TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አምጥቷል። በግላስኮ ዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ በአትሌት ሰለሞን ባረጋ አማካኝነት የነሃስ ሜዳሊያ ማግኘት ችላለች። ጌትነት ዋለ 4ኛ ወጥቷል። ኢትዮጵያ በዚህ ርቀት በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ላይ የወርቅ ሜዳሊያ ሳታሸንፍ ስትቀር ከ3 ተከታታይ ውድድሮች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ሰለሞን ባረጋ…
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ሆና አጠናቀቀች።

በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 1ኛ ከዓለም ደግሞ 5 በመሆን አጠናቃለች።

ከማርች 1-3/2024 በእንግሊዝ ግላስጎ ሲካሄድ የ19ኛው የዓለም የቤት ዉስጥ ሲካሄድ ነበር። በሻምፒዮናው ከ130 በላይ አገሮች የተውጣጡ ከ650 በላይ አትሌቶቸ ተሳትፈዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በ800 ሜትር፣ በ1500 ሜትር እና በ3000 ሜትር በሴትና በወንድ  በአጠቃላይ በ8 ሴቶች እና በ5 ወንዶች በድምሩ በ13 አትሌቶች ተሳትፋለች።

በዚህም #በሴቶች 800 ሜትር ፅጌ ዱጉማ እና በሴቶች 1500 ሜትር ፍሬወይኒ ሀይሉ #የወርቅ፣ በሴቶች 3000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋይ የብር እንዲሁም #በወንዶች 3000 ሜትር ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል።

ይህን ተከትሎ ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ አንድ ነሀስ በአንድ ብር በአጠቃላይ በአራት ሜዳሊያዎች በሜዳልያ ሰንጠረዡ   ከአፍሪካ 1ኛ  ከዓለም 5ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሳለች።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

@tikvahethiopia