TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ተማሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሁነኛ አካል በአማራ ክልል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚገኙ ተማሪዎች ማክሰኞ ጥር 28 ቀን ከምሽቱ 2፡30 ገደማ ታጣቂዎች በካምፓሱ ውስጥ ተኩስ መክፈታቸውን፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡም ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው፣ የሚመለከተው አካል ሰላም ወዳለበት…
#Update

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፤ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ " ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው፣ ተማሪዎቹ ከግቢው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል " የተባለውን ጉዳይ በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንድ ስማቸውን እንዲገለፅ ላልፈለጉ የዩኒቨርስቲው አካል ጥያቄ አቅርቦ ነበር።

እኚህ የዩኒቨርሲቲው አካል፤ በትላንት በስቲያ ምሽቱ ተኩስ ተማሪ ላይ ያተኮረ / ተማሪ ላይ ታርጌት ያደረገ ጉዳት እንዳልደረሰ ገልጸዋል።

" ተማሪዎች እንጠራ ብለው በተደጋጋሚ ትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀዋል። ትምህርት ሚኒስቴርም ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት ነው ዩንቨርሲቲው ሊጠራ የቻለው " ሲሉ አስታውሰዋል። 

" ዩንቨርሲቲው አሁን ላይ እያስተማረ ነው። ተማሪዎችም ትምህርት ጀምረዋል። በርከት ያሉ ተማሪዎች መጥተዋል። በዚህ መንገድ ደግሞ ተደጋጋሚ የሚፈጠሩ ነገሮች አሉ። ዩንቨርሲቲው አቅም እስከፈቀደለት ድርስ ትምህርቱን ይቀጥላል። በመካከል ተማሪዎች ለራሳቸው የሚፈሩት፣ የሚሰጉት ነገር ካለ አይገደዱም " ሲሉም አክለዋል።

" ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማንም አይገምትም። ማንም ለማንም ዋስትና መሆን አይችልም። By theway በዚህ ጊዜ ላይ ከባድ ነውና ሁሉም ተማሪ ለራሱ ዲሳይድ ማድርግ መቻል አለበት " ያሉት እኚሁ የዩኒቨርሲቲው አካል፤ " ሲመጡም ያንን ተገቢ ግምት ውስጥ ያስገባሉ ተብሎ ነው የሚታሰበው። ተማሪዎች  መማር አለብን ብሎ የሚያስብ ከሆነ ማስቀጠል እስከተቻለ ድረስ ይማራሉ " ብለዋል።

አክለውም " ይህንን ዓመት Withdraw ማድልግ እፈልጋለሁ የሚል (ተማሪ) አይከለከልም። ተማሪ በራሱ አምኖበት የሚያደርገው ስለሆነ በዩኒቨርስቲ በኩልም አይጠየቅም " ያሉ ሲሆን " ሁኔታው ግን እስከመቼ እንደዚህ ይቀጥላል ? የሚለው ነገር እንዲህ ነው ብዬ ማለት አልችልም/አላውቅም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የጸጥታው ሁኔታ አጠቃላይ በአገሪቱም፣ በክልሉ አግሪቬት እያደረገ በሄደ ቁጥር ዩኒቨርሲቲዎች ሴንተር ሊሆኑ ይችላሉ። እከባለፉት ዓመታት ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ካየነው ሁኔታ አንጻር፣ ዩኒቨርስቲዎች የማህበረሰቡ ነፀብራቅ ስለሆኑ እዚያ (ውጭ ላይ) የተፈጠረው ነገር እዚህም (ዩኒቨርሲቲ ውስጥ) ይፈጠራል " ብለዋል።

የሁኔታውን አሳሳቢነት በተመለከተ በሰጡት ቃልም፣ " Risk free የሆነ Environment የለንም። ምንም ስጋት የሌለበት ሁኔታ የለም። አሁን ከሚታዩት ነገሮችም አንጻርም፣ ከዚህ በኋላም ማለቴ ነው ፤ Risk free zone ስለሌለን ተማሪዎች መወሰን አለባቸው " ብለዋል።

ተማሪዎች በበኩላቸው " የዩንቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ውይይት እያደረጉ ነበር " ቢባልም የመፍትሄ ሀሳብ እንዳልተነገራቸው፣ ቢያንስ ሰላም ወዳለበት ካምፓስ እንዲያዘዋውሯቸው ጠይቀዋል።

ይህን ተከትሎም ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አድርጋችሁ ? ሲል ጠይቋል።

" እንኳን እንዲህ አይነት ነገር ተፈጥሮ ሁሌም አስቸኳይ ስብሰባ አለ " ሲሉ ገልጸው፣ " ችግር ተፈጥሮ በጉዳዩ ዙሪያ ሳይወራ አይቀርም። ካምፓስ ተቀይሮ የሚመጣ ለውጥ አለ ወይ? Through time long run ምን ይፈጠራል ? የሚለውን analaysis ሲሰራ ካምፓስ መቀየር ዘላቂ የሆነ Problem solve mechanism ነው ? የሚለው ነገር ላይ ያጠራጥራል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለው፣ " እስከመቼ ድረስ ቀይረህ ትችለዋለህ ? ደግሞስ ካምፓስ ተቀይሮ ምን ያህል ይችላል ? አንድ ካምፓስ ምን ያህል ይችላል ? የሚሉት ጉዳዮች አሉ በዚያው ልክ። ለተማሪዎቹ imidate የሆነ መፍትሄ እየተፈለገ ነው። ግን ዘላቂያዊነቱ ላይ ነው ትንሽ ጥያቄ ያለው " ሲሉ አስረድተዋል።
#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
#CRRSA

የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ፤ በጥር ወር አገልግሎትን በገንዘብ በመሸጥ እንዲሁም ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ኤጀንሲው ፥ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት  ላይ የተሰማራ ህገ-ወጥ ደላላ እና አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ  እንዲሁም ላልተገባ ግለሰብ በገንዘብ አገልግሎት የሰጠ የተቋሙ ሰራተኛ እና ተገልጋዮችን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጉን ነው ገለጸው።

ኤጀንሲው በሰጠን ማብራሪያ ፤ የአቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የስራ ዕድል ፈጠራ ጽ/ቤት #ሰራተኛ የሆነ ተጠርጣሪ 30 ሺህ ብር በመቀበል በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 5 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ እና  የጋብቻ ሰርትፍኬት ማዘጋጀቱ ተደርሶበር በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ፤ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 8 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከጽ/ቤቱ ያልወጣ ሀሰተኛ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የልደት ሰርተፍኬት እና የመሸኛ ማስረጃ /Clearance / በ10 ሺ ብር  ያዘጋጀውን ግለሰብ ከየካ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር በየካ ወረዳ 10  አካባቢ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር አውሎታል።

ኤጀንሲው፤ ከኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደረሰው ጥቆማ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 4 እና አዲስ ከተማ ወረዳ 9 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት ምዝገባ ጽ/ቤት ሰራተኛ የሆኑ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ግለሰቦች የነዋሪነት መታወቂያ እና የልደት ማስረጃ በመስጠታቸው በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዚህ ጥር ወር በኤጀንሲው ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት በተመራው ክትትል እና ኦፕሬሽን ፦
- ሰባት በተቋሙ ስም የተሰሩ ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ ግለሰቦች፣
- ሶስት የተቋሙ ሰራተኞች ፣
- አንድ የሌላ ተቋም ሰራተኛ እና አንድ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተሰማሩ በድምሩ 12 ተጠርጣሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረግ መቻሉን አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፤ " በመዋቅሬ ያለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትል በማድረግ ከሌብነት የፀዳ ተቋም ለመገንባት ጥረት እያደረኩ ነው " ያለ ሲሆን ህብረተሰቡ  በተቋሙ ስም ከሚያጭበረብሩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች እራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።

" በተቋሙ ጥቂት ሰራተኞች የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ተግባራት በቅንነት እና ታማኝነት የሚያገለግሉ ሰራተኞችንም አይወክልም " ብሎ " በህዝብ የሚታመን አገልጋይ ተቋም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ነዋሪው አጋዥ እንዲሆን " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በትግራይ ክልል የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ከሰዓት በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን ታሪካዊውን የ " አል ነጃሺ መስጂድ "ን ጎብኝተዋል። የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ አደም ፤ " ነጃሺ ያለ ኢትዮጵያ ሙስሊም ምንም ነው፤ የሚለማው ታሪኩም የኢትዮጵያ ሙስሊም ነው " ብለዋል። የፌዴራል መጅሊሱ…
#Update

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመካከል የነበራቸውን ችግር #በይቅርታ ከፈቱ በኃላ ግንኙነታቸውን ወደነበረበት መልሰዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችም ወደ ትግራይ ተጉዘው በጦርነት የተጎዳውን የአልነጃሺ መስጂድን ጉብኝተው በጦርነት ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ላሉ  እና በድርቅ ለተጎዳው ህዝብ ድጋፍ ሰጥተው ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

የተደረገው ድጋፍ የጥሬ ገንዘብ፣ የመድሃኒትና የእህል ሲሆን የርክክብ ስነ-ሰርዓቱ ዛሬ በመቐለ ከተማ ተከናውነዋል።

ድጋፉ በዝርዝር ምን ይመስላል ?

1ኛ. እህል 5,700 ኩንታል በቆሎ/እህል ብር 24 ሚልዮን የሚያወጣ።

2ኛ. መድሐኒት 1 ኮንተይነር 40 ፊት መድሐኒት ብር 40,200,000 ብር የሚያወጣ።

3ኛ. ለአልነጃሺ ትራንስፎርመር  3 ሚልዮን ብር

4ኛ. ለሌሎች 1.2 ሚልዮን ብር

ጠቅላላ ብር 67 ነጥብ 2 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለትግራይ ህዝብ መደረጉ ተነግሯል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

ፎቶ፦ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
               
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba #Update በማህበር የተደራጁ የጋራ መኖሪያ ቤት ፈላጊዎች  በወሰን ማስከበር  ምክንያት እንቅፋት  ስላጋጠማቸው ግንባታቸው  መጓተቱ ተገለጿል። ከዚህ ቀደም በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው ዛሬ በቤቶች ልማት አስተዳደር…
" ሙሉ በሙሉ እገዳቸው ተነስቷል ፤ ግንባታቸውን መቀጠል ይችላሉ " - የቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ

በአዲስ አበባ ከተማ የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበረባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነሳ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ ፅጌወይን ካሳ ፤ " የማህበር ቤት ለመገንባት የወሰን ማስከበር ችግር የነበረባቸው መሬቶች ሙሉ በሙሉ እግዳቸው ተነስቷል " ብለዋል።

ማህበራቱም ግንባታቸውን መቀጠል እንደሚችሉ ኃላፊዋ ገልፀዋል።

በ40/60 እና በ20/80 ተመዝጋቢ የነበሩ እና በማህበር ተደራጅተው የጋራ መኖሪያ ቤት ለመገንባት የተዘጋጁ 57 ማህበራት በወሰን ማስከበር ምክንያት የግንባታ ስራቸው ላይ እንቅፋት እንዳጋጠማቸው የቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
ዛሬ ጠቅለይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር በቢሯቸው መምከር መጀመራቸው ተነግሯል።

ዶ/ር ዐቢይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የነበሩትን ስራዎች እና መሻሻሎች ላይ ነው ግምገማ ማካሄድ የጀመሩት።

በዚህ የግምገማ መድረክ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አማራሮች በተጨማሪ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናትም ተገኝተዋል።

የጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት " ይህ በፌደራል እና የክልል ኃላፊነት ባላቸው የስራ ተዋንያን የሚደረገው ጠቃሚ ግምገማ በድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ እና በሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ ያተኮረ ነው። " ብሏል።

በዛሬው መድረክ የህወሓት ሊቀመንበር እና የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በአካል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ተገናኝተዋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉ።

የዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የካቲት 03 ቀን 2016 ዓ.ም ይመረቃል።

የምረቃ ስነ-ስርዓትን ተከትሎ በዕለቱ ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት:-

ከአፍንጮ በር ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

ከሰሜን ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣ከዮሃንስ ቤተ ክርስቲያን ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

ከአራት መንታ ወደ ጅንአድ፣

ከይርጋ ሃይሌ የገበያ ማዕከል ወደ አቡነ ጴጥሮስ፣

ከሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ወደ ሱማሌ ተራ ፣

ከሱማሌ ተራ ወደ ኤሊያና ሆቴል(ባንኮዲሮማ) መስቀለኛ፣

ከተክለ ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ

➡️ ከሀገር አስተዳደር መብራት (ኢሚግሬሽን) ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

➡️ ከንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ፣

➡️ ከአሮጌው ቄራ ወደ ባንኮ ዲሮማ መብራት፣

➡️ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ፣

➡️ ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፣

➡️ ከመቅደላ ሆቴል ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን፣

➡️ ከቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ወደ ቴሌ እና ወደ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ወደሚገኘው አደባባይ የሚወስዱት መንገዶች በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት (የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ጀምሮ) ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች በሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በዋዜማው የካቲት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት መንገዶችና የምረቃ ስነ-ስርዓቱ በሚከናወንበት በዓድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ዙሪያ ተሽከርካሪ ማሳደርም ሆነ ለአጭርም ሆነ ለረጀም ሰዓት አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑንም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ይለፍ ያላቸው አሽከርካሪዎች ቸርችር ጎዳና ጫፍ የቀድሞ ሜክሲኮ ታክሲ ተራ እና ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ ቸርችር ጎዳና ጫፍ መኪናዎቻቸውን መቆም ይችላሉ።

ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ እንደሚኖር በመገንዘብ ታዳሚዎች የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች ውጪ ወደ ሙዚየም የሚወስዱ መንገዶች ዝግጅቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለእግረኞች ዝግ ይሆናሉ።

(አዲስ አበባ ፖሊስ)

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#አቢሲንያ_ባንክ

በአቢሲንያ ባንክ ፀሐይ አትጠልቅም!

24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት በአቢሲንያ የቨርችዋል ባንኪንግ ማዕከላት ያግኙ

አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
ከቴሌብር አካውንት ወደ ሌላ የቴሌብር ደንበኛ አካዉንት ገንዘብ መላኪያ ታሪፍ ላይ እስከ 80% ቅናሽ ማድረጋችንን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

በአዲሱ የታሪፍ ቅናሽ እስከ ብር 5,000 ሲልኩ 0.1% እንዲሁም ከብር 5,001-75,000 ለመላክ 5 ብር ብቻ የአገልግሎት ክፍያ ይፈጽማሉ።

የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ https://onelink.to/fpgu4m ያውርዱ ወይም *127# ይደውሉ!

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia