TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray የትግራይ ክልል የማህበረሰብ ተወካዮች ጥያቄ እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምን ነበር ? ከትግራይ ወደ አ/አ የመጡ የማህበረሰቡ ተወካዮችና እዚህም ያሉ ተወላጆች ከጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ የትግራይ ህዝብ ከማንም ህዝብ ጋር  መጋጨት እንደማይፈልግ ገልጸው ፓለቲከኞችም ልጓም ማበጀት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። በአፅንኦት በጦርነቱ ከቄያቸው የተፈናቀሉ ወደ ቦታቸው…
#ትግራይ #አማራ

" እኔ #ከሪፈረንደም ውጭ መፍትሄ ያለ አይመስለኝም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትግራይ እና አማራ በኩል ላለው ችግር " ዘላቂው መፍትሄ ህዝባዊ ሪፈረንደም " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጠቅለይ ሚኒስትሩ ፥ ከዚህ ቀደምም በትግራይ እና አማራ ላለው ችግር ዘላቂ መፍትሄ " ህዝቡ ህዝበ ውሳኔ ሲያደርግ " እንደሆነ በተደጋጋሚ እንደተናገሩት ጠቁመዋል።

" የሆነን ሰዎች እዛ ተቀምጠው ፣ እዛ ተቀምጠው ሲናገሩ አይደለም። ህዝቡን መልሰን ህጋዊ በሆነ መንገድ ዓለም እያየው ሪፈረንደም አድርገው ወደሚፈልጉት ቢጠቃለሉ ከዚያ በኃላ ለጥያቄ አይመችም " ብለዋል።

" አሁን ላይ ግን ሪፈረንደም የሚባል ነገር አይፈልገም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " እራሱ ነዋሪው ሳይሆን ሌላ ሰው ነው መወሰን የሚፈልገው እዚህ እየመጣ ጥያቄ ያቀርባል ' አልተፈታም ' እያለ እኔ ደግሞ አቅጣጫ አስቀምጫለሁ እንዲፈታ " ሲሉ ተናግረዋል።

እሳቸው ያስቀመጡት አቅጣጫ በመጀመሪያ የተፈናቀውለው ህዝብ እንዲመለስ ከዛ ህዝቡ እንዲወስን (ሪፈረንደም እንዲያደርግ) መሆኑን ተናግረዋል።

" ሪፈረንደም ከተደረገ በኃላ ህዝቡ የወሰነውን እናክብርለት ፤ እኔ እዚህ ሆኜ መወሰን አልችልም " ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ " በትግራይ በኩል ስናነጋግር ያለው ናሬሽን እና በአማራ በኩል ስናነጋግር ያለው ናሬሽን በጣም የተራራቀ ነው ምንም የተቀራረበ አይደለም ለማቀራረብ የሚቻለው ህዝቡ እራሱ ሲወስን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ (ሪፈረንደም) ውጭ ለጊዜው ሌላ #መፍትሄ ያለ እንደማይመስላቸውም ገልጸዋል።

" ህዝቡ እንዲወስን ከተደረገ የተረጋጋ አካባቢ ይፈጠራል " ብለዋል።

" እያባላን ያለው የቦታ ችግር አይደለም እኛን የሚያባላን እንደ ንብ ቀፎ ውስጣችን የሚጮኸው ጩኸት ነው እንጂ ሀገሩማ በቂ ነው ቢሰራበት ቦታዎቹ ክፍት ናቸው መንገድ የላቸው ፣ ቤት የላቸው ክፍት ናቸው ' አልገባሁም ገባሁ ' እንጨቃጨካለን እንጂ የቦታ ችግር የለም ቦታው ላይ የሚስራት ችግር ነው የሚያጨቃጭቀን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ታዳጊዋ የት ናት ? በትግራይ ዓድዋ ከተማ የታገተችውና ለማስለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊዋ ማህሌት ተኽላይ እስካሁን እንዳልተገኘች እና ድምጿም እንዳልተሰማ ቤተሰቦቿ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። እገታው ከተፈፀመ 7 ቀናት ሆኖታል። የ16 አመቷ ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ መጋቢት 11 ባጃጅ ይዘው በመጡ ' ማንነታቸው አልታወቀም ' በተባሉ ሰዎች ታፍና ከተወሰደች በኃላ በራሷ ስልክ ለአባቷ…
#ትግራይ

ታጋቹ ከ3 ወር መሰወር በኃላ የማስለቀቂያ ክፍያ ተጠየቀባቸው። 

"አጋቾች ነን" ባዮች የጠየቁት ገንዘብ በ1 ሳምንት ጊዜ ካልተከፈላቸው ታጋቹን እንደሚገድሉት እንደዛቱ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

እገታው እንዴት እና መቼ ተፈፀመ ? 

የሰዎች እገታ ከህፃናት አልፎ እድሜያቸው በገፉት ላይም በመቀጠል በህብረተሰቡ ውስጥ ቀውስን ማቀጣጠል መቀጠሉ እየተገለፀ ይገኛል።

ታጋቹ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ በትግራይ ፤ ምስራቃዊ ዞን ጉለመኻዳ ወረዳ የፍረዳሽም ቀበሌ ነዋሪ ናቸው።

ከ3 ወራት በፊት ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ / ም ከቤት እንደወጡ አለመመለሳቸው ያሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው ወደ አቅራቢያ ፓሊስ አመልክተው ራሳቸውንና ሌላውን በማሳተፍ በፍለጋ ቢታክቱም ሳይሳካላቸው ቆይተዋል።

የታጋቹ ሃለቃ ኣኮቦም ቤተሰቦች በከፍተኛ የተስፋ መቁረጥና የሀዘን ስሜት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ታድያ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም የሞባይል ስልክ ጥሪ ይደርሳቸዋል።

የታጋቹ ቤተሰቦች የተደወለላቸው የሞባይል ስልክ ቁጥር የወንድማቸው ሃለቃ ኣከቦም ቢሆንም  ሞባይሉን ሲያነሱት የሰሙት ድምፅ ግን ከዛ በፊት ሰምተውት አያውቁም።

ይህ ማንነቱ ያልታወቀው ደዋይ በወንድማቸው የሞባይል ቁጥር በመጠቀም ፥ "...ወንድማችሁ ኣከቦም በህይወት ለማትረፍና በአካል ለማግኘት ከፈለጋችሁ 350 ሺህ ብር ክፈሉ። " የሚል ትዕዛዝ ያስተለልፋል።

የታጋቹ ወንድም ግደይ መሓሪ አባይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል በሰጠው ቃል ፥ ስልክ ደዋዩ ከአጋቾቹ አንዱ መሆኑን በማሳወቅ የተጠየቀው ብር እንዲከፍሉ የአንድ (1) ሳምንት ጊዜ ብቻ እንደሰጣቸውና ብሩን ካልከፈሉ ወንድማቸውን እንደሚገድሉባቸው እንደ ዛተ ተናግረዋል።

የታጋቹ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ በማህበራዊ ሚድያ ተሰራጭቶ ያነበቡ አስተያየት ሰጪዎች ፦ " ይህንን ያልተለመደና መጤ የእገታ ተግባር እጅግ አሳስቦናል !፤ ይህ እገታ ማቆምያው የት ይሆን ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" አስከፊው ተግባር ወደየ ቤታችን ከመድረሱ በፊት መፍትሄ ያሻዋል " ያሉ አስተያየት ሰጪዎች " ከህግ አካላት በቅንጅት መስራት ሲቻል ችግሩ መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል " ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዓድዋ ከተማ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም የታገተችውና እንድትለቀቅ 3 ሚሊዮን ብር የተጠየቀባት ታዳጊ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ 12 ቀናት ቢያልፋትም ደብዛዋ ሊገኝ አልቻለም።

መረጃው የተዘጋጀው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

ፎቶ 1 ፦ ሃለቃ ኣከቦም መሓሪ ኣባይ
ፎቶ 2 ፦ ተማሪ ማህሌት ተኽላይ

@tikvahethiopia            
#ትግራይ

የኤርትራ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው የኢሮብ የኢትዮጵያ የትግራይ አከባቢዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች ማስጠንቀቅያ ሲሰጥ የሚያሳይ የቪድዮ መረጃ የኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆችን አሰቆጥቷል።

የኤርትራ ሰራዊት ተወካይ የኢሮብ ተወላጆች ስብስቦ ማስጠንቀቅያ ሲሰጥ የሚያሳየው የቪድዮ መረጃ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በመሰራጨት ላይ ሲሆን በክልሉ ሚድያዎችም ሽፋን ሰጥተውታል።

የቪድዮው የድምፂ ቅጂ ምን ይላል ?

"... እናንተ ህዝብ ናችሁ። የምትኖሩበት መሬት ደግሞ የኤርትራ ነው። ኤርትራውያን ከሆናችሁ ለዚሁ አከባቢና መሬት ተገዢ እንዲሁም እዚህ ላለው ሰራዊት የማገዝ ግዴታ አለባችሁ።
አገራዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታም አለባችሁ። በትወልዱም በትጠሉም አንድ የኤርትራ ዜጋ የሚያሳልፈውን ህይወት  ልታልፉ ግድ ይላል።

አንድ ሰው ከዚህ አከባቢ ወደ አገራዊ አገልግሎት ከሄደ ለኤርትራ አገሩ ብሎ ነው የሚሄደው። ስለዚህ እያንዳንዳችሁ አገራዊ አገልግሎት እንደሚመለከታችሁ ማወቅ አለባችሁ።  አባቶች የሃይማኖት መሪዎች ስሙ ከመካከላችሁ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ካለ የኤርትራ መንግስት እዚህ አስገድዶ አያኖረውም። ወደ ኢትዮጵያ የመሄድ መብት አለው። የኤርትራ መሬት ደግሞ ኤርትራውያን ይኖሩበታል።

ወደ አገራዊ አገልግሎት መሄድ ካለብህ ትሄዳለህ፤ ረሃብ ካለ እንደ ሌላው ኤርትራዊ ትራባለህ።  በቃ ተካፍለህ ትኖራለህ። ላንተ ተብሎ የሚደረግ የተለየ ነገር የለም። ልቅ የሆነ አካሄድ ነው የቆየው ይህ ከአሁን በኃላ አይቀጥልም። " ሲል ያስጠንቅቃል የኤርትራ ሰራዊት ተወካዩ።

ቪድዮውን የተመለከቱ የኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆች የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና የፌደራል መንግስት በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ከጥፋት እንዲታደግዋቸው ተማፅነዋል።

ብርሃን ወዲ ኢሮብ የተባለው የብሄረሰቡ ተወላጅ በሰጠው አስተያየት " ... አራት ዓመት ሙሉ በሁለት ተከፍለን ኮምፓስዋ እንደጠፋት መርከብ ሆነን ተሰፋችን ጨልሞብናል።  ብሄረሰባችን እየጠፋ አረ የሰሚ ያለህ.." ሲል ምሬቱን ገልጿል።

የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ፦
- የዛላኣንበሳ ከተማ
- በጉሎመኸዳ ወረዳ ማርታ ፣ አዲስ ተስፋ ፣ አዲስ ዓለም ፣ ሸዊት ለምለምና ሰበያ
- በኢሮብ ወረዳ እንዳልጌዳ ፣ ወርዓትለ ዓገረ ሎኽማና ዓሊቴና የተባሉ የኢትዮጵያ አከባቢዎች ተቆጣጥሮ ይገኛል።

በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በታሕታይ ኣድያቦ የኩናማ ማህበረሰብና ሌሎች የሚኖሩባቸው ገማህሎ ፣ አደመይቲ ፣ የባድመ ከተማና አከባቢው ፣ ዓዲ ፀፀር ፣ ለምለም ሸዊት ፣ ሸምበሊና ፣ መንጠብጠብ ፣ ዓዲ ኣሰር ፣ ሰየምቲ አድያቦ እንደሁ ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።
                                               
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ የኤርትራ ሰራዊት በተቆጣጠራቸው የኢሮብ የኢትዮጵያ የትግራይ አከባቢዎች ለሚገኙ ነዋሪዎች ማስጠንቀቅያ ሲሰጥ የሚያሳይ የቪድዮ መረጃ የኢሮብ ብሄረሰብ ተወላጆችን አሰቆጥቷል። የኤርትራ ሰራዊት ተወካይ የኢሮብ ተወላጆች ስብስቦ ማስጠንቀቅያ ሲሰጥ የሚያሳየው የቪድዮ መረጃ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በመሰራጨት ላይ ሲሆን በክልሉ ሚድያዎችም ሽፋን ሰጥተውታል። የቪድዮው የድምፂ ቅጂ ምን ይላል ?…
#ትግራይ

የኤርትራ ሰራዊት ከሶስት የኢትዮጵያ የትግራይ ምስራቃዊ ዞን ወረዳዎች ' 93 ወጣቶች ' አግቶ መሰወሩን የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ገልጹ።

እገታው የተፈፀመው ኢትዮጵያ በትግራይ በኩል ከኤርትራ ከምትዋሰንባቸው የዛላንበሳ ከተማ የጉሎመኻዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች ላይ ነው ተብሏል።

ይህን የተገለፀው የከተማ እና የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች ከኤርትራ ድንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የዓዲግራት ከተማ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች (AU military attaches) ባካሄዱት ውይይት ነው። 

የዛላአንበሳ ከንቲባ መምህር ብርሀነ በርሀና ፣ የጉሎመኻዳ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቶም ባራኺ በጋራ ከአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በኃላ :- 

በአከባቢያቸው የተለወጠ የፀጥታ ሁኔታ አለመኖሩ ፤

ጦርነቱ ተከትሎ የተፈጠረው ችግር እንዳልተፈታ፤

የኤርትራ ሰራዊት የዛላአንበሳ ከተማ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ እንደሚገኝ፤

ከዛላኣንበሳ ከተማ መግብያ በቅርብ ርቀት ዝባን ሑፃ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ኬላ አቋቁሞ ፍተሻ እንደሚያካሂድ ፤

የኤርትራ ሰራዊት ከዛላኣንበሳ ከተማ 15 ፣ በቁጥጥሩ ስር ከሚገኙ የጉሎመኻዳና የኢሮብ ወረዳዎች የተለያዩ ቀበሌዎች 78 ባጠቃላይ 93 ወጣቶች አግቶ የወሰዳቸው ወጣቶች ያሉበት ሁኔታ እንደማይታወቅ  አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር በሚገኙ የጉሎመኻዳ እና የኢሮብ ወረዳዎች 10 ቀበሌዎች የሚኖር ህዝብ እርዳታ ጨምሮ የጤና የትምህርት እንዲሁም ሌሎች የመንግስት አገልግሎቶች እንደማያገኝ አስተዳዳሪዎቹ ለአፍሪካ ህብረት ወታደራዊ ታዛቢዎች በዝርዝር አስረድተዋል።

በስብሰባው ወቅት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተወካዮች መሳተፋቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

የሀገር መከላከያ ሚንስትሩ ዶክተር አብራሃም በላይ በየካቲት 2016 ዓ.ም የመጨረሻው ሳምንት ላይ በትግርኛ ቋንቋ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃለመጠይቅ ፥ "  የሻብዕያ ሰራዊት " ብለው የገለፁት የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ መሬት ስለመውጣት ጉዳይ ፤

"  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊት በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች የሻዕብያ ሃይል ገብቶ ነበር ፣ ከስምምነቱ በኋላ እንዲወጣ ተደርጓል ፣ አሁንም የተቀሩ ቦታዎች ካሉ ቦታዎቹ እና ቀበሌዎች ከፌደራልና ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ቡድን በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲሰጠው እየሰራን ነው ሁሉም ልክና መስመር ይይዛል " ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው የተዘጋጀው።
                                                
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
 #Update " ለፍትሃዊ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ መሰጠት አለበት ፤ መንግስት የገባው ቃል ካልተገበረ ማህበሩ መብቱን ለማስከበር ይንቀሳቀሳል " - የትግራይ መምህራን ማህበር የትግራይ መምህራን ማህበር የተገባለት ቃል እንዲተገበር ጠየቀ። ማህበሩ ባወጣው መግለጫ፤ መምህሩ የተማሪው የትምህርት ጥማት ለማርካት እየሰራ ቢገኝም ላቀረበው ጥያቄ ተገቢ ምላሽ ባለማግኘቱ በኑሮ ውድነት ከፉኛ እየተጎዳ ይገኛል ብሏል።…
 #ትግራይ #መምህራን

" ጥያቄያችን ፍትሃዊ ምላሽ ካላገኘ ወደ ቀጣይ እርምጃ እንገባለን " - የትግራይ መምህራን ማህበር

የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጥያቄያችን ፍትሃዊ መልስ ካላገኘ በምክር ቤት አስወስነን ለቀጣይ ትግል እንዘጋጃለን " አለ።

የትግራይ መምህራን ማህበር ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የ5 ወራት ውዙፍ ደመወዝ ለመክፈል የገባው ቃል እስከ አሁን አልተገበረም ብለዋል። 

መምህራን ውዙፍ ደመወዝ ባለመከፈላቸው ምክንያት ለከባድ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠዋል ሲል አሳውቋል።

ማህበሩ ፤ ጊዚያዊ አስተዳደሩ የትግራይ መምህራን ካለቸው ያልተከፈለ የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ መካከል የ5 ወራት እንደሚከፈል በወርሃ ጥር መግባባት ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል።

ነገር ግን እስከ አሁን አለመተግበሩ እንዳሳዘነው ገልጿል።

መምህራኑ ያላቸው 17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ አለመከፈላቸው እየታወቀ ፣ ከጦርነቱ በፊት ከደደቢት ማይክሮ ፋይናንስ የወሰዱት ብድር ወለድ የወለድ ወለድና ቅጣት እንዲከፍሉ እየተገደዱ መሆኑን የገለጸው ማህበሩ " ጉዳዩ መንግስታዊ መፍትሄ ያሻዋል " ብሏል።

" ፍትሃዊው ጥያቄያችን ፍትሃዊ የሆነ መላሽ እንዲያገኝ ተደጋጋሚ መግለጫ አውጥተናል ፤ ከሚመለከተው አካል ጋር ተወያይተናል ነገር ግን ምልስ የማያገኝ ከሆነ በማህበሩ ምክር ቤት በማስወሰን ለቀጣይ እርምጃ እንዘጋጃለን " ሲል ማህበሩ አስጠንቅቋል።

' ቀጣይ እርምጃው ምን እንደሆነ ' ግን በግልፅ አላብራራም።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።
                        
@tikvahethiopia            
#ትግራይ

ሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች በክልሉ ለሚገኙ ሚድያዎች መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ " በፕሪቶሪያ ውል ያልተፈፀሙት እንዲተገበሩ እየሰራን እንቀጥላለን " ብለዋል። 

" የፕሪቶሪያ ውል የፈረምነው የተለያዩ የትግራይ ቦታዎች ከክልሉ አስተዳደር ውጭ በነበሩበት በርካታ ወገኖች ከቄያቸው በተፈናቅሉበት ጊዜ ነበር " ያሉት ጄነራሉ " የውሉ ተዋዋዮች በህገ-መንግስት መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ተስማምተዋል " ብለዋል። 

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውልን በጥንቃቄ መተግበር ይገባል " ሲሉ ገልጸዋል።

" አሁን በመታየት ያለው ውጤት የጦርነቱ ውጤት እንጂ የጦርነቱ መነሻ አይደለም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግራይ በሃይል የተያዘባት መሬት ሙሉ በሙሉ መልሳ የተማላ ቁመናዋ መያዝ ፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ እንዲተገበሩ ያስገድዳል ይህ እንዲሆን ደግሞ በሃይል በተያዙ ቦታዎች ያሉ ታጣቂዎች መውጣትና ህጋዊ ያልሆነው አስተዳደር መፍረስ አለባቸው " ብለዋል።     

" ህጋዊ ያልሆኑ አስተዳደሮች ማፍረስና ታጣቂዎች ትጥቃቻውን ማስፈታት የፕሪቶሪያ ውል የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን ቀጥሎ የሚደረገው ሁሉ #ሰላም ከተረጋገጠ በኋላ የሚሆን ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ተፈናቃዮች ሲመለሱ ክብራቸው ተጠብቆ ፣ የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማት ሁሉ ተሟልቶ ሰብአዊ ድጋፍ ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎች በማድረግ መሆን አለበት "  ያሉት ጀነራሉ  " አስተዳደርን በሚመለከት ቀበሌዎችና ወረዳዎችን የሚያስተዳድሩ ጊዚያዊ  አስተዳደሮች ራሱ ህዝቡ ይመርጣል " ብለዋል።  

ዘላቂ መፍትሄ በሚመለከት ምን አሉ ?

" የፌደራል መንግስት ' አከባቢዎቹ በፌዴራል ስር ቆይተው #ሪፈረንደም ይካሄድ ' የሚል አቋም ያለው ሲሆን በእኛ በኩል ደግሞ በአከባቢው ጊዚያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ ወደ ትግራይ ይመለሱ የሚል አቋም ነው ያለው፤ ይህ የአቋም ልዩነት እስካሁን አልተፈታም እንዲፈታ ደግሞ ቀጣይ ሰላማዊ ትግል እናደርጋለን " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

Photo Credit - Tigrai & DW TV
                                          
@tikvahethiopia            
#ትግራይ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር ትናንት ሌሊት በራያ ዓዘቦ ወረዳ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ ወገኖች " በግፍ ተጨፍጭፈው መገደላቸውን " ገለጸ።

አስተዳደሩ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉና ግድያ የተፈጸመበትን ልዩ ስፍራ በተመለከተ በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም ድርጊቱን " ዘግናኝ ወንጀል " ብሎታል።

" ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት ከዓፋር አከባቢ የመጡ ናቸው " ብሎ " ማንነታቸውን በሚመለከት ጥብቅ ክትትል እያደረግን ነው " ሲል አሳውቋል።

የአፋር ክልል መንግስትና የፌደራል ፖሊስም ወንጀለኞችን ተከታትለው በመያዝ ወንጀል ወደ ፈፀሙበት አከባቢ መጥተው ይዳኙ ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፤ " የራያ ዓዘቦ ወረዳ ህዝብ እና አስተዳደር ሁኔታውን ለማረጋጋት እና ለመቆጣጠር ያደረጉት ከፍተኛ ጥረት  እጅግ የሚበረታታ ነው " ብሏል።

ወንጀለኞችን በመያዝ እና ለሕግ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ለህዝቡ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

በትግራይ፣ መቐለ የሚገኘው ፍሬምናጦስ የአረጋውያን ፣ የአእምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ሚገመት የገንዘብ የቁሳቁስ ድጋፍ ቃል ተገባለት።

ይህን የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ቃል የተገባለት ትላንት " #አለሁ_ለፍሬምናጦስ " በሚል በመቐለ ከተማ በተካሄደ ዓለም አቀፍ የሆነ የገቢ ማሳባሰብያ የቴሌቶን ፕሮግራም ላይ ነው።

መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ የተባለ የትእምት ኩባንያ በምግባረ ሰናይ ደርጅቱ ላክ በባለፈው ሚያዝያ ወር በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የወደመውን አዳራሽ ሙሉ ለሙሉ መልሶ እንደሚገነባው ቃል ገብቷል።

ከዚህ በተጨማሪም የ20 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው የጭነት መኪና፣ አምቡላንስ የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ለሚያሰገነባው ግዙፍ የእንክብካቤ ማእከል የሚውሉ ማሽነሪዎች በአገር ውስጥና በውጭ በጎ ለጋሾች ተበርክቷል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱ መስራችና ስራ አስኪያጅ አባ ገብረ መድህን በርሀ ፥ " ጦርነት በፈጠረው ጉዳት ምክንያት #የአእምሮ_ህሙማን_ቁጥር በመጨመር ላይ በመሆኑ ድርጅቱ ለሚሰጠው የነፃ እንክብካቤ አገልግሎት የህዝቡ እገዛ ይሻል " ብለዋል።

ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በአሁኑ ወቅት 29 አረጋውያን ፣ 206 የአእምሮ ህሙማን እና 40 አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናት ጨምሮ በአጠቃላይ #ከ275_በላይ ለሆኑ ወገኖች የተሟላ የመጠለያ አገልግሎት በመስጠትና በመንከባከብ ላይ ይገኛል። 

በትግራይ በነበረው አስከፊ የሆነ ጦርነት ምክንያት ግን ወደ ማዕከሉ መግባት የሚፈልጉ ወገኖች ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል።

ለማሳያ ባለፉት ወራት ብቻ 1500 የእእምሮ ህሙማን ወደ ማእከሉ ለመግባት መመዝገባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከምግባረ ሰናይ ድርጅቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል። 

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia            
#ትግራይ #ኢሮብ

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነቱ በኃላም ቢሆን እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የኢትዮጵያ፣ ትግራይ ኢሮብ ወረዳ 23 ት/ ቤቶች በኤርትራ ወታደሮች ስር ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል ኢሮብ ወረዳ ተነፃፃሪ የሆነ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ባለባቸው አከባቢዎች ባሉ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በቀጣዩ ሃምሌ ወር 2016 ዓ.ም ለሚሰጠው አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመዘጋጀት ይገኛሉ።

ለፈተናው እየተዘጋጁ ያሉት ተማሪዎች በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ ፤ ትግራይ ክልል በጊዜያዊ አስተዳደር ስር ያሉ ናቸው።

በወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ስር የሚታወቁ እና ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩት አንድ ሁለተኛ ደረጃ የሚገኙባቸው 23 ትምህርት ቤቶች ከ3 ዓመት በላይ #በኤርትራ_ወታደሮች_ቁጥጥር_ስር እንደሚገኙ በኢሮብ ወረዳ የትምህርት ፅህፈት ቤት ተገልጿል።

የትምህርት ቤቶቹ  መምህራን እና ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል። 
 
ቃላቸውን የሰጡ ተማሪዎች ፦
- ጦርነቱ ብዙ ነገሮች እንዳሳጣቸው
- አሁን በወረዳቸው ትምህርት ቤት የኢንተርኔት አቅርቦት ጨርሶ እንደሌለ
- ውሃ ፣ መብራት ፣ ትራንስፓርት የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንደሌለ ጠቁመዋል።

ተማሪዎቹ በቴክኖሎጂ ታግዞ ከሚፈተኑ ተማሪዎች ጋር ተፈኳኳሪ ለመሆን እንደሚከብድም ገልጸዋል።

ያም ሆኖ ግን አሁን ላይ የተገኘው ዕድል እንዳያመልጥ ለመፈተን ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

መምህራን በበኩላቸው ፥ በወረዳው ያሉት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የክልሉና የፌደራል ትምህርት ሚኒስቴር እገዛ እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት በኤርትራ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና ተማሪዎች ነፃ ወጥተው የዘወትር አገልግሎት እንዲሰጡ ትኩረት ማድረግ አለበት ብለዋል።

በወረዳው በጦርነት ምክንያት የትምህርት ሴክተር ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የወደመ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም ምንም የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት በሌለበት ለመፈተን በዝግጅት ላይ መሆናቸው ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት የእገዛ እጃቸው እንዲዘረጉ የወረዳው የትምህርት ፅህፈት ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ይህንን መረጃ የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማደረግ የላከው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia            
#ትግራይ

ግለሰቡ በአሰቃቂ የግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ይፈለጋል።

ግድያው መቼና ? የት ተፈፀመ ? 

አሰቃቂ የግድያ ተግባሩ ግንቦት 17/2016 ዓ.ም ነው የተፈጸመው።

የተፈፀመበት ደግሞ በትግራይ ደቡባዊ ዞን ራያ ዓዘቦ ወረዳ ሀወልቲ ቀበሌ ዓዲ መጥሓን በተባለ ልዩ ቦታ ነው።

በግድያ ተግባር ተጠርጥሮ የሚፈለገው ግለሰብ ኣባዲ መሓሪ ረዳ ይባላል።

ግለሰቡ የአምስት ልጆች እናት የሆነች ባለቤቱ ወ/ሮ ዕፃይ ከበደ ገድሎ ከተሰወረ ከአንድ ወር በላይ ሆኖታል። 

የወ/ሮ ዕፃይ ቤተሰቦችና የራያ ዓዘቦ ወረዳ ፓሊስ በጋራ በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ የተሰወረውን ኣባዲ መሓሪ ረዳ የተባለ ግለሰብ ያየውና ያለበት ቦታ የሚያውቅ 0996709824/0919548923 የሞባይል ቁጥሮች በመጠቀም መረጃ እንዲሰጣቸው ትብብር ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia