TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ነገር #ሰላም ነው፡፡›› ተማሪዎች

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ነገሮች #እንደቀድሞው ወደ #ሰላማዊ ሁኔታ መመለሱን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ያነጋገራቸው ተማሪዋች ገልጸዋል። የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል አቡ አንዳርጌ ‹‹አሁን ላይ ሁሉም ነገር ሰላም ነው፡፡ ወደ ዩኒቨርሲቲው ከተመለስኩ በኋላ የተለወጡ ነገሮችን አስተውያለሁ›› ብሏል፡፡

አብዛኛው የዩኒቨርሲቲው ግቢ #የአጥር ግንባታ መጠናቀቁንና የፀጥታ ጥበቃውም ተሻሽሎ እንዳገኘው ነው ተማሪ አቡ ለአብመድ ያስታወቀው፡፡ ብዙዎቹ ከዩኒቨርሲቲው ርቀው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እየተመለሱ ስለመሆናቸውም ተናግሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እንደ ከዚህ ቀደሙ #ብሔር ለይቶ አንድ ላይ የመንቀሳቀስ ልምድ መቅረቱን መታዘቡንም ገልጿል፡፡ ‹‹ፖሊስ እንደበፊቱ በሁሉም አቅጣጫ ሳይሆን በበር ይገባል፡፡ መታወቂያ አሳይቶ የመግባት ልምድም ዳብሯል›› ነው ያለው ተማሪ አቡ፡፡ ‹‹የወደፊቱን ባላውቅም አሁን የሚታየው እንቅስቃሴ ጥሩ ነው፤ ከፍተኛ መሻሻል አለ›› ነው ያለው፡፡

ተማሪ ቤተልሔም ኃይሉም የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሰላም የተሻሻለ መሆኑን ነው ያረጋገጠችው፡፡ ‹‹ከምዝገባው ቀን አሳልፈን በመገኘታችን የገንዘብ ቅጣት ተጥሎብናል፡፡ በነበረው ግርግር ምክንያት በተቀሰቀሰው እሳት ቃጠሎ መታወቂያ የጠፋባቸው ተማሪዎች አሁን ላይ እየተጉላሉ ነው፤ የፀጥታው ጉዳይ ግን አሁን ሰላማዊ ነው›› ስትል ለአብመድ በስልክ ተናግራለች፡፡

ሌላኛዋ የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ብስኩት አለማየሁም የፀጥታ ችግሮች ተስተካክለው በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ ሁኔታ መፈጠሩን ተናግራለች፡፡ የተጀመረው ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስባለች፡፡

በምዝገባ ወቅት መታወቂያ ባለመያዛቸው መቸገራቸውን የተናገሩ ተማሪዎችን ጉዳይ በተመለከተ ምላሽ የሰጡት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ሪጅስትራር አቶ መኩሪያው አበራ ‹‹መንገድ ተዘግቶ ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ የራሱ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፤ ችግሩን ተረድተን ለምዝገባው እስካሁን እያስተናገድን ነው፡፡

የጠፋባቸውን መታወቂያ ለማውጣትም ይሁን ለምዝገባ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ባይሆንም እንኳ በፊት የነበረውን አሠራርና ሥርዓት ተከትሎ ምላሽ እየተሰጠ ነው›› ብለዋል፡፡

የቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር መርሻ አሻግሬ ተማሪዎች አስቀድሞ ከጥር መጀመሪያ አንስቶ ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲገቡና የመማር ማስተማር ሂደት እንዲጀመር ተገልጾላቸው እንደነበር ነው ዶክተር መርሻ የተናገሩት፡፡ ነገር ግን ‹‹በስጋት ምክንያት ወደ ዩኒቨርሲታችን ያልመጡ ተማሪዎች ካሉ ትምህርት እያመለጠ ነውና ይመለሱ፤ በቅጣት እስከ መጭው ዓርብ መመዝገብ ይችላሉ›› ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በፀጥታውም ዙሪያ የተጠናከረ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን አንስተው የተማሪዎችን ግንዛቤ ለማሻሻል ውይይቶችና ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የባከነውን የትምህርት ጊዜ ለማካካስ የትምህርት የጊዜ ሰሌዳውን በመከለስ እስከ ሐምሌ መጨረሻ ድረስ የመማር ማስተማር ሂደት ለመቀጠል ተስማምተናል›› ነው ያሉት አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲደናቀፍ በማድረግ በግጭት የተሳተፉ የአስተዳደር ሠራኞችም ሆኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው እርምጃ እንደተወሰደባቸውና ለሕዝብ ይፋ እንደተደረገም ዶክተር መርሻ አስታውቀዋል፡፡ በሕግ መጠየቅ ያለባቸው በሕግ እንዲጠየቁ መንግሥት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ የፀጥታ ችግር ትምህርት ተቋርጦ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ለሳምንታት በባሕር ዳር መቆየታቸውና የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች በቅርቡ እንዲወጡ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ በባሕር ዳር መቆየታቸው በቅርቡ ወደ ዩኒቨርሲቲው መመለሳቸው የሚታወስ ነው፡፡ የዩኒቨርሲቲው የፀጥታ ሁኔታ መስተካከሉን በመጠራጠር እስካሁን ወደ ዩኒቨርሲቲው ያልተመለሱ ተማሪዎች መኖራቸውንም አብመድ አረጋግጧል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia