆስ ሊቀጳጳስ ተብለው እንዲጠሩና አስቀድሞ ተመድበው ይሰሩበት በነበረው የሥራ ኃላፊነታቸው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በተደረገው ውይይት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ጥሪውን ተቀብለው ለስምምነቱ ተገዥ በመሆን በጽሑፍ ጥያቄያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ያቀረቡት 20ዎቹ የቀድሞ መነኮሳት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ የተላለፈው ውግዘት ከዛሬ መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ #ተነስቷል፡፡ ቀሪዎቹ 5ቱ ባለው ጊዜ ተጠቅመው ወደቤተ ክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ ያሳሰበ ሲሆን ውግዘቱን በሚመለከት በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ታይቶ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ውግዘቱ የተነሣላቸው 20ዎቹም የቀድሞ መነኮሳት አስቀድሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከዲቁና እስከ ቁምስና ባለው ማዕረገ ክህነታቸው እንዲያገለግሉ እና በምንኩስና ስማቸውም እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

- ሃያዎቹ (20ዎቹ) የቀድሞ መነኮሳት የሥራ ምደባን በተመለከተ በተደረሰው ስምምነት መሠረት በቀድሞው የሥራ መደብ ደረጃቸው እንዲመደቡ ቅዱስ ሲኖዶስ በመወሰን ዝርዝር ጉዳዩ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ አዟል።

- ምንም እንኳን አስቀድሞ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በተደረገው ውይይትና ስምምነት መሠረት የታሰሩት ግለሰቦች በሙሉ እንደሚፈቱ ቃል የተገባ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በርካታ ሰዎች በእስር ላይ የሚገኙ ስለሆነ መንግስት አስቀድሞ በገባው ቃል መሠረት ሁሉንም እስረኞች እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ በጥብቅ አሳስቧል።

- በተከሰተው ችግር ከሀገረ ስብከት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ላይ በኃላፊነት ተመድበው ሲሰሩ ቆይተው በችግሩ ምክንያት ተፈናቅለው የቆዩት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሀገረ ስብከትና የወረዳ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት በምድብ ሥራቸው ላይ እንዲቀጥሉ ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡

(#ሙሉ ውሳኔው እንዲሁም መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈#የሰራተኞችድምጽ " ቢብስብን ነው ወደ ህዝብ ፊትና ሚዲያ የመጣነው " - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በሚሰሩበት ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ በፋይናንስ ስርዓት መማረራቸውን የገለጹ የአካዳሚክ ጉዳይ አካላት፣ መምህራንና ሌሎችም ችግሮች ካልተፈቱ ስራ ሊያቆሙ እንደሚችሉ አሳስቡ። ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በኦዲት ግኝት እንዲሁም በሌሎችም ችግሮች በስፋት ስሙ መነሳቱ የሚዘነጋ አይደለም። " ከፍተኛ የሆነና…
#Update #GambellaUniversity

“ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ' ይነሳልን ' ያሉት ሰው #ተነስቷል ” - የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ ዩኒቨርሲቲው ሪፎርም ቢያደርግም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻው የፋይናንስ ጉዳይ እንዳልተደረገ፣ በዚህም ችግሩ በተለይ ከክፍያና ከስልጠና ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ፒቲሽን አሰባስበው ዩኒቨርሲቲውን ቢጠይቁም ምላሽ እንዳልተሰጣቸው ገልጸው፤ “ በቢብስብን ነው ወደ ህዝብና ፊትና ሚዲያ የመጣነው ” ብለው የነበረ ሲሆን፤ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ለቅሬታው ምላሽ ተሰጥቶ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲውን ጠይቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ደሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) ምን ማላሽ ሰጡ ?

“ ከዚህ በፊትም በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ቅሬታውን አቅርበው ቅሬታውን አክኖሌጅ አድርገን በአሰራር ለውጥ ለማምጣት ከተወሰኑ መምህራን ጋር ውይይት አድርገናል፡፡

እንደተባለው በዩኒቨርደሲቲ ደረጃ ሪፎርም ተደርጓል፡፡ ያ ማለት ከዚህ በፊት የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ካለው አፈጻጸም አንጻር መዘጋት አለበት ተብሎ፤ ከሚዘጋ ደግሞ ሪሮርም መደረግ አለበት ተብሎ ከፍተኛ የአመራር ለውጥ ተደርጓል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል አለበት የሚል እምነት አለን እኛም፡፡ ዩኒቨርሲቲ ያለተማሪዎችና ያለመምህራን የሚሰራው ሥራ የለም፡፡

ስለዚህ መምህራን የጠየቋቸውን ጥያቄዎች ላለመመለስ ሳይሆን ወደ ሚዲያም የወጡበት 'በ72 ሰዓታት ውስጥ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ እርምጃ ካልተወሰደ ከዩኒቨርሲቲ በላይ ላሉት አካላት ሪፖርት እናደርጋለን ' ብለው ነው፡፡ ያንን ደግሞ እኛ መከልክል አንችልም፡፡

ፋይናንስ ውስጥ ያሉ ሠራተኞች አገልግሎት አሰጣጣቸውን በዬጊዜው እንዲያሻሽሉ አድርገናል፡፡

ሪፎርም አልተደረገም ማለት አልችልም ምክንያቱም እኛ ሥራ ስንጀምር የነበረውን ዳይሬክተር (ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ክፍተት አለበት የተባለውን ሰው) አንስተናል ከዛም በፊት፡፡

አሁን እዛው ክፍል የነበረ በቡድን ደረጃ ያለውን በጊዜያዊነት ነው ያስቀመጥነው፡፡ እሱንም ደግሞ ለማንሳት መጀመሪያም ፒቲሽን አቅርበው ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ፒቲሽን በሚያቀርቡበት ጊዜ ያለውን አብረን ተነጋግረናል እንደምናስተካክል፡፡

ትልቁ ችግር በቂ ፋይናንስ ባለመኖሩ ሁሉንም ጥያቄ በአንዴ መመለስ አይቻልም፡፡ ብዙ ሪፎርም ያደረግንባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ 'በ72 ሰዓታት ውስጥ' የሚባለው ግን ፋይናንስ ላይ የሚሰራ ሰው ሰነድ ማስረከብ አለበት፡፡ የኮሚዩኒኬሽን ክፍተት ነበረ ይህንን ሲያስተባብሩ ከነበሩ መምህራንና በከፍተኛ ማኔጅመንት።

የ10 ዓመት እድሜ ታሪክ ያለው ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ እንዳሉትም ላብራቶሪ በትክክል ሰርቪስ አልተደረገም፡፡ ግን መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየተሰራ ነው ያለው አሁን፡፡ ለመምህራን እውነት ለመናገር ትልቅ አክብተሮት አለን፡፡

የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ስለሚፈልጉ፣ ስለጓጉ ነው እንጂ፡፡ ይህም መብታቸው ነው፡፡ ለምን ይህንን አደረጉ አንልም፡፡ ግን መሻሻል እንዳለበት ከእነርሱ ጋርም ተነጋገረናል፡፡ ግልጽ ነው፡፡ እነርሱ ፒቲሽን አመጡም አላመጡም ያው ሪፎርሙ ይቀጥላል፡፡

ችግሩ ወዲያው የማይቀረፈው በኢትዮጵያ ደረጃ አዲስ የሠራተኛ ምደባ ተደርጓል፡፡ አዲስ ቅጥር ደግሞ በሲቪል ሰርቪስ አይፈቀድም፡፡ ቅጥር ተፈቅዶ ገና በፕሮሲጀር የሚከድበት ነው፡፡ የሰለጠነ ባለሙያ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማግኘት ይከብዳል፡፡ ጠይቀናል፤ ሊሳካ አልቻለም፡፡

' በ72 ሰዓት ምላሽ ስጡን ' የሚለውም ቢያልፍ እኛ ወስነን ስለነበረ አዲስ ዳይሬክተር ተመድቦ ይነሳልን ያሉት ሰው ከዛ
ተነስቷል፡፡ ባይሉም እኛ እንደ ከፍተኛ አመራር ይህንን ወስነናል፡፡ መወሰናችንን ደግሞ አስቀድመን ነግረናቸዋል፡፡ አሁን ያለው እውነታ ይሄ ነው፡፡

በቂ በጀት የለም፡፡ ፍላጎትና በጀት ስለማይመጣጠን ቅድሚያ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ የ2015 ዓ/ም ያልተከፈሉ እዳዎች እንደተባለው የ12ኛ፤ የዊኬንድ፤ የኦቨርሎድ ክፍዎች እየተከባለሉ መጥተው 2016 ዓ/ም ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድረዋል፡፡

ለመምህራን ስልጠና አለመስጠት፣ ወርክሾፕ ላይ ላብራቶሪ አለማሟላት የተፈጠረው የበጀት እጥረት በመኖሩ ነው፡፡ እጥረቱ ደግሞ እንዲፈታ ከፌደራል ገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተበነጋርን ነው፡፡

በጀትና የምናቅፀደው እቅድ አለመጣጣም ነው፡፡ አንዱ ያነሱት ቅሬታ 'እዛ ያለው ኃላፊ ይነሳልን' የሚል ነው ተነስቶላቸዋል፡፡ ይህንንም ኮሚዩኒኬት አድርገናል፡፡ መምህራንም አሁን ሥራዎችን እየሰሩ ነው፡፡ እንደተባለው ግን በ72 ሰዓት የተባለውን አንደርስታንድ መደራረግ ያስፈልግ ነበር፡፡

ይህንን ፒቲሽን ከተፈራረሙ በኋላ መምህራንን ለማነጋር እየሄድንብት ያለውን ፕሮሲጀር ለማስረዳት ቀጠሮ ይዘንላቸው እኔ ሌላ ስብሰባ ነበረኝ፤ የአስተዳደርና የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲያገኟቸው ወደ አዳራሽ ሲሄዱ አንድም ሰው እዛ አልተገኘም፡፡

ነገር ግን አሁን አዲሱ ሪፎርም ላይ ባለው አመራር 24 ሰዓት በራችን ክፍት ነው፡፡

ከእነርሱ የምንደብቀው ነገር የለም አንድ ላይ ነው የምንሰራው፡፡ ቀጠሮም ይዘንላቸው እዛ ላይ አልተገኙም ” ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ዩኒቨርሲቲው የኦዲት ክፍተት እንደነበረበት መረጃዎች መውጣታቸው ይታወሳል፤ ለመሆኑ እርምጃ ተወስዷል ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፤ የማስተካከያ እርምጃዎች እንደተወሰዱ ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

“ ኮመንት የተደረጉት የፌደራሉ ኦዲት መስሪያ ቤት የአመቱን የኦዲት ሪፖርት ይጠይቃል፡፡ ግኝቶቹ ላይ በቂ ማብራሪያ ወይንም ግብረ መልስ ተሰጥቷል ” ነው ያሉት፡፡

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia