TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የተረክ በM-PESA የሁለተኛ ዙር እጣ የመጀመርያ መኪና ወላይታ ገብታለች::
ወላይታ ሶዶዎች ሀሹ እንላችኋለን!
ቀጣዩን ሽልማት እስቲ ወደናንተ ጥሩት!

M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ ዛሬ 3,854 የመንግሥት ሰራተኞች ፈተና ተቀምጠዋል። ዛሬ ለባህሪና ብቃት ምዘና ፈተና የተቀመጡት ፦ - የአዲስ አበባ መሬት ይዞታ ቢሮ፣ - የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ - የከንቲባ ፅ/ቤት (ማለትም የ3 ተቋማት) ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች፣ ሰራተኞች እና ባለሙያዎች ናቸው። ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቪርስቲ በ6 ኪሎ ካምፓስ ውስጥ እየተሰጠ ይገኛል። ከዚህ ቀደም 15,151 የአስተዳደሩ…
#Update

" ፈተናውን ያለፉት 1 ሺህ 680 ናቸው " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

ለ3 ሺህ 861 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የተሰጠው የቴክኒክ እና ባህርይ ብቃት ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ መሆኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩንቨርስቲ የተዘጋጀው ይህን ፈተና፦
* ከአዲስ አበባ መሬት ይዞታ፣ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ቢሮ፣
* ከመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ
* ከከንቲባ ፅ/ቤት የተውጣጡ  3 ሺህ 861 አመራር እና ሰራተኞች ተፈትነዋል።

በዚህም ፈተናውን ያለፉት 1 ሺህ 680 ወይንም 44.39 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ተብሏል።

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ፤ ድልድሉ የሚመራበት ደንብ በሚመለከተው አካል ተዘጋጅቶና ፀድቆ የተተገበረ ሲሆን ባለሙያ ከምዘናው 50% በየደረጃ ያሉ ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች 60% የመወዳደሪያ  መስፈርት እንዲሆን ተደርጓል።

በዚህም በሶስቱ የሪፎርም አካል የሆኑት ተቋማት እንደ ከዚህ ቀደሙት 13 ተቋማት ሁሉ ከማእከል አስከ ቅርንጫፍ ክፍለ ከተማ እና ወረዳ ባሉ ፅህፈት ቤቶቻቸው ድልድል እንደሚካሄድባቸውም ቢሮው ጠቁሟል።

በፈተናውም ተገቢውን እውቀት፣ ክህሎትና ስነምግባር አሟልተው የተገኙ ሰራተኞች በተወዳደሩበት ቦታ የመመደብ ተግባር እንደሚከናወን ፤ በውድድሩ ከ30 አስከ 35 በመቶ ከመመዘኛ ፈተና እንደሚያዝ እና ቀሪው በመቶ ደግሞ የስራ አፈጻጸም ፤የስራ ልምድ፤ ስነ ምግባር እና መሰል ነጥቦችን ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
Are you ready to turn your bold visions into reality?

JASIRI is inviting trailblazers and visionaries of 🇪🇹🇷🇼🇰🇪 to join our Talent Investor Program. We're looking for individuals who dare to dream big and aim to be the game-changers in the entrepreneurial world.

If you're passionate about initiating high-impact businesses and are at the cusp of a meaningful entrepreneurial journey, this is for you. Cohort 6 applications are now open.

Visit https://jasiri.org/application and enter a future where your big dreams meet even bigger opportunities.

#DareToDreamBig   #JASIRITalentInvestor
#Innovation    #StartUpCulture
#ApplyNow‌‌
#ኮሬዞን

" ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት #መንታ ልጆቿን አጥታለች  " - ነዋሪዎች

" እኛ አካባቢ ትንንሽ ነገሮችን አጋኖ እና ሌላ አቀላቅሎ የማቅረብ መሠረታዊ ችግሮች አሉ " - አቶ ታደለ አሸናፊ

በአዲሱ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ በሚነሳባቸው ቀበሌዎች የታሰሩ ባለስልጣናት ጭምር ከእስር አለመፈታታቸው እንዲሁም የህክምና አገልግሎት ክፍተት በተለይ ለእናቶች ፈተና መደቀኑ የአካባቢውን ነዋሪዎችን አማሯል።

አንድ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ ነዋሪ ፦
- የዞኑ አመራሮች ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረውን አምቡላንስ ከክላስተሩ
በመቀማታቸው የወላድ እናቶች ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል።

- አምቡላንሱን ከክላስተር ወደ ዞኑ ከተማ በመውሰድ ለአመራሮች አግልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

- ይህ አምቡላንስ ከመወሰዱ ጋር ተያይዞ በቀን 07/05/2016 ዓ/ም አንዲት የአልፈጮ ቀበሌ ነዋሪ የሆነች እናት በወሊድ ምክንያት ወደ አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት መንታ ልጆቿን አጥታለች።

- ይህ ብቻ አይደለም፣ በአካባቢው የህሙማን ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም በቂ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልተቻለም።

የተነሳውን ቅሬታ በተመለከተ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የጤናውን ዘርፍ ጭምር እየተቆጣጠሩ ነው የተባሉት የኮሬ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊና የማኀበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ታደለ አሸናፊ ፦

* በወረዳው የመዋቅር ይገባኛል ጥያቄ ይነሳል፤ ልክ ነው።

* መኪናው ተበላሽቷል ለጊዜው።

* ጋራዥ እንዲገባ ሁሉ ደብዳቤ ተፅፎ ያንን ፕሮሰስ እጨረሰ ነው ያለው። አመራሩ ተነጋግሮ ‘ይሄ መኪና በፍጥነት ጋራዥ ገብቶ መውጣት አለበት’ ተብሎ አቅጣጫ ከተሰጠ በኋላ ሌላ አምቡላንስ እዛው ማዕከል አለ።

* ሌላ እዛው ሁለተኛ አምቡላንስ አለ፤ ያ አምቡላንስ ደግሞ ለአገልግሎት ሂዶ እናቶችንም ሌሎች የታመሙ ሰዎችንም አገልግሎት እየሰጠ ነው።

* የሚባለው ነገር በተባለው ልክ አይደለም።

" ሪፈር ብትባልም አምቡላንስ በማጣቷ ምክንያት መንታ ልጆቿን አጥታለች " የተባሉትን እናት ጉዳይ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፦ " ሰው ሞቷል መባሉ ምናልባት በጤና ችግር ሰው ሊሞት ይችላል። እኛ አካባቢ ላይ ትንንሽ ነገሮችን #አጋኖ ሌላ አቀላቅሎ የማቅረብ መሠረታዊ ችግሮች አሉ። " ሲሉ መልሰዋል።

ሌላው እዛው ሁለተኛ አምቡላንስ አለ የሚለውን የአቶ ታደለ ምላሽ በተመለከተ አንድ የአልፈጮ ቀበሌ ነዋሪ ለቲክቫህ በሰጠው ቃል ፤ " ‘አምቡላንሱን ጋራዥ ነው የወሰድነው’ ስለተባለው፣ አምቡላንሱ ምንም አይነት እንከን አልነበረውም። ‘ምትክ ልከናል’ የሚለውም ውሸት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም  ፤ " ሚዲያን እንደጠላት ነው የሚፈሩት። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ጠይቀናቸዋል። ‘ይህን ወደ ሚዲያ ላይ ከመውጣቱ በፊት የምትልኩልን ከሆነ አምቡላንሷን ላኩልን’ ብለን ከአንዴም አራቴ ጠይቀናል። ‘የምንፈልግ ከሆነ እንሰጣለን፣ የማንፈልግ ከሆነ እንደምትሆኑ ሆኑ’ ብለው ነው ምላሽ ሰጥተው የነበረው " ብለዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ፤ በ15 የፌደራል ሚኒስቴር መ/ቤቶች ላይ ‘አካሄድኩት’ ባለው እና ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም ልኬት/ምዘናና ምክረ ሃሳብ በርካታ ክፍተቶችን አግኝቷል።

በ15 የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ላይ ተደርጓል የተባለው ይህ ምዘና አምስት ጉዳዮችን ማለትም ፦
* ውጤታማነት፣
* ተጠያቂነት፣
* ግልፀኝነት፣
* ፍትሃዊነት
* የሕግ ተገዥነት ላይ መሠረት ያደረገ ነው።

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፦
- የግልፀኝነት፣
- የሕግ ተገዥነት፣
- የፍትሃዊነት ክፍተቶች ሥር የሰደዱ አኳር ችግሮች ናቸው ተብሎ ተወስዷል።

ከአምስቱ በተለይ በሦስቱ ማለትም በግልፀኝነት፣ በሕግ ተገዥነትና በፍትሃዊነት ያለውን አጠቃላይ የጋራ የተጨመቀ ሪፖርት ሲታይ እነዚህ ላይ ጎላ ያሉና አንኳር ችግሮች ታይተዋል።

በዚህም በግልፀኝነት ፦
👉 የአስተዳደር ውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ለተገልጋይ ግልጽ አለማድረግ ፤
👉 የአስተዳደር ውሳኔውን ለተገልጋይ አለመስጠት ፤
👉 ለሕዝብ ይፋ እንዲሆኑ በሕግ የታዘዙትን መረጃ ይፋ ከማድረግ አኳያ የመረጃ ማዕከል አለመኖር፣ 
👉 ያሉ የመረጃ ማዕከል የማይሰሩና አፕዴት የማይደረጉ መሆን፣ እነዚህ መረጃ እንዲሰጥ ለሚቀርብ ጥያቄ ተገቢ ወይም ወቅታዊ ምላሽ አለመስጠት፣
👉 ሪፖርት ለተቋማት አለማቅረብ፣ የግልፀኝነት ክፍተቶች ዋና ዋና መገለጫ ተደርገው ተወስደዋል።

በሕግ ታገዥነት ፦
በተሰጠ ስልጣን ብቻ ኃላፊነት አለመወጣት፣
በመልካም አስተዳደር ላይ ተባባሪ አለመሆን፣
አስገዳጅ የሆኑ የነፃነት ድንጋጌዎችን አለመፈጸም ሌሎች አንኳር ክፍተቶች ናቸው ተብሏል።

ከፍትሃዊነት ጋር በተያያዘ ፦
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ተደራሽ አለመሆን፣
ለሴቶች፣ ህፃናት፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን ቁጥጥርና ክትትል ተገዢ አለመሆን፣ 
መረጃ እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ ሰዎችን አለማስተናገድ፣
የአስተዳደር መመሪያ ሲያወጡ በረቂቅ መመሪያው ላይ በሚደረገው ሕዝበ ውይይት ሁሉም ሰው እንዲሳተፍ ዕድል አለመስጠት በፍትተሃዊነት ረገድ የታዩ አንኳር ክፍተቶች ናቸው።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-29

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

" በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት እንደማይቻል ይታወቅ " - የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር

በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ቢከለከልም " ይሄን አልሰማንም " ያሉ ሰዎች የነዳጅ ተሽከርካሪዎችን ገዝተው ወደ ሀገር እያመጡ ይገኛሉ ተብሏል።

ይህ የተሰማው የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ በዛሬው እለት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው።

የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ ምን አሉ ?

- ማንኛውም የቤት አውቶሞቢል የኤሌክትሪክ ካልሆነ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ መንግስት ውሳኔ አስተላልፏል። ኢትዮጵያ ነዳጅ አታመርትም በጣም ውስን በሆነ የውጪ ምንዛሬ ሃብቷ ነው ከውጭ የምታስገባው።

- ኤሌክትሪክ ኢትዮጵያ ላይ በብዛት ይመረታል እንደገና ደግሞ ከነዳጅ ጋር ሲነፃፀር የኤሌክትሪክ ዋጋ ርካሽ ነው።

- ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት አቀንቃኝ ነች ለዛም በትኩረት የምትሰራ ሀገር ነች፤ የአየር ብክለትን ለመቀነስ ከነዳጅ ከሚሰራው አውቶሞቢል ይልቅ በኤሌክትሪክ የሚሰራው የሚመረጥ ነው።

- በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በዓለም ላይ በስፋት እየተመረቱ ሲሆን በሀገራችን በከተማ አካባቢም ስለሚንቀሳቀሱ ቻርጅ ማድረጊያ መሰረተ ልማትን ማዳረስ የሚቻል ነው።

☑️ ማንኛውም ከውጭ የሚገባ የግል መገልገያ አውቶሞቢል የኤሌክትሪክ ብቻ ነው መሆን ያለበት። በነዳጅ የሚሰራ አውቶሞቢል መግባት አይችልም። " ይህን አልሰማንም ! " በሚል በነዳጅ የሚሰሩ አውቶሞቢሎችን ገዝተው የሚመጡ አሉ። ስለሆነም የነዳጅ አውቶሞቢያል ወደ ሀገር እንደማይገባ ሁሉም ማወቅ አለበት።

Via @tikvahethmagazine

@Tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ቁጠባ+ !
ደንበኞች መደበኛ የቁጠባ ሂሳባቸዉን ከአዲሱ የቁጠባ+ ሂሳብ ጋር በማስተሳሰር ዝቅተኛዉ የቁጠባ መጠንን ከሚቀመጥበት ጊዜ ጋር ተገናዝቦ የተሻለ ወለድ መጠን የሚያገኙበት ሆኖ የተለያዩ የቁጠባ ደረጃዎች ያሉት ነው፡፡
አገልግሎቱ የሚያስገኛቸውን ዝርዝር ልዩ ጥቅሞች እና መለያዎቹን ለመረዳት በአቅራቢያዎ የሚገኝ ቅርንጫፋችን ጎራ ይበሉ ወይም ነፃ የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል መስመር 8397 ላይ ይደውሉ፡፡


#savingplus #savings #BoA #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#ሴጅ_ማሰልጠኛ

የፊታችን ቅዳሜ ጥር 25 2016 ዓ.ም 8ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy and Auditing) ስልጠና ይጀምራል።

👉 100% በተግባር የተደገፈ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ፦ ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://t.iss.one/sagetraininginstitute
Facebook: https://www.facebook.com/sagetraininginstitute
Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Linkedin: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
የሙስሊም ሊቃውንት/ #ዓሊሞች ጉባዔ ከትላንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ  እየተካሄደ ይገኛል።

ለሶስት ቀን ይቆያል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ  ምክር ቤት ሁለተኛው ዓመታዊ የዓሊሞች (የሙስለም ሊቃውንት) ጉባዔ ላይ ፦
- #የትግራይ
- የሶማሊ
- የአፋር
- የአማራ
- የኦሮሚያ
- የጋምቤላ
- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ
- የደቡብ ኢትዮጵያ
- የሐረሪ
- የሲዳማ
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ የዑላማ ምክር ቤቶች እተካፈሉ ይገኛሉ።
                          
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶ/ር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ትላንት ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ፤ " ጦርነት በፈጠረው የሰላም እጦት ችግር ሳቢያ ተለያይተን ከነበርነው የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር ግንኙነታችን ቀጥሎ ዛሬ በአንድ ጉባዔ ላይ መታደማችን የሚያስደስትና የሠላምን ዋጋ ከፍ የሚያደርግ ነው " ብለዋል።

ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ፤ " የሀገራችን ሙስሊም ሊቃውንት በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆነው ዲኑን ለትውልዶች ለማሻገር እና ማኀበራዊ ትስስር እንዲፈጠር ትልቅ ልፋት የሚያደርጉ ታላቅ የሕዝብ ባለውለታና የዲን መሪ ናቸው " ብለዋል።

የሀገር አቀፉ የዑለማ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢና የፈትዋ ዐብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ጀይላን ኸድር በበኩላቸው፣ " የዑለማው በዚህ ዓይነት ትስስር መፍጠር ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ አንድነት ትልቅ ፋይዳ አለው " ብለዋል።

የዑለማው ጉባዔ የሙስሊሙ ችግሮች እና የሚገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ የሚገለጹበት በመኾኑ፣ የሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲዎቾ፣ የየክልሉ የዑለማ ም/ ቤት እና የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ኃላፊዎች በዚህ መድረክ ላይ ተገናኝተው መምከራቸው መድረኩን ታሪካዊ ያደርገዋል ተብሏን።

የጉባዔው ተሳታፊ የሆኑት ክልሎች የየክልላቸውን ተጨባጭ ሁኔታ አስመልክተው ለጉባዔው ሪፖርት ማቅረባቸውን ለማቀው ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊም ሊቃውንት ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባዔ ዛሬም ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ እልምና ጉዳዮች ጠቅላት ምክር ቤት ያገኘው መረጃ ያሳያል።

​NB. የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከቀናት በፊት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጋር የነበረውን አለመግባባት በይቅርታ ፈቶ ወደ ቀደመው ግኝኑነት መመለሱ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#መንገድ

ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ ሌላ አማራጭ ነው የተባለው የአሳይታ- አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ዋና ስራው ተጠናቆ ለትራንስፖርት ክፍት ሆነ።

ወደ ጅቡቲ ለመጓዝ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኘው የጋላፊ መስመር በተጨማሪ ለወደፊቱ ሌላ አማራጭ ሆኖ የሚያገለግለው የአሳይታ-አፋምቦ-ጅቡቲ ድንበር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቆ ለትራንስፖርት አገልግሎት ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አሳውቋል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ስራዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን፣ የትራፊክ ምልክቶች ተከላ ፤ የቀልም ቅብ ስራዎች እና ሌሎች ጥቃቅን ስራዎች ተገባደዋል ተብሏል።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ የመንገድ መሰረተ ልማት ያልነበረ በመሆኑ ህብረተሰቡ በትራንስፖርት  እጦት ምክንያት በእግር እና በግመል ከመጓዝ ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረውም።

መንገዱ በዋናነት ኢትዮጵያን በአሳይታ በኩል ከጅቡቲ ጋር በቅርበት ያስተሳስራል። የኢትዮጵያን የገቢ እና ወጪ ንግድ በማቀላጠፍ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም አሳይታ ከተማን ከአፋምቦ ወረዳ ብሎም በርካታ ቀበሌዎችን በማገናኘት የህዝብ ለህዝብ ትስስሩን ይበልጥ ያጠናክራል ተብሏል።

ይህ አካባቢ የአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ የሚገኝበት በመሆኑ በርካታ ምርቶች የሚመረትበት መስመር ነው። ከእነዚህ ምርቶች መካከል ፦
* ከፍተኛ የጨው ምርት፣
* ጥጥ፣
* ቴምር፣
* ሰሊጥ፣
* ቲማቲም፣
* ሽንኩርት፣
* ብርቱካን፣ ሃባብ እና በርካታ ፍራፍሬዎች ይጠቀሳሉ።

የመንገዱ መገንባት እነዚህን ምርቶች በቀላሉ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ብሎም ወደ ጀቡቲ ለማድረስ ይበልጥ ያግዛል ተብሎለታል።

ከዚህ ባሻገር በመስመሩ የትምህርት ፣ ጤና እና መሰል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶችን በአፋጣኝ አንዲስፋፉ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

በተጨማሪም ይህ መስመር አሁን ላይ ያለውን ሚሌ - ዲቼ ኦቶ-ጋላፊ-ጅቡቲ ወደብ ያለውን መንገድ በ30 ኪሎ ሜትር ያሳጥረዋል።

ወደፊት በአካባቢው ሊመረቱ የሚችሉ የፋብሪካ ውጤቶችን (ስኳር ፣ የስንዴ ዱቄት) ወደ ውጪ ገበያ ለማቅረብ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

አጭር መረጃ ስለ መንገድ ፕሮጀክቱ ፦

- የመንገዱን ግንባታ ለማከናወን የተመደበው 1,600,901,379 (አንድ ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ዘጠኝ ብር) ሙሉ ለሙሉ የተሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው።

- የመንገዱ ርዝማኔ 50.34 ኪሎ ሜትር ነው። የጎን ስፋቱ ትከሻን ጨምሮ በገጠራማ ሥፍራዎች 10 ሜትር ፣ በወረዳ ከተሞች 19 ሜትር እና በዞን 21.5 ሜትር ስፋት አለዉ።

- ፕሮጀክቱ የ3 ድልድዮች ግንባታንም ባካተተ መልኩ ነው የተካሄደው።

- ግንባታውን ያካሄደው ሀገር በቀሉ የስራ ተቋራጭ አሰር ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነው። የማማከርና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ይዲዲያ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንትስ አከናውኗል።

Via ERA

@tikvahethiopia