TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር ደብረፅዮን ስለ ህዳሴው ግድብ⬇️

የሕወሓት ሊቀ-መንበር ዶክተር #ደብረፅዮን_ገብረሚካኤል የበረታ ወቀሳ ሲሰነዘርበት በከረመው የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።

ደብረፅዮን በትናንትናው ዕለት ከትግራይ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ ለግድቡ ግንባታ የተዘጋጀው ውል መቀየሩን ገልጸዋል።

ዶ/ር ደብረፅዮን "መጀመሪያ የነበረው ውል ተቀይሯል። በመጀመሪያ ያዘጋጀንው በፅሁፍ #የተቀየረ ነገር የለም። በተግባር ግን ተቀይሯል።

ማሻሻልም አልመረጥንም። እንደ አካሔድ የመጀመሪያው ውል፤ መሻሻል የሚገባው ውል ነው። የመጀመሪያ ውሉ ከአንድ አመት በኋላ #ተቀይሯል። የእኛ ኩባንያ አስገብተናል። ኢትዮጵያዊ ኩባንያ የሚያመነጨው ኃይልም ተቀይሯል። የመጀመሪያው ውል 5250 ነው የሚለው።

ወደ ስድስት ሺሕ በመጀመሪያው አመት ስድስት ሺህ ነው የተቀየረው" ሲሉ ተናግረዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን በውሉ ላይ የተደረገው ለውጥ በታላቁ ኅዳሴ ግድብ ግንባታ ከሚሳተፉት ሜቴክ እና የጣልያኑ ሳሊኒ ኩባንያዎች የትኛውን እንደሚመለከት የገለጹት ነገር የለም። በጽሁፍ ያልሰፈረበትንም ምክያት አላብራሩም።

ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ የግድቡ ግንባታ በአስር አመትም አይጠናቀቅም የሚል አስተያየት ሰጥተዋል የሚል #ወሬ ከተሰማ በኋላ
ኢትዮጵያውያን ጎራ ይዘው ሲከራከሩ ሰንብተዋል። በተለይ ዋልታ በግንባታው መዘግየት እና የክፍያ አፈፃጸም ላይ የሰራው ዘገባ ለውዝግቡ መጦዝ ከፍ ያለ ሚና ነበረው። በውሐ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ዘርፍ ምኒስትር ድኤታ ዶ/ር ፍሬሕይወት ወልደሐና፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሐም በላይ እና የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ተወካይ ሆነው የቀረቡት አቶ አብዱል አዚዝ መሐመድ ግንባታው #ከታቀደለት ጊዜ በላይ መዘግየቱን በዘገባው ተናግረው ነበር። አቶ አብዱል አዚዝ እንዳሉት ሜቴክ እስካሁን ለሰራው ስራ 16 ቢሊዮን ብር ገደማ ተከፍሎታል።

ዶክተር ደብረፅዮን ግን በአምስት አመታት ኃይል ለማመንጨት የተያዘው ዕቅድ ተለውጧል ብለዋል። ዶክተር ደብረጽዮን "ከጅምሩ ኮንትራቱን የለወጡ ነገሮችን ታሳቢ አድርገን ነው መነጋገር የምንችለው። በ5 አመት ኢነርጂ እናመነጫለን የሚለው አይሰራም። ለምን ተቀይሯል። በተቀየረ ውል መነጋገር አይቻልም" ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የግንባታው ሒደት ያለበትን ደረጃ መናገር እንደማይችሉ የገለጹት የሕወሓት ሊቀ-መንበር "እስከ የካቲት መጋቢት ነው የማቀው እኔ። ከዛ በኋላ ያለው በሌሎች #ኃላፊዎች የሚገለፅ ነው። እኔ እስከነበርኩበት ጊዜ ድረስ ግን ባጠቃላይ #በጥሩ ሁኔታ ሊባል የሚችል ሥራ ነው እየተሰራ የቆየው" ብለዋል።

አቶ አብዱል አዚዝ መሐመድ የሥራው አፈጻጸምን በተመለከተ ግልፅ መረጃ እንደሌለ ተናግረው ነበር።

©ሸገርTribune
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደምቢ_ዶሎ

• " በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው ነው " - ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ

• " እንዲህ አይነት ክስተት የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ ነው " - ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ

በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት ማስተማሪያ ሆስፒታል 2 ጭንቅላት ያለው ህፃን ተወለደ።

የዩኒቨርሲቲው የጤና ሳይንስ ማስተማሪያ ሆስፒታል የጽንስና ማህፀን ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ፀጋዬ ሚደክሳ በሰጡት ማብራሪያ ህፃኑ ሁለት ጭንቅላት ኖሮት መወለዱን ተናግረዋል።

ዶ/ር ፀጋዬ ፤ በሆስፒታሉ እንዲህ አይነት ክስተት ሲከሰት ይህ የመጀመሪያው መሆኑን በመግለፅም ህፃኑ በተሳካ ቀዶ ጥገና መወለዱን አስረድተዋል።

በአንዳንድ ነፍሰ ጡር እናቶች ላይ እንደዚህ አይነት ክስተቶች አልፎ አልፎ የሚከሰቱ እና በእናቶች ማህፀን ውስጥ በሚስተናገዱ እንቁላሎች ብዛት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ዶ/ር ፀጋዬ አብራርተዋል።

በኢኒስቲትዩቱ የህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ናጋሳ ቶላሳ በበኩላቸው ክስተቱ በመንታ ምድብ የሚመደብ እና የመከሰት እድሉ በጣም አናሳ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሁኑ ጊዜ እናትም ሕፃኑም #በጥሩ_ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity