TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፌልትማን ሀሙስ ኢትዮጵያ ይመጣሉ። የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማ ሀሙስ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ተነግሯል። ፌልትማን ኢትዮጵያ የሚመጡት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሰላም ድርድር ጉዳይ ለመነጋገር እንደሆነ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ መናገራቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል። አምባሳደር ፌልትማን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከከፍተኛ…
#EXCLUSIVE

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው ይለቃሉ ተብሏል።

ነገ ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁት በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከሃላፊነታቸው ሊለቁ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።

ሮይተርስ አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ከ9 ወራት የስልጣን ቆይታ በኋላ በዚህ ወር ከኃላፊነታቸው እንደሚለቁ መስማቱን ገልጿል።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።

አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን ይተኳቸዋል ተብለው የሚጠበቁት #በቱርክ የአሜሪካ አምባሳደርነት ጊዜያቸውን የጨረሱት ዴቪድ ሰተርፊልድ መሆናቸውን ሮይተርስ ለጉዳዩ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች መስማቱን ገልጿል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#IGAD

" ... ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት " - ኢጋድ

የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዛሬ ኡጋንዳ ኢንቴቤ ውስጥ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባውን አድርጎ ነበር።

ይህ አስቸኳይ ስብሰባ የኢጋድ መስራቿ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኤርትራ እና የሱዳን መንግሥት ተወካዮች / መሪዎች ባልተገኙበት የተካሄደ ነው።

ስብሰባው ትኩረት ያደረገው ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ግንኙነት ጉዳይ እንዲሁም ስለ ሱዳን ጦርነት ነው።

ከኢጋድ አባል ሀገራት የትኞቹ መሪዎች ተገኙ ?

🇩🇯 የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢማኤል ኦማር ጌሌህ (ስብሰባውን የመሩት እሳቸው ናቸው/ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ናቸው)
🇰🇪 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ
🇸🇴 የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇺🇬 የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ተገኝተው ነበር።

ሌሎችስ እነማን ተገኙ ?

- የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የሱዳን የግል መልዕክተኛ ራምታኔ ላምራ፣
- የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ አልኩራጂ
- የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች / #UAE የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሻሂን አል ማራርት
- የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔታ ዌበር፤
- #የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፤
- የአረብ ሀገራት ሊግ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪ
- የኢጋድ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ አብዲ ዋሬ
- የደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ እና የሱዳን የሰላም ሂደት የኢጋድ ተወካይ አምባሳደር እስማኤል ዋይስ
- የኢጋድ የቀይ ባህር፣ የኤደን ባህረ ሰላጤ እና የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሀመድ አሊ ጉዮ
- #በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቱትኩ ኢናም
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ቺክ ኮንዴ ተገኝተው ነበር።

ኢጋድ ከስብሰባው በኃላ ባወጣው መግለጫ ምን አለ ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግኙነት መካከል የተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

በዋነኛ መርህነት የሶማሊያ ሉዓላዊነት ፣ አድነት እና የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል ሲል አረጋግጧል። ማንኛውም ተሳትፎ ይህንን መርህ ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል። ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት ብሏል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በማርገብ በምትኩ ገንቢ የሆነ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ስብሰባው ላይ ለምን አልተገኘችም ?

ኢትዮጵያ ከዛሬው የአስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል " በተደራራቢ መርሃ ግብር " ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት እንዳማትችል ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር እና ኢጋድ በድብዳቤ አሳውቃለች።

ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘ መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና የተቀመጠውም ጊዜ አጭር በመሆኑ በስብሰባው ላይ መገኘት እንደሚያስቸግራት በዚሁ ደብዳቤ አሳውቃ ነበር።

ነገር ግን " ኢጋድ በሚመራበት ደንብ መሰረት " በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃቸዋለች።

(ሙሉ የኢጋድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia