TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ራስ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጁ ለአመታት ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 271 የህክምና ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙዔል ክፍሌን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።

ከተመራቂዎች መካከል 158 ወንዶች ሲሆኑ 113 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
- በህክምና ትምህርት ዶክትሬት ዲግሪ 240፣
- በጥርስ ህክምና ዶክትሬት ዲግሪ 9
- በ 'ቢኤስሲ' አኔስቴዥያን ባችለር ዲግሪ 22 ተማሪዎችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎች መካከል 198 የሚሆኑት በማዕረግ፣ በከፍተኛ ማዕረግ እና በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ናቸው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ተማሪዎችን አሰተምሮ ሲያስመርቅ የዛሬው ለ52ኛ ጊዜ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update አዲስ አበባ በአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የሀገራት መሪዎችን እየተቀበለች ትገኛለች። እስካሁን ድረስ የየትኞች ሀገራት መሪዎች ገቡ ? 🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት 🇨🇮 የኮትዲቯር ም/ፕሬዜዳንት ቲሞኮ ሚዬሊ ኮኔ 🇰🇲 የኮሞሮስ ፕሬዜዳንት አዛሊ ኡሱማኒ 🇳🇬 የናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ቦላ አሕመድ ቲኒቡ 🇸🇱 የሴራሊዮን ም/ፕሬዜዳንት  መሀመድ ዡሌ ዣሎህ…
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ ይጀምራል።

በአሁን ሰዓት ጉባኤው በሚካሄድበት " ማንዴላ አዳራሽ " መሪዎች እና ተሳታፊዎች በመግባት ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል።

በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች መሪዎች የመክፈቻ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
መንትዮቹ👏

ዛሬ ራዝ ገዙ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 271 የህክምና ተማሪዎቹን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ  198 የሚሆኑት በማዕረግ፣ በከፍተኛ ማዕረግ እና በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ደግሞ መንትዮቹ  ዶ/ር ቸርነት ተስፋሁን እና ዶ/ር ብሩክ ተስፋሁን በከፍተኛ ማዕረግ በህክምና ዶክትሬት ተመርቀዋል።

#AAU

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🥇3.87 GPA👏

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው እለት ካስመረቃቸው ሴት ተማሪዎች መካከል ዶ/ር ረድኤት ጌቱ ከበደ በህክምና ዶክትሬት 3.87 GPA በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆናለች።

#AAU

@tikvahethiopia
««« ሽልማት የሚያስገኝ ቀላል ጥያቄ »»»

በምስሉ ላይ የተመላከቱትን ቁጥሮች በትክክል ለመለሱ እና የቁጥሮቹን ምንነት ለነገሩን ሶስት ተከታዮቻችን ስጦታ የምናበረክት ይሆናል፡፡

ምላሽ ኤዲት ማድረግ ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፣ ከሶስት በላይ መላሾች በዕጣ የሚለዩ ይሆናል፡፡

በሚቀርብዎ አማራጮች ያግኙን፡ https://bit.ly/3TkrrXD

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

#GlobalBankEthiopia #OurSharedSuccess #GBE #questionandAnswer #BankinEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ ይጀምራል። በአሁን ሰዓት ጉባኤው በሚካሄድበት " ማንዴላ አዳራሽ " መሪዎች እና ተሳታፊዎች በመግባት ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል። በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች መሪዎች የመክፈቻ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። @tikvahethiopia
" የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም " - መንግሥት

37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ " ወደ ስብሰባው እንዳልገባ የመከልከል ሙከራ ተደርጎብኛል " የሚል ክስ አሰምተዋል።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ከስብሰባው መክፈቻ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ፕሬዜዳንቱ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በዝግ በሚደረገው ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ በምሞክርበት ጊዜ የኢትዮያ የፀጥታ ኃይሎች ካረፍኩበት ሆቴል እንዳልወጣ መንገድ ዘግተው ከልክለውኛል።

- በሌላ ፕሬዝዳንት መኪና ከሆቴል በመውጣት የስብሰባው ስፍራ ብደርስም፤ የፀጥታ አካት እንዳንገባ ክልከላ አድርገውብን ነበር።

በኋላ ላይ ግን ፕሬዝዳነቱ ወደ ስብሰባው መግባታቸው እና በስብሰባው መክፈቻ እንዲሁም የቤተሰብ ፎቶ ላይም ታይተዋል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ላይ በሰጠው መግለጫው ፤ " የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት እና ልኡካቸው ወደ 2024 የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ እንዳይገቡ ያደረገውን ሙከራ የሶማሊያ ፌደራላዊ ሪፐብሊክ መንግስ በጽኑ ያወግዛል” ብሏል።

" የኢትዮጵያ መንግስት ድርጊት የዲፕሎማሲ እና ዓለም አቀፍ ደንብን የሚጥስ ነው ፤ የአፍሪካ ኅብረትን የቆየ ባህል የሚቃረን በመሆኑም ህብረቱ ጉዳዩን በገለልተኛ ሆኖ እንደሚረምር " ሲል ጠይቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ምን ምላሽ ሰጠ ?

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፦

- የኢትዮጵያ መንግሥት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ለመጡ ሁሉም ሀገራትና መንግስታት መሪዎች ያደረገውን የክብር አቀባበል ለሶማሊያ ፕሬዚዳንት አድርጓል።

- እንደ አስተናጋጅ ሀገር ኢትዮጵያ የሁሉንም ሀገራትና መንግስታት መሪዎችን በቆይታው ደህንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት። ነገር ግን የሶማሊያ ፕሬዝዳት ልኡካን በመንግሥት የተመደቡላቸውን የፀጥታ አካላት አንቀበልም ብለዋል።

- ከዚህ በላይ ግን የሶማሊያ ልዑክ የደህንነት አባላት የጦር መሳሪያ ታጥቀው ወደ አፍሪካ ኅብረት ለመግባት ሲሞክሩ በኅብረቱ የፀጥታ አካላት ተከልክለዋል።

- የኢትዮጵያ መንግሥት የሶማልያው ፕሬዝዳንት እና የልኡካቸውን ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር በስብሰባው ላይ እንዳይገኙ አላደናቀፈም ፤ ወደ ኅብረቱ ቅጥር ጊቢ እንዳይገቡም አልከለከለም።

- ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ቁርጠኛ አቋም አላት።

Credit : AL AIN NEWS (Amh)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ እና አማራ አዋሳኝ ስፍራ ምን ተፈጠረ ? በትግራይ ክልል እና በአማራ ክልል የራያ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች በትጥቅ የተደገፈ ግጭት እንደነበረ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመስማት ችሏል። የካቲት 6 / 2016 ዓ.ም የተቀሰቀሰው መጠነኛ ነው የተባለው ግጭት በሀገር መከላከያ ሰራዊት ጥረት ሊቆም እንደቻለ ነው የተነገረው። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ለመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ…
" ችግሩ በሰላማዊ መንገድ የፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲፈታ ፍላጎታችን ነው " - አቶ ኃይሉ አበራ

ከሰሞኑን #በአማራ እና #በትግራይ ክልሎች መካከል ተቀሰቀሰ የተባለውን ለአጭር ጊዜ የቆየ የተኩስ ልውውጥ በተመለከተ በአማራ ክልል በኩል ያለውን ሁኔታ አስመልክቶ በአሁን ሰዓት በአማራ ክልል ስር እየተዳደረ ያለው የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የሆኑት አቶ ኃይሉ አበራ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አቶ ኃይሉ አበራ ምን አሉ ?

- በባላ አቅጣጫ ማሮ በሚባል ቦታ ከእኛ ሚሊሻ ጋ ገጠሙ። ተመትተው ተመልሰዋል አሁን ላይ ቦታውን ለቀዋል።

- ወደ ሁለት ቀበሌዎች ወረራ ለማድርግ ሙከራ አድርገው ነበር። በመጀመሪያ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሰላም ጥሪ ነበር እየተላለፈ የከረመው፣ አሁን ግን እሳቢያቸው የነበረው በወረራ ቦታውን ይዘው ‘እንደራደራለን’ አይነት፣ በተፈናቃይ ስም ግጭት መፍጠር ነው።

* የጉዳት መጠንን በተመለከተ ፦ " እኛ ጋር የደረሰ ጉዳት የለም። እነሱ ግን ሊያጠቃ የመጣ ምንጊዜም ተመትቶ ነው የሚሄደው። የተወሰኑት ተመተው ሂደዋል። " ብለዋል።

- አላማጣን፣ ኮረምን ለመውረር እንዲሁ በጡሩባ እና በጩኽት የሚለቅ ህዝብ መስሏቸው ነበር። ሕዝቡ ማዕበል ሆኖ ነው የወጣው ከዚህ በኋላ የሰላሙን ጥሪ የማይቀበሉት እና ሰላሙን የማይፈልጉት ከሆነ አሁን እኛ ህዝባዊ አድርገነዋል።

* የመፍትሄ ሀሳብን በተመለከተ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለተነሳው ጥያቄ ፦ " ችግሩ በሰላማዊ መንገድ የፌደራል መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲፈታ ፍላጎታችን ነው። 'አይ የለም ህዝቡ ወደ ሚፈልገው መሆን አይችልም፣ እኔ ብቻ ነኝ የምወስንልህ' የሚል እሳቤ የሚቀሳቀስ ከሆነ እሱ የሚቻል አይደለም። ፋሽኑም ግዜውም አልፎበታል። አሁን ላይ ወደ ኋላ የሚመልስ ኃይል የለም። Already ሁሉም ተደራጅቷአል። " ብለዋል።

- የትግራይ ፖለቲከኞችም ሀይ ሀይ የሚሉትን ዲያስፖራ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል። ' አይ የለም የትግራይ ሉዐላዊ ግዛት ' እያሉ በወረራ የያዙትን ቦታ 'በኃይል እናስመልሳለን' የሚሉ ከሆነ ግን ከዚህ በኋላ የሚኖረው ሕዝባዊ ነው። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ አደጋው የከፋ ነው የሚሆነው። በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ነው ሊፈጠር የሚችለው። ይህንን እንዲያስቡበት ነው የምናስገነዝበው።

- እኛ የማንንም መብት አንጋፋም የትኛውንም ሰው በማንነቱ ምክንያት የምናደርስበት ጉዳት የለም። ሊወርና ሊገድል ኃይል ከመጣ ግን ህዝብን መቆጣጠር አይቻልም። ስለዚህ ነገሮች ከቁጥጥር ውጭ ከመሆናቸው በፊት ቆም ብለው ቢያስቡ ይሻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
የካቲት 9 ቀን 2016 ዓ/ም
አላማጣ

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia