TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ ጠቅለይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር በቢሯቸው መምከር መጀመራቸው ተነግሯል።

ዶ/ር ዐቢይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩትን ስራዎች እና መሻሻሎች ላይ ነው ግምገማ ማካሄድ የጀመሩት።

በዚህ የግምገማ መድረክ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አማራሮች በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናትም ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት " ይህ በፌደራል እና የክልል ኃላፊነት ባላቸው የስራ ተዋንያን የሚደረገው ጠቃሚ ግምገማ በድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ እና በሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ነው። " ብሏል።

በዛሬው መድረክ የህወሓት ሊቀመንበር እና የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በአካል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ።

የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የካቲት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ይመረቃል።

የምረቃ ስነ-ስርዓትን ተከትሎ በዕለቱ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት:-

ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ፣

ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ ፣

ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ፣

ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

➡️ ከሀገር አስተዳደር መብራት (ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

➡️ ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

➡️ ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣

➡️ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ፣

➡️ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፣

➡️ ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

➡️ ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት (የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ) ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች በሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በዋዜማው የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶችና የምረቃ ስነ-ስርዓቱ በሚከናወንበት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪ ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑንም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይለፍ ያላቸው አሽከርካሪዎች ቸርችር ጎዳና ጫፍ የቀድሞ ሜክሲኮ ታክሲ ተራ እና ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ቸርችር ጎዳና ጫፍ መኪናዎቻቸውን መቆም ይችላሉ።

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር በመገንዘብ ታዳሚዎች የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ውጪ ወደ ሙዚየም የሚወስዱ መንገዶች ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለእግረኞች ዝግ ይሆናሉ።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

በአቢሲንያ ባንክ ፀሐይ አትጠልቅም!

24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት በአቢሲንያ የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከላት ያግኙ

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ከቴሌብር አካውንት ወደ ሌላ የቴሌብር ደንበኛ አካዉንት ገንዘብ መላኪያ ታሪፍ ላይ እስከ 80% ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በአዲሱ የታሪፍ ቅናሽ እስከ ብር 5,000 ሲልኩ 0.1% እንዲሁም ከብር 5,001-75,000 ለመላክ 5 ብር ብቻ የአገልግሎት ክፍያ ይፈጽማሉ።

የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ https://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ ወይም *127# ይደውሉ!

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#Mekelle

መቐለ ከተማ  የነዳጅ እጥረት አጋጥሟታል።

ቤንዚን በጥቁር ገበያ እስከ 300 ብር በሊትር እየተሸጠ ነው። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንዳልሆኑ አረጋግጧል።

በነዳጅ መጥፋት ምክንያት በተለይ የባጃጅ ትራንስፓርት ዋጋ ጨምረዋል።

ህዝቡ ለአንድ ሰው ኮንተራት ላጠረው መዳረሻ እስከ ሁለት መቶ ብር እየተጠየቀ በመሆኑ ባለፈው አስከፊ ጦርነት የነበረው ሁኔታ በማስታወስ ምሬቱ እየገለፀ ነው። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረቱ መነሻ ምን እንደሆነ ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። በዚሁ ዙሪያ የሚመለከተው  አካል የሚሰጠን አስቸኳይ የመፍትሄ ሃሳብ ካለ ተከታትለን እናቀርባለን።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር  በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ፤ የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጠል መሆኑ ማስታወቁ ይታወሳል። 

በዚሁ መሰረት ፦

- ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም 

ሆኖ በየካቲት ወር እንደሚቀጥል መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#EHRC የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በአማራ ከልል ምዕራብ ጎጃም ዞን መርዓዊ ከተማ በ20/05/2016 ዓ.ም በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂ ቡድኖች መካከል በነበረ ግጭት ከፍተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚያሳዩ መረጃዎች እንደደረሱት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል። በእዚህ ግጭት ምክንያት በመርዓዊ ከተማ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ እንደነበር…
#USA #ETHIOPIA #MERAWI

በአማራ ክልል መርዓዊ ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን ኢላማ በማድረግ ግድያ የፈጸሙ ላይ ምርመራ ተደርጎ ለፍርድ እንዲቀርቡ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጠየቁ።

አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በኤምባሲው የX ገጽ ላይ ባወጡት መልዕክት በመርዓዊ ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በሚመለከት የወጡ ሪፖርቶች የአሜሪካ መንግሥትን እንደሚያሳስበው ገልጸዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ፣ የክስተቱን አሳሳቢነት ከመግለጻቸው ባሻገር " የግድያውን ፈጻሚዎች ለሕግ ለማቅረብ " ገለልተኛ የሰብዓዊ መብት ተቆጣጣሪዎች ምንም ገደብ ሳይደረግባቸው ወደ ሥፍራው እንዲንቀሳቀሱ እንዲፈቀድላቸው እንዲሁም በግድያው ዙሪያ ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በአገሪቱ ባሉት የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ በሌሎችም ቦታዎች ላይ " በመንግሥት እና ከመንግሥት ውጪ በሆኑ ኃይሎች በተመሳሳይ የመብት ጥሰቶች እና ጥቃቶችን መፈጸማቸውን የሚያመልክቱ በርካታ የሚረብሹ ሪፖርቶች " እየወጡ መሆናቸውንም አምባሳደሩ ጠቅሰዋል።

" ኃይል ሳይሆን ውይይት ብቸኛው አማራጭ ነው"ም ሲሉ አሳውቀዋል። #USEmbassy #BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#SamoaAgreement ከወር በፊት ሀገራችን #ኢትዮጵያን ጨምሮ አጠቃላይ 79 የአፍሪካ እና የካረቢያንና ፓስፊክ ሀገራት / 48 ከአፍሪካ፣ 16 ከካረቢያን፣ 15 ከፓስፊክ / ሳሞአ ላይ አንድ ስምምነት ተፈራርመዋል። የተፈረመው ስምምነት " #የአፍሪካ ፣ #የካረቢያን እና #የፓስፊክ ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ጋር የሚያደርጉት የንግድ እና ኢኮኖሚ ትብብር " የሚል ነው። ስምምነቱ 22…
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫቸው ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የተመለከተ ነው።

ጉባኤው ስምምነቱ ተካተውበታል ያላቸውን ጎጂ ሀሳቦች በዝርዝር አስፍሯል።

ከነዚህም መካከል ፦

- በስምምነቱ አንቀፅ 36.2 ላይ የተጠቀሰው የወሲብና የተዋልዶ ጤናና መብቶች" ("Sexual and Reproductive Health and Rights") የሚለው ሐረግ በቀጥታ ፦
* #ከግብረሰዶም መብቶች፤
* ከፆታ መቀየር፤
* ከውርጃ፤
* ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርትና ግልሙትናን ሕጋዊ ከማድረግ በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ በአውሮፓ ፓርላማና በዓለም የጤና ድርጅት የመረጃ ምንጮች ላይ በግልፅ መቀመጡ፤

- በስምምነቱ የአፍሪካ ፕሮቶኮል አንቀፅ 40.6 ላይ በአህጉሪቱ ለሚገኙ ልጆችና ታዳጊዎች ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት (Comprehensive Sexuality Education) የተባለ እጅግ አደገኛ ኢግብረገባዊና ልቅ የወሲብ ትምህርት እንዲማሩ አስገዳጅ መሆኑ ለዚህም በዩኔስኮ የተዘጋጀውና እጅግ አደገኛ ይዘት እንዳለው የተረጋገጠው መተግበርያ "International Technical Guidance on Sexuality Education” በስም ተጠቅሶ መቀመጡ፤

- የፆታ ትንኮሳን (gender based violence) ማስቀረት በሚል በጣም አሻሚ የሆነ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን ለማስረፅ እንዲረዳው በሰነዱ በበርካታ ክፍሎች ውስጥ " አካታች " (inclusive) በሚሉ ቃላት ተሸፍኖ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ፤

- በበርካታ ሥፍራዎች የተጠቀሰው "Gender" የሚለው ቃል ወንድና ሴት ተብሎ እንደሚተረጎም በስምምነቱ በግልጽ ባለመቀመጡ ይልቁንም በርካታ ጾታዎች እንዳሉ በማስመሰል ሀገራትን የሚያደናግሩባቸው እንደ (sexual orientation እና gender identity)ን የመሳስሉ ግብረሰዶማዊ አስተሳሰቦችን የያዙ ዶክመንቶች በስም ተጠቅሰው በስምምነቱ ውስጥ መካተታቸው፤

- ስምምነቱ የወላጆችን መብት የሚጥስና የኢትዮጵያዊ ቤተሰብ እሴቶችን አደጋ ላይ የሚጥሉ አንቀፆችን የያዘ ስለመሆኑ በሰነዱ ላይ ከተደረገ የኤክስፐርቶች ጥልቅ ጥናት ተረድተናል...  የሚሉት ይገኙበታል።

ጉባኤው በነዚህ እና ሌሎች ጎጂ ምክንያቶች ፦

መንግስት የሳሞአ የንግድና የኢኮኖሚ የአጋርነት ስምምነትን በርካታ ጎጂ ጎኖች እንዳሉት በማመን ከዚህ ስምምነት #ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገልል በማድረግ መንግስታዊ ኃላፊነቱንና አደራውን በተግባር እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል።

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በሥሩ ያሉ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የስምምነት ሰነዱ ውስጥ በዝርዝር የቀረቡትን በተለይም ፦
° ከሰብኣዊ መብቶች፣
° ከወሲባዊና የተዋልዶ ጤናና መብቶች፣
° ሁሉን አቀፍ የወሲብ ትምህርት፤
° አካታችነት እና መሰል በሰነዱ የተካተቱ አንቀጾች ወይም ይዘቶች ከግብረሰዶማዊነትና ጾታን ከመቀየር እንዲሁም ከልቅ ወሲብና ከውርጃ ጋራ በቀጥታ ተያያዥነት ያላቸው ጽንስ ሃሳቦች መሆናቸውን በመረዳት ይህንን እጅግ አደገኛ ስምምነት ባለማጽደቅ ህዝባዊና ታሪካዊ አደራውን እንዲወጣ በአጽንኦት ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ስለ " ሳሞአ ስምምነት " ያዘጋጀው ሰፊ እና ዝርዝር ዘገባ በዚህ ይገኛል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/84172

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደርጓል።

በ15 ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች በቀን በአማካይ እስከ 6 ሺህ ተገልጋዮችን የሚያስተናግደው መ/ቤቱ ከየካቲት 1/2016 አንስቶ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አድርጓል።

በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሻያ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ ፦

- ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ #ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ (በአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ) አገልግሎት ይሰጣል።

👉 እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት የሚቆየው የስራ ሰዓት በሌሎች ቅርንጫፎችም በሂደት እንደሚጀመር ተነግሯል።

- ቅዳሜ ከጥዋት አንስቶ እስከ ቀኑ 11:30 ድረስ (በሁሉም ቅርንጫፍ) #አገልግሎት ይሰጣል።

በአዲሱ የስራ ሰዓት ማሻሻያ አገልግሎቱ " ለምሳ ሰዓት " በሚል የማይቋረጥ ሲሆን በምሳ ሰዓትም አገልግሎት ማግኘት ይቻላል ተብሏል።

ከዚህ ቀደም በዚህ መስሪያ ቤት አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ከጥዋት 3:00 ሰዓት አንስቶ ሲሆን ለምሳ ተብሎ ደግሞ ሰራተኞቹ ወጥተው 8:00 ነበር የሚገቡት።

ቅዳሜ ደግሞ ግማሽ ቀን ነበር የሚሰራው።

ከዛሬ በኃላ በአ/አ ዋናው መ/ቤት እና በድሬዳዋ ቅርንጫፍ ከሰኞ እስከ አርብ ከጥዋት 2:00 ሰዓት እስከ ምሽት 1:00 ሰዓት ፤ ቅዳሜ በሁሉም ቅርንጫፍ ከጥዋት እስከ 11:30 አገልግሎት ይሰጣል።

ዛሬ የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት የስራ ሰዓት ማሻሻያ ባደረገበት ስነስርዓት ላይ የተገኘው ፍትህ ሚኒስቴር ፤ ይህ አሰራር የተገልጋዮችን እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ በመሆኑ ሌሎችም ተቋማት መሰል አሰራር ቢከተሉና ወስራ ቢያስገቡ ሲል ጠይቋል።

@tikvahethiopia