TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኮኮሜሎን

ካለፈው የታሕሳስ ወር አንስቶ በተለያዩ የውጭ ሀገራት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች እና የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴን የሚቃወሙ አካላት "ኔትፍሊክስ" እንዳይታይ የአድማ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

"ኔትፍሊክስ" ላይ የአድማ ጥሪ እያደረጉ ያሉት ባለፈው ዓመት (እኤአ) መጨረሻ ለእይታ በበቃ በአንድ የልጆች ፊልም ላይ #ግብረሰዶምን ለማስፋፋት ዓላማ ያለው ትዕይንት አለበት በሚል ነው።

ኮኮሜሎን ሌን (CoComelon Lane) በተሰኘው የልጆች ፊልም ኢፒሶድ ላይ አንድ ህፃን ልጅ የዳንሰኛ አጭር ቀሚስ ለብሶ ሲጨፍር መታየቱ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን ተቺዎች ይህ የተደረገበትን መንገድ "መጥፎና ሰይጣናዊ" ሲሉ ነው የገለጹት።

CoComelon lane ለልጆች የተሰራ የNetflix ተከታታይ ፊልም ነው። በኃላም ከ1 ወር በፊት በዩትዩብ ላይ ተጭሮ በሚሊዮኖች ታይቷል።

በዚሁ ፊልም በሲዝን 1፤ ኢፒሶድ 8 ላይ አንድ ኒኮ የተባለ ህፃን ልጅ (2 አባቶች እንዳሉት ተደርጎ የተገለፀ-ይህ ግብረሰዶማውያን አባቶች እንዳሉት የሚያሳይ ተደርጎ ተወስዷል) ከቤተሰቦቹ ጋር ለሚነሳው ፎቶ ምን መልበስ እንዳለበት ለመወሰን ተቸግሮ ይታያል።

በዚህም ወቅት የኒኮ አባቶች ተደርገው የተሳሉት ሁለቱ ገፀባህርያት " ስለ አንተ የምናውቀው ነገር ቢኖር ተነስተህ መደነስ እንደምትወድ ነው " እያሉ ይዘፍናሉ።

ከዚያም ኒኮ የዳንሰኛ አጭር ቀሚስ ለብሶ እና ዘውድ ከአናቱ ላይ አድርጎ መደነስ ይጀምራል።

የኒኮ አባት ተብሎ ከተገለፁት አንዱ፤ " ምን መምረጥ እንዳለብህ እርግጠኛ ካልሆንክ ማድረግ የምትፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ አስብ። አንተ እራስህን ብቻ ሁን " እያለ ይዘፍንለታል።

ከዚያም ኒኮ "እኔ ራሴን ብቻ ልሁን?" ብሎ ይጠይቃል ካዛም አባት ተብየው ገፀባህሪ " አዎ! " ሲል ይመልስለታል።

ይህ ንግግር ህፃኑ ልጅ "የማንም ተፅእኖ ሳይኖርብህ #በፈለከው_መንገድ እራስህን ሁን" የሚል ይዘት ያለው መልዕክት ለማስተላለፍ እንደሆነ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ተቆርቋሪች ይገልጻሉ።

ትዕይቱን "ጥፎና ሰይጣናዊ" ሲሉም ገልጸው ዋነኛው አላማው ህፃናትን ማበላሸት፣ ምንም በማያውቁ ህፃናት ላይ ግብረሰዶምን ማስፋፋት ነው ብለዋል።

የግብረሰዶማውያን እንቅስቃሴና ሰዎቹን አጥብቀው የሚያወግዙት እነዚህ ተቆርቃሪዎች፤ "ትዕይንቱ ህፃናት በለጋ እድሜያቸው ስለግብረሰዶም እና ስለፆታ ማስቀየር "እንዲዘጋጁ" እያደረገ የሚሄድ ነው ብለውታል።

በዚህ ምክንያት ይህንን ለህፃናት እንዲታይ እያሰራጨው "ኔትፍሊክስ"ን ሰዎች እንዳያዩ የአድማ ጥሪ እያቀረቡ ናቸው።

ምንም እንኳን ፊልሙ በህዳር ወር ውስጥ የወጣ ቢሆን ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ተቆርቋሪዎች ወላጆች ልጆቻቸውን ከመሰል አደገኛ ይዘት ካላቸው መልዕክቶች እንዲጠብቁ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ይህ "CoComelon" የተባለውና ለህፃናት በተለያዩ ርዕሶች እየተዘጋጀ የሚቀርበው ካርቱን ፊልም በዓለም አቅፍ ደረጃ ብዙ እይታ ያለው ነው። ብዙ ወላጆችም ለልጆቻቸው ይከፍቱላቸዋል።

ወላጆች ዘመኑ ያለበትን ሁኔታ በመረዳት ልጆች እንዲያዩ የሚያደርጉትን ማንኛውንም ነገር በቅድሚያ መገምገም፣ ጥሩነው መጥፎ፣ ከጀርባ ምን ይዟል የሚለው መመርመር አለባቸው። ዝም ብሎ ልጅ ስላስቸገረ ስልክ መስጠትንም ተገቢ አይደለም።

ከዚህ ባለፈ ልጆች በሃይማኖት ተኮትኩተው ፣ የማህበረሰቡን ባህል፣ ስርዓት አክብረው በትምህርታቸው፣ በሃይማኖታቸው ጠንካራ ሆነው እንዲያድጉና እንዲኖሩ በተገቢው አቃጣጫ መምራት ይጠበቅባቸዋል።

ኢትዮጵጵያውያን የቴክ ሰዎችም የሀገራችን ህፃናት ወደሌላ እንዳይሳቡ በሀገር ባህል፣ ስርዓት የተቀረፁ የማስተማሪያ ካርቱን ፊልሞችን በብዛት ማዘጋጀት አለባቸው። #ቲክቫህ

@tikvahethiopia
#ትግራይ #ኢሮብ

በትግራይ ክልልና ኤርትራ አዋሳኝ ድንበር ላይ የሚኖረው የኢሮብ ብሔረሰብ ተወላጆች ፣ የሚኖሩባቸው አካባቢዎች ለሁለት በመከፈላቸው ማኅበረሰቡ ለድርቅ ፣ ለስደትና ለተለያዩ በደሎች እየታገለጠ ይገኛል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

- ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ አሁንም ድረስ ከብሔረሰቡ 8 ቀበሌዎች ውስጥ ፦
* እንዳልገዳ፣
* ወርዓትስ፣
* ዓገረለኩማና ዳያዓሊቴና በተባሉ 4 ቀበሌዎች የኤርትራ ሠራዊት ይገኛል።

- ኢሮብን በዓዲግራት በኩል ከተቀሩት የትግራይ ክልል ከተሞች ጋር የሚያገናኘው መንገድ አገልግሎት አይሰጥም።

- በወረዳው ከባድ ረሃብ ነው ያለው። የዕርዳታ እህል ለማግኘት ምዝገባ አለ። ግን በስንት አንዴ የምግብ ድጋፍ ቢገኝም የተወሰነ እንጂ የሰውን ሕይወት ሊያተርፍ የሚችል ነገር አይገኝም።

- በጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙት 4 ቀበሌዎች ትምህርት ተቋርጧል። በተቀሩት የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጥሯቸው ባሉት አራቱ ደግሞ ሕፃናት #በኤርትራ_ካሪኩለም እንዲማሩ እየተደረገ ነው።

- ከጦርነቱ በፊት የብሔረሰቡ ቁጥር 32 ሺሕ ነበር። አሁን ኅብረተሰቡ በተለይ ወጣቱ ወደ ስደት እየሄደና ብሔረሰቡም በተደራረቡበት ችግሮች ምክንያት ቁጥሩ እየተመናመነ እየጠፋ ነው።

የኢሮብ ወረዳ አስታዳዳሪ ኢያሱ ምስግና ምን አሉ ?

* ወደ 60 በመቶ የሚሆነው የብሔረሰቡ ግዛት በኤርትራ ሠራዊት ሥር ነው። ሁለቱን ቀበሌዎች ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሯቸው ይገኛል። የተቀሩት ሁለቱ ውስጥ ደግሞ በከፊል ሰፍሮ ይገኛል።

* ከዓዲግራት ወደ ኢሮብ የሚወስደው መንገድ በኤርትራ ሠራዊት ወድሟል። አሁንም በሠራዊቱ ተዘግቶ ይገኛል። ይህ ዋና መንገድ በመዘጋቱ ትራንስፖርት ችግር ነው። ቀበሌዎችን ውስጥ ለውስጥ ለማገናኘት ከጦርነቱ አራት ዓመታት በፊት ቀድሞ ግንባታቸው ተጀምሮ ባልተጠናቀቁ መስመሮች ነበር የሚኬደው አሁን ይኼም አስቸጋሪ እየሆነ ነው።

* ኢሮብ ወረዳ ዘንድሮ ከባድ ድርቅ ያጋጠመው አጋጥሞታል። እስካሁን ድረስም ምንም ዓይነት ዝናብ አልተገኘም። የምግብና የውኃ እጥረት በሰውና በእንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው።

* ዕርዳታ በሰብዓዊ ድርጅቶችና አልፎ አልፎ በመንግሥት ይቀርብ ነበር። በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት የምግብ ዕርዳታ ካቀረበ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኖታል። በወቅቱ ድጋፉ ለአራት ሺሕ ሰዎች ነበር የቀረበው።

* መንግሥትም አልፎ አልፎ የሚልክልን የአደጋ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ነበር፡፡ እሱም ከጊዜው ቆይታ አንፃርና ከሕዝቡ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን አልነበረም።

* የመድኃኒት እጥረት ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። በረሃብ አደጋ ውስጥ ወድቀው ያሉ ብዙ ታማሚዎች የመድኃኒት ዕጦቱ ተደምሮ ሕይወታቸውን እያሳጣቸው ነው።

* የኢሮብ ብሔረሰብ የድርቅ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን እንደ ብሔረሰብ እየጠፋ ነው። ቋንቋው፣ ባህሉና ወጉ ተጠብቆ በራሱ አካባቢ መኖር ሲገባው በስደት፣ በረሃብ፣ በድርቅና በጠላት ተበታትኖ እንዳይጠፋ ዓለም አቀፍ ሕግጋት መተግበር አለባቸው፣ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነትም መከበር አለበት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሪፖርተር ጋዜጣ መውሰዱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia
#FoodandAgricultureOrganization #UN

የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ  የከበረውን የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያ ተሸለሙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህ ሽልማት የተሰጣቸው ዛሬ በጣልያን፤ ሮም ከተማ ነው።

በተባበሩት መንግሥታት የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) ፤ ሮም ውስጥ ባሰናዳው ዝግጅት ዶ/ር ዐቢይ ፤ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያደረጉ ላለው ጥረት የከበረውን አግሪኮላ ሜዳልያ እንዳበረከተላቸው ተነግሯል።

የፋኦ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኩ ዶግዩ ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፋኦ ከፍተኛ ሽልማት ለሆነው አግሪኮላ ሜዳልያ ሽልማት በመብቃታቸውን " እንኳን ደስ አልዎት ! " ብለዋቸዋል።

ይህ ሽልማት መሪዎች እና ሌሎችም የዓለማችን እውቅ ሰዎች የምግብ ዋስትናናን ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ድህነትን ለመቀነስ ለሚያደርጉት የተሳካ ጥረት የሚሰጥ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም የአግሪኮላ ሜዳሊያ ለጠ/ ሚኒስትሩ እየተበረከተው ፦
* በኢትዮጵያ ገጠርና ኢኮኖሚ ልማት ላይ ላበረከቱት አስተዋፅኦ
* በተለይም " በስንዴ፤ ምግብ እራስን መቻል ፕሮግራም " ባደረጉት የግል ድጋፍ
* በኢትዮጵያ አረንጓዴ ሌጋሲ (Green Legacy) ስራ መሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈ ዋና ዳይሬክተሩ " ባለፉት 5 አመታት ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለችውን አስደናቂ እድገት ተመልክቻለሁ " ማለታቸው ተነግሯል።

ይህ ሊሆን የቻለው " በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተሰጡ ውጤታማ፣ ተጠያቂነት ያለውና የተረጋጋ አመራር ነው " ያሉት የፋኦ ዋና ዳይሬክተር ፤ ተመልክቼዋለሁ ያሉት እድገት የተመዘገበው " ባለፉት ዓመታት በነበሩ አስቸጋሪ ሀገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ነው ፤... ይህ ደግሞ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን እንደ አህጉር ለአፍሪካም ይልቅ መልዕክት ነው " ማለታቸው ተሰምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው የተሰጣቸውን ሽልማትና እና እውቅናን ተከትሎ ባሰራጩት መልዕክት ምስጋና አቅርበው ፤ " ከፍ ያለ ጠቀሜታ ባላቸውና የኢንደስትሪ ግብዓት በሆኑ የግብርና ምርቶች ላይ ማተኮራችን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያስገኘልን ይገኛል። የምግብ ሉዓላዊነት ጉዟችንን በፅናት እናስቀጥላለን " ብለዋል።

የፋኦ አግሪኮላ ሜዳልያን በተሸለሙበት ወቅት የፋኦ አመራሮች፣ ዲፕሎማቶች፣ እና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ነበር ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፋኦ ድረገፅ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
Africa-Italy

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ጣልያን፣ ሮም ገብተዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ሮም ይገኛሉ።

የሀገራት መሪዎች ፣ እና የመንግሥታት ተወካዮች በሮም እየተሳብሰቡ የሚገኙ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ እና ነገ ለሚካሄድ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ነው።

የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ግንኙነታቸው ሻክሯል የተባለው ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መሪዎቻቸው በአንድ መድረክ በአካል ሲገኙ ይህ የመጀመሪያው ይሆናል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እና ሶማሌለንድ መካከል ከተፈረመው ስምምነት ጋር በተያያዘ ስለ " ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ " ግንኙነት እንዲሁም ስለ " ሱዳን ጦርነት " ለመምከር በኡጋንዳ ፤ ኢንቴቤ በተሰባሰበው የኢጋድ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ዶ/ር ዐቢይ ሳይገኙ ቀርተዋል።

ከአንድ ቀን በኃላ ደግሞ በዛው በኡጋንዳ ፣ ካምፓላ ትላንት በተካሄደው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (NAM) ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ላይ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በአካል ሲገኙ ፤ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ አልተገኙም ነበር።

የአሁኑ የሮም የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ሁለቱንም መሪዎች በአካል በአንድ መድረክ እንዲገኙ ያደርጋል።

መሪዎቹ ከጉባኤው ጎን ለጎን ስለሁለቱ ሀገራት ግኝኑነት የተናጠል ውይይት ያዳርጉ እንደሆነ የሚታወቅ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TPLF " ላለፉት 39 ቀናት ያካሄድኩትን ሰብሰባ በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት አጠናቅቃለሁ " - የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ " ለ64 ቀናት ስብሰባ ተቀምጠን ህዝብን የሚረባ ጠብ ያለ ቁምነገር የለም " - የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜደንት ጌታቸው ረዳ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ፤ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ ላለፉት 39 ቀናት ከፀጥታ ሃይሎች ፣ ከተተኩ…
# Update
 
ህወሓት ለ41 ቀናት ፤ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዚደንት ከ64 ቀናት በላይ መካሄዱ የሚገልፁት ረጅም ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁ ፍንጭ ተሰጠ።

ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጥር 19/2016 ዓ.ም አመሻሽ " ኢንስቲትዩት ግርዓልታ ንመፅናዕትን ስልጠናን " ከትግራይ ህዝባዊ ግንኙነቶች ጉባኤ በመተባበር ባዘጋጀው የሁለት ቀን ውይይት ማጠቃለያ ተገኝተው እንዳሉት ድርጅታቸው ህወሓት ያካሄደው የግምገማ ፣ ሂስና ግለሂስ መድረክ ዛሬ መጠቃለሉን ፍንጭ ሰጥተዋል። 

ፕረዚደንቱ ዛሬ በመድረኩ በመገኘት ባደረጉት ንግግር ስብሰባው መጠናቀቁን የሚመለከት ፍንጭ ሰጥተዋል።

በተሰብሳቢዎቹ መካከል መግባባት መደረሱን፣ ህዝቡን ወደ ተሻለ የለውጥ ጉዞ መምራት የሚችል ማስተካከያ መደረጉንም ተናግረዋል።

ፕረዚደንቱ " ተደረሰ " ስላሉት መግባባትና ማስተካካያ ዝርዝር መረጃ እንዳልሰጡ ከቦታው የዘገበው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።  

#TikvahFamilyMekelle
                   
@tikvahethiopia            
#ትግራይ

ትንሳኤ 70 እንደርታ የተሰኘው ፓርቲ ፤ በትግራይ ከ1 ሚሊዮን በላይ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።

ፓርቲው አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ፦
* የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር፣
* የዜጎች የዓመታት ስቃይ እንዲያበቃ፣
* የተፈጠሩ አለመግባባቶች ሕገ መንግሥታዊ በሆነ አግባብ እንዲፈቱ መንግሥት ግዴታውን እንዲወጣ አሳስቧል።

ፓርቲው የፕሪቶሪያው ስምምነት አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት የፈጠረ፣ ተስፋ የሰጠ ቢሆንም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩ ምክንያት ከ1 ሚሊዮን በላይ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቄያቸው ባለመመለሳቸው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ ብሏል።

የመሬት ወረራ በተለይም በመቀሌ 70 እንደርታና ራያ አካባቢ በልማት ስም በማይረባና ያለምንም ካሳ ከሕዝቡ ቀምቶ ለጥቅመኞች የማስተላለፍ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ይህ ሳይውል ሳያድር እንዲቆም ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው በክልሉ ባለ የጸጥታ ችግር ፦
- ሕዝብ በሰላም ወጥቶ ለመግባት እንደሚቸገር፣
- የሕዝብና የመንግሥት ንብረት እንደሚዘረፍ ፣
- ሴቶችም በጠራራ ፀሐይ የሚደፈሩበት እና መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሕዝቡን ከጦርነት ባልተናነሰ ከባድ ስቃይና መከራ ውስጥ እንደጣለው ገልጿል።

በክልሉ ሕዝቡ ባጋጠመው በድርቅ የማለቅ አደጋ በተጋረጠበት ጊዜ ሕወሓት ማለቂያ በሌለው ስብሰባ መቀመጡም ከሥልጣን ውጪ ሕዝባዊነት የሌለው ነው የሚል ትችትንም ፓርቲው ሰንዝሯል።

Via @thiqamediaeth
TIKVAH-ETHIOPIA
Africa-Italy የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ጣልያን፣ ሮም ገብተዋል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድም ሮም ይገኛሉ። የሀገራት መሪዎች ፣ እና የመንግሥታት ተወካዮች በሮም እየተሳብሰቡ የሚገኙ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ዛሬ እና ነገ ለሚካሄድ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ ነው። የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ከተፈረመ…
ፎቶ ፦ የአፍሪካ-ጣልያን ጉባኤ በጣልያን፣ ሮም ከተማ እየተካሄደ ሲሆን የበርካታ ሀገራት መሪዎችና የመንግስት ተወካዮች ጉባኤውን እየተካፈሉ ይገኛሉ።

በዚህ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙት መሪዎች መካከል፦
* የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣
* የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
* የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ
* የኬንያው ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶ ይጠቀሳሉ።

የሁለት ቀኑ የአፍሪካ-ጣሊያን የመሪዎች ጉባኤ በተለያዩ ዘርፎች ማለትም በኢኮኖሚና መሰረተ ልማት፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢነርጂ ደህንነት እና ሽግግር እንዲሁም በሙያ ስልጠናና በባህል ዘሪያ እኩል አጋርነትን መፍጠር ላይ ያተኩራል።

#Africa #Italy

@tikvahethiopia