TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ ትግራይ ክልል ውስጥ በ5 መጠለያ ጣቢያዎች ከ900 በላይ ሰዎች ከምግብ እጦት እና ከመድሃኒት እጥረት ጋር በተያየዝ ሞተዋል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አሳውቋል። የተቋሙ የመቐለ ቅርንጫፍ ፤ ረሃብ የሰው ህይወት መንጠቅ ከጀመረ ወራቶች መቆጠሩንም ገልጿል። * በሽረ * አክሱም * በአብይአዲ * በመቐለ * ዓዲግራት ባሉ መጠለያ ጣቢያዎች የሰው ህይወት በረሃብ እና በመድሃኒት እጥረት…
#FederalGovernment

የፌዴራል መንግሥት ከተለየዩ አካላት ጋር በመተባበር አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈለጋቸው 3.8 ሚሊዮን ወገኖች እርዳታ ማድረሱን አሳውቋል።

ለሰብዓዊ እርዳታ በሦስት ተከታታይ ዙሮች 15 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን አመልክቷል።

ከዚህ ውስጥ 40 በመቶውን የፌዴራል መንግሥት፣ 60 በመቶውን ደግሞ የዓለም ባንክ እንደሸፈነው ገልጿል።

በቀጣይ በድርቅ እና በተለያዩ ምክንያቶች ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ9 ሚሊዮን በላይ ሚሊዮን ወገኖች ተለይተው እርዳታውን ከጥር እስከ የካቲት ለማድረስ እየተሰራ ነው ብሏል።

ለዚህም 9.2 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

" አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ያልተቋረጠ ሰብአዊ እርዳታ ለማድረስ እየሰራሁ ነው " ያለው ፌዴራል መንግሥት፤ " የክልል መንግሥታትም የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ " ብሏል።

ለተቸገሮች ወገኖች ለመድረስ የእርዳታ ድርጅቶችን ጨምሮ ሁሉም ወገኖች የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ መቅረቡን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#FederalGovernment

የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ የፌዴራል መንግሥት ገለጸ።

የፌዴራል መንግሥት ፤ ሕወሓት ትላንትና ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን #በአንክሮ እንደተመለከተው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ መሆኑን የኢፌድሪ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን አሳውቋል።

ይሄንንም በተመለከተ የፌዴራሉ መንግሥት ከመነሻው እስካሁን ያለው አቋም ወጥ እና የማይናወጥ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

" ህወሓት " ትላንትና ያወጣው መግለጫ በዚህ ተያይዟል ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/84794?single

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FederalGovernment የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ የፌዴራል መንግሥት ገለጸ። የፌዴራል መንግሥት ፤ ሕወሓት ትላንትና ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነት እንዲከበር መጠየቁን #በአንክሮ እንደተመለከተው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ዋነኛው መፍትሔ የፕሪቶርያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ…
#FederalGovernment

የፌዴራል መንግሥት ፤ " የፕሪቶርያው ስምምነት ከምንም በላይ ተግባራዊ ምላሽ እንደሚፈልግ " በገለፀበት የዛሬ መግለጫው ፤ በትግራይ ክልል ተፈናቃዮችን ወደ መደበኛ መኖሪያቸው ለመመለስ እንዲቻል የሚመለከታቸውን አካላት አቀናጅቶ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ትክክለኛ ተፈናቃዮችን ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ መደረጉንም ገልጿል።

የአከራካሪ ቦታዎችን ሁኔታ በዘላቂነት ለመፍታት በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ጉዳዩ በዋናንት ከሚመለከታቸው ከአማራ እና ከትግራይ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ እንደነበር አስታውሷል።

" በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት በሕወሓት በኩል ታጥቀው ሲዋጉ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ መመለስ አለባቸው " ያለው የፌዴራል መንግሥት " ለዚህ የሚረዳ የተሐድሶ ኮሚሽን ተቋቁሟል። ፌዴራል መንግሥትም የሚጠበቅበትን የሰው ኃይልና በጀትም መድቧል " ብሏል።

የፌዴራል መንግሥት ፤ ከሰሜኑ ጦርነት ጋር የተያያዙ ወንጀሎችን በተመለከተ ተገቢውን ርምጃ በእራሱ በኩል መውሰዱን ፤ ተጠያቂ መሆን ያለባቸውንም ተጠያቂ ማድረጉን ገልጿል።

ሌሎች ሥራዎችን ለማከናወን እንዲቻል የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ዐዋጅ ረቂቅ ዝግጅት መጠናቀቁን አሳውቋል።

ይህ ሂደት እንዲሳካም እንደ ሌሎቹ ክልሎች ሁሉ የትግራይ ክልልም ተገቢው ሚና እንዲጫወት ይጠበቃል ብሏል።

የፌዴራል መንግሥት ፤ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ልማትና ደኅንነት ሲባል ማድረግ ያለበትን ተግባራት ሁሉ ከሚገባው ባሻገር ተጉዞ ማከናወኑን አሳውቋል።

ለክልሉ ሕዝብ መደረግ ያለባቸው ድጋፎችንም በራሱ ዐቅምም ሆነ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለማከናወን የፌዴራሉ መንግሥት ምንጊዜም ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#FederalGovernment #TPLF

" አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " - የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን

የፌዴራል መንግሥት ኮሚኒኬሽን በህወሓት ጉዳይ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፦

- ህወሓት እንዴት ሕጋዊ ሰውነቱን ሊያጣ እንደቻለ ወደኃላ መለስብሎ አስታውሷል ፤

- የፕሪቶሪያ ስምምነት ሲፈጸም የፌዴራል መንግሥት በስምምነቱ የገባው ግዴታ የህወሓት የሽብርተኝነት ፍረጃ እንዲነሣ ሂደቱን የማሣለጥ ኃላፊነት (የስምምነቱ አንቀጽ 7 (2) (C)) እንደሆነ ፤

- የፌዴራል መንግሥት የህወሓትን የሕግ ሰውነት እና የምዝገባ ጉዳይ በተመለከተ በፕሪቶሪያ ስምምነት ውስጥ የወሰደው የተለየ ኃላፊነት ወይም ግዴታ እንዳልነበር፤

- ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት እንቀጽ 7 (1) (A) መሠረት የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት፣ ሕጎች፣ የፌዴራል ተቋማትን እና ሌሎች ሕገ መንግሥታዊ ተቋማትን ሥልጣን የማክበር ግዴታ መግባቱም ፤ ስለዚህ ሕወሐት የሀገሪቱን የፖለቲካ ፖርቲዎች የምዝገባ ሕግ እና የምርጫ ቦርድን ሥልጣን በማክበር የመሥራት ግዴታ እንዳለበት ... ገልጿል።

የፌዴራል መንግሥት በመግለጫው ፤ ህወሓት ወደ ህጋዊ መስመር ለማምጣት ስለተኬደባቸው መንገዶች ፣ ውይይቶች ፤ በህወሓት እና ምርጫ ቦርድ በኩል ስለተነሱት ልዩነቶች አብራርቷል።

ድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና እንዲኖረው ለቦርዱ የትብብር ጥያቄ ስለማቅረቡም አስታውሷል።

እንዲሁም አዋጅ እስከማሻሻል በደረሰ እርምጃ ድርጅቱ ወደ ህጋዊ መስመር እንዲገባ ለማድረግ የተኬደበትን ርቀት ገልጿል።

ይህን ተከትሎ ህወሓት ሕጋዊ ሰውነት እና ዕውቅና ለማግኘት የሚጠበቅበት የፓርቲ ሰነዶቹን ማለትም የፓርቲውን ፕሮግራም እና ሕገ ደንብ፣ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በማቅረብ በተሻሻለው አዋጅ መሠረት ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነት እንዳገኘ አሳውቋል።

በመሆኑም " የምዝገባ እና የህግ ሰውነትን ጉዳይ በዚህ በመቋጨት፤ የሁሉም ባለድርሻ አካል ርብርብ ሰላምን በማጽናት፣ በመልሶ ግንባታ እና በልማት አጀንዳ ላይ ሊሆን ይገባል " ብሏል።

ፌዴራል መንግሥት"  አላስፈላጊ እና ሕዝብን የማይጠቅም፣ ትርጉም አልባ ንትርክን አስወግደን ለሕዝብ ረብ ያላቸው ጉልህ የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ላይ ልናተኩር ይገባል " ሲልም ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia