በመኪና የታገዘ ዝርፊያ . . .
እኚህ በፎቶው የምትመለከቷቸው ግለሰቦች፦
1. ናትናኤል አለሙ
2. አብደላ ሰኢድ
3. ቢያንያም መዝገበ አዲስ አበባ፣ ካዛንችስ ጠማማ ፎቅ አካባቢ ጉብኝት ሲያደርጉ ከነበሩ የውጭ ሀገር ሰዎች አይፎን ስልክ ቀምተው በመኪና (ከላይ በፎቶው በምትታየው ላዳ) ለማምለጥ ሲሞክሩ በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በህብረተሰቡ ርብርብ እጅግ ከፍንጅ የተያዙ ናቸው።
አንደኛው ስልክ ቀሚ ፣ ሁለተኛው የተሽከርካሪውን በር ከፍቶ ሲጠባበቅ የነበረ ፣ ሶስተኛው ደግሞ ሹፌር ልክ ግብረአበሮቹ ወደመኪናው እንደገቡ በፍጥነት ለማምለጥ ጥረት ያደረገ ነው።
እንዲህ አይነት ተመሳሳይ የሆነ በመኪና የታገዘ የወንጀል ተግባር ከወራት በፊት " ቦሌ ሩዋንዳ " ጋር ተፈፅሞ እንደነበር አንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ገልጿል።
በወቅቱ ድርጊቱ የተፈፀመው ምሽት 4 ሰዓት ገደማ ነበር " በቶዮታ ወያኔ ዲኤክስ " መኪና የነበሩ በቁጥር 4-5 የሚሆኑ ዘራፊዎች አንድ ሰው መንገድ ላይ አስቁመው በስለት እና በመሳሪያ አስፈራርተው ስልክ እና ገንዘብ ዘርፈው በፍጥነት መኪናውን እያሽከረከሩ ተሰውረዋል።
ከዛ በኃላ ዘራፊዎቹ ይያዙ አይያዙ የሚታወቅ ነገር የለም። የግል ተበዳይ ንብረትም አልተገኘም።
በፊት በፊት ዝርፊያ ሲፈፀም የሚሰማው በእግር ፣ ጨለማን ተገን በማድረግ ነበር አሁን አሁን ላይ ታርጋ ጭምር የለጠፈ መኪና በመጠቀም በእግሩ የሚሄድን ሰው በስለት በማስፈራራት፣ አንዳንዴም ሊፍት እንስጣችሁ በሚል ሆኗል።
እናተስ መሰል ነገር አጋጥሟቹ ይሆን ? ወይስ ያጋጠመው ሰው ታውቁ ይሆን ? ዝርፊያ ሲፈፀምባቸው የነበሩ መኪኖችን ትለይዋቸው ይሆን ? በ @tikvahethmagazine ላይ አጋሩን !
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DStv
📣 ሰምተዋል?
በማንኪያ ሲሉ በጭልፋ ፤ በጭልፋ ሲሉ በአካፋ!
👉 ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ድረስ ከሚጠቀሙት ፓኬጅ ከፍ ካሉ በእኛ ወጪ ወደ ቀጣዩ ትልቅ ፓኬጅ ለአንድ ወር ከፍ ይላሉ!
⏰ ይህ አገልግሎት ክፍያ ከፈፀሙ ከ48 ሰዓት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
*ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው።
የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን
የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇👇👇
https://bit.ly/2WDuBLk
#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #StepUp

ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይከተሉ!
=====================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ስምና አርማ በመጠቀም በሚከፈቱ ሀሰተኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎችን በማሰራጨት የሌብነት ተግባር የሚፈፅሙ አጭበርባሪዎች አሉ፡፡
በመሆኑም የባንኩን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ብቻ በመከተል ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ ያግኙ፤ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ!
የባንኩ ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች፡
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• YouTube፡- https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia
• LinkedIn፡- https://www.linkedin.com/company/commercialbankofethiopia
• Twitter፡- https://twitter.com/combankethiopia
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
• Instagram፡- https://www.instagram.com/commercialbankofethiopia/
• tiktok:- https://www.tiktok.com/@combankethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ ከላይ የሚታዩት ተጠርጣሪዎች ተሽከርካሪ በመጠቀም እየተንቀሳቀሱ የማታለል ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ግለሰቦች እንደሆኑና አሁን ላይ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።
እንደ ፖሊስ መረጃ ፤ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የሰሌዳ ቁጥር ኮድ " 3-B48631 አ.አ " በሆነ ተሽከርካሪ ወንጀል ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ናቸው።
ግለሰቦቹ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው 6 ኪሎ ዩኒቪርሲቲ አንደኛ በር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በፈፀሙት ወንጀል ነው የተያዙት።
ተጠርጣሪዎቹ ባንኮች ላይ ትኩረት አድርገው ሲንቀሳቀሱ የነበር ሲሆን ፤ በዚሁ አካባቢ በሚገኝ አንድ የባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ አንዱ ተጠርጣሪ ስራ አስኪያጁን የNGO አካውንት ለመክፈት እንደፈለገ ይነግረዋል።
ስራ አስኪያጁም አስፈላጊ መስፍቶችን ይነግረዋል ፤ በኃላም ፎቶና ሌሎች መስፈርቶችን አሟልቶ እመለሳለሁ ይላል። ቀጠል አድርጎ ድርጅታቸው በቅናሽ የሚሸጣቸው 53 ኢንች ሁለት ቴሌቪዥኖች ስላሉ የሚገዙ ከሆነ ይውሰዱ ሲል ይናግረዋል።
ስራ አስኪያጁ ቴሌቪዥን መግዛት እንደሚፈልግ ፤ እጁ ላይ ግን ያለው 3 ሺህ ብር እንደሆነና 12 ሺህ ተበድሮ 15 ሺህ ብር መስጠት እንደሚችል ይገልጻል። በዚህ ወቅት ተጠርጣሪው ችግር የለም ሌላ ጊዜ ቀሪውን ገንዘብ ወስዳለሁ ይላል።
ስራ አስኪያጁም ብሩን ሰጥቶ ቴሌቪዥኑን ለመረከብ አንድ የራሱን ሰው አብሮ ይልካል። ልክ ከባንክ እንወደጡ ከላይ ያለችው መኪና (የግብረአበሩ) ውስጥ ይገባሉ። ጥቂት ተጉዘው 6 ኪሎ ሲደርሱ ተጠርጣሪው ብሩን የያዘውን ሰው ብሩን ስጠኝ ብሎ ይቀበላል።
ሹፌሩ (ግብረአበር) መኪናውን ሲያቀዘቅዝ በሩን ከፍቶ ቴሌቪዥንኑን ሊያመጣ የተላከውን ሰው ወርውሮ ይጥለውና በፍጥነት ይነዱታል።
በወቅቱ በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የወንጀል መከላከል ስራ ሲሰሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት በደረሳቸው ጥቆማ ወንጀሉን ፈፅሟል የተባለውን ግለሰብ ከነ ግብራበሩ እና ሲጠቀሙበት ከነበረው መኪና ጋር ተከታትለው በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋል።
#AddisAbabaPolice

“ 12 የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ተገድለዋል ” - የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበር
“ እውነት ነው። እኔ እንደ ባለሙያ ሁለት ሰዎች የተመቱ አይቻለሁ ” - የዓይን እማኝ የጤና ባለሙያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በትፋቴ ቀበሌ መንግሦት “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው ታጣቂዎች በድንገት አደረሱት በተባለ ጥቃት 12 የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻዎች መገደላቸውን የዞኑ ሆስፒታል ባለስልጣንና የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያ፣ የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበርና የዓይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
የዓይን እማኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት፣ 9ኙ ሚሊሻዎች እሬሳቸው ሆስፒታል አድሮ መሸኘቱን፣ 3ቱ ደግሞ በምዕራብ ጉጂ ዞን በጋላና አባያ ወረዳ ኤርጋንሳ ወይም ፃልቄ ቀበሌ መመለሳቸውን ነው።
ሚሊሻዎች ተገደሉ የሚባል መረጃ ደርሶናል እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምለሽ በኮሬ ዞን የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ኪታሞ በሰጡት ቃል፣ “እውነት ነው ሚሊሻዎች ተገድለዋል” ብለዋል።
“ፃልቄ የሚባል አካባቢ (በገዳና ፃልቄ መካከል) ላይ 12 የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ተገድለዋል” ያሉት ሊቀመንበሩ፣ ድርጊቱ የተፈጠረው “ሰኞ ዕለት (ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም) ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
አክለው ፤ “ሌሎች ታካሚዎችም አሉ። እኔ ከእነርሱ ጋር አይደለም የቆጠርኩት። የሞቱ ብቻ 12 ናቸው” ብለዋል።
ጥቃቱን ያደረሱት የ “ሸኔ” ታጣቂዎች ናቸው እንዴ ? ተብለው ሲጠየቁም፣ “አዎ የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ከሸኔ ጋ ተገናኝተው” ብለዋል።
ስለ ጉዳዩ #ማረጋገጫ እንዲሰጡን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኬሌ ከተማ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ በለጠ በበኩላቸው ፤ “ እኛ ጋ በእርግጥ የህክምና አገልግሎት ለመቀበል የመጡ 2 በጥይት የተመቱ ነበሩ። ከዚያ ወጪ ዘጠኝ እሬሳ እንደመጣና በዚሁ እንዳለፈ ነው የምናውቀው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
“ መረጃው የደረሰኝ ሁለቱ ተወግተው መጥተው አገልገሎት አግኝተው እንደሄዱና ዘጠኙ እሬሳ ግቢ ገብቶ (ለማሳደር ከምሽቱ 3 በኋላ ነው ያመጧቸው” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ “አሁን ያሉበትን ደረጃ ባናውቅም ሁለቱ ታክመው ነው የሄዱት” ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ስለ ጉዳዩ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ እንደሻ በበኩላቸው፣ “እውነት ነው። እኔ እንደ ባለሙያ ሁለት ሰዎች የተመቱ አይቻለሁ። ታክመው ለተጨማሪ ህክምና ሂደዋል ጠዋት። የእነርሱ አመራርሮችም (የታካሚዎቹ) መጥተው ነበር” ብለዋል።
አክለውም፣ “የእኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነው። የእነርሱ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ስለሆነ በአቅራቢያ በሚገኘው ዞን መጥተው ነበር ወደ እኛ፣ ሲታከሙ አድረው ሂደዋል። የተመቱት የኦሮሚያ ጉጂ ዞን ሚሊሻዎች ናቸው” ሲሉ አስረድተዋል።
ዘገባውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

#ኢትዮጵያ
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዘንድሮ በመላ ሀገሪቱ የ " ኬጂ " ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋ እየተማሩ አይደለም።
የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች " ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ… " ን በዜማ መቁጠር፣ " ኤ ፎር አፕል፣ ቢ ፎር ቦል… " እያሉ ቃላት መመሥረትም አቁመዋል።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ " ስፖክን ኢንግሊሽ " እና " ኢንግሊሽ ሊትሬቸር " ከ " ኬጂ " ተማሪዎች የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ተሰርዘዋል።
እንደ ቀድሞው በአማርኛ ሂሳብ፤ በእንግሊዝኛ " ማትስ " እያሉ የቁጥሮችን አጠራር በሁለት ቋንቋ መሸምደድም ቀርቷል።
የዘንድሮ የ " ኬጂ " ተማሪዎች ለአካባቢ ሳይንስ እና ለ " ጄኔራል ሳይንስ " ሁለት ደብተር አይዙም።
በአራት ዓመታቸው " ነርሰሪ " የሚገቡት ህጻናት፣ በ6 ዓመታቸው ከ " ዩ ኬጂ " ሲመረቁ የሚያውቁት ብቸኛ የፊደል ገበታ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን እንዲሆን ተደርጓል።
ልጆችን እንግሊዝኛ በማስተማር ተመራጭ የሆኑት የግል መዋለ ህጻናት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁሉንም ትምህርት የሚሰጡት በአካባቢው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ብቻ ነው።
በአዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር አሠራር መሠረት ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋን እንደ አንድ ትምህርት መማር የሚጀምሩት #አንደኛ_ክፍል ሲደርሱ ነው።
ከዚህ ዓመት ጀምሮ መተግበር የጀመረው ሥርዓተ ትምህርት ህጻናት የሚማሩትን ትምህርት በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች (ሰብጀክት) አይከፋፍልም።
የኬጂ ተማሪዎች እንደ ቀድሞው ሂሳብ፣ አማርኛ ወይም አካባቢ ሳይንስ የሚባሉ የትምህርት ዓይነቶች አይኖሯቸውም። በትምህርት አይነቶች ፋንታ ህጻናቱ የሚማሩት " ጭብጦችን " ነው።
ለምሳሌ፤ የመጀመሪያ ዓመት የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ስድስት ጭብጦችን ይማራሉ። ከእነዚህ ጭብጦች ውስጥ፦
* ስለ እኔ፣ ስለ ቤቴ እና ስለ ቤተሰቦቼ
* ትምህርት ቤቴ እና አካባቢዬ የሚሉት ይገኙበታል።
የኬጂ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከሚማሯቸው ጭብጦች ውስጥ ደግሞ ፦
* ዋሊያ
* ህዋ
* ተክሎች እና መጓጓዣ ተጠቃሽ ናቸው።
በአዲሱ ካሪኩለም መሠረት ህጻናቱ እንደ ቀድሞው አብዛኛውን ጊዜያቸውን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለው ከሰሌዳ እና ከደብተር ጋር እንዲፋጠጡ አይደረግም።
ዘንድሮ የኬጂ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ዋነኛ መንገዶች ጨዋታ፣ መዝሙር እና ተረት ናቸው።
በአዲሱ ካሪኩለም የኬጂ ተማሪዎች እንግሊዝኛ እንዲማሩ አይደርግም። በእንግሊዝኛ ምንም ነገር የለም። ሁሉም ነገር በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል።
የኬጂ ትምህርት ይዘት መቀነስ ያላስደሰታቸው ወላጆችም ያሉ ሲሆን ተማሪዎች ከአቅማቸው በታች እንዲማሩ እያደረገ ነው ብለዋል።
በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶችም ከወላጆች ቅሬታ እየተቀበሉ መሆኑን የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች አሠሪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ጣሰው አሳውቀዋል።
የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ካሪኩለሙ በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት የትምህርት ይዘቱ መቀነሱን እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መውጣቱን በተመለከተ ማኅበሩ ተቃውሞ አስተያየት መስጠቱንም አስታውሰዋል።
የቅድመ አንደኛ ሥርዓተ ትምህርትን ካዘጋጁ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ጃለታ ፤ " ቤተሰብ ልጁ እንግሊዝኛ ከቻለ፣ ፊደል ከቆጠረ ወይም መደመር ከቻለ ተምሯል፣ አድጓል ብሎ ያስባል። በህጻናት ደረጃ ትምህርት እርሱ አይደለም " ብለዋል።
ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/BBC-AMAHRIC-01-24
Credit - #BBCAMAHRIC

#ኤርትራ
ኤርትራ የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ቤርቦክን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረን አውሮፕላንን ከአየር ክልሏ ማስወጣቷ ተነግሯል።
የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌላ ባየርቦክ ትላንት እንዳስታወቁት፤ ወደ ጂቡቲ ሲጓዝ የነበረው የጀርመን መንግስት አውሮፕላን ያለ እቅድ ሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዱን ገልጸለዋል።
ይህ የሆነ በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማለፍ ፍቃድ ባለማግኘቱ እንደሆነም አስታውቀዋል።
ሚኒስትሯ በ3 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ለ3 ቀናት ጉብኝት ለማድረግ በጉዞ ላይ የነበሩ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውም ጂቡቲ ነበረች።
ሚኒስትሯ ፤ ያለ እቅድ በሳዑዲ አረቢያ ለማረፍ መገደዳቸው በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ያለውን አለመረጋጋት ያመለክታል ብለዋል።
ትላንት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው ለማደር የተገደዱት ሚኒስትሯ ዛሬ በጅቡቲ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል።
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ " አውሮፕላኑን በኤርትራ የአየር ክልል ላይ ለማብረር ፈቃድ እንዳልተሰጠው ያወቅነው ትናንት ጠዋት ከበረራው ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ ነበር " ብሏል።
አውሮፕላኑ #በበረራ_ላይ_እያለ ፈቃዱን ያገኛል ተብሎ በመወሰኑ ወደዚያ መሄዱንም ገልጿል።
ከቤርቦክ ጋር የተጓዙት ልዑካን ፤ አውሮፕላኑ እየበረረ ፈቃድ ማግኘት እንግዳ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
ቤርቦክን ፤ የሱዳን ጦርነት ጉዳይ እና የቀይ ባህር የመርከብ መንገድ ጉዳይ ትኩረት አድርጓል የተባለው የምሥራቅ አፍሪቃ ጉብኝታቸውን ነገ በደቡብ ሱዳን ያጠናቅቃሉ ተብሏል።
#AlAinNews #DW

" ከሶማሊያ ጋር የመዋጋት ፣ የመጣላት ፍፁም ፍላጎት የለንም " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ጋር #የመዋጋትም ሆነ የመጣላት ፍላጎት እንደሌላት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ዶ/ር ዐቢይ ይህን ያሉት ለፓርቲያቸው ማዕከላዊ ኮሚቴ ባቀረቡት ገለፃ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " የምንከተለው የዲፕሎማሲ ጉዟችን ክብርንና ጥቅምን ማስከበር ላይ ያተኮረ ነው። " ብለዋል።
" ሶማሊያ ከማንም በላይ የኢትዮጵያ ወንድም ዘመድ ጎረቤት ናት፤ ባለፉት 10 ዓመታት በሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በሶማሊያ ውስጥ የሶማሊያ ሰላም ለማስከበር የህይወት ዋጋ ከፍለዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።
" ማንም ሀገር በዓለም ላይ ኢትዮጵያ የከፈለችውን ያህል የከፈለ የለም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " አግዛለው ብሎ መፎከርና ሄዶ መሞት ይለያያል " ብለዋል።
" ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ህዝብና መንግስት ጋር ለመጣላት ለመዋጋት ፍጹም ፍላጎት የላትም " ሲሉም ተደምጠዋል።
" አሁን በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በሶማሊያ አንድነት የሚታማ መንግስት አይደለም " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ሶማሊያዊያን አንድ እንዲሆኑ በንግግር ሳይሆን በተግባር የሰራ መንግስት ነው " ብለዋል።
" ከልባችን አንድ እንዲሆኑ ስለምንፈልግ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ፈርማጆ ስልጣን ላይ እያሉ ከሱማሌላንድ ፕሬዜዳንት ቢሂ ጋር ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ ለማገናኘት በተደረገ መኩራ እንዲገናኙ አድርገን ውይይት ተደርጓል ፤ ሶማሊያ እና ኬንያ በድንበር ጉዳይ ሲጣሉ አለም ሲንጫጫ ፕሬዜዳንት ፈርማጆን ኬንያ ወስደን ከወንድማቸው ከፕሬዜዳንት ኡሁሩ ጋር እንዲነጋገሩ ጥረት አድርገናል፤ ለምን ? የነሱ ሰላም የኛ ስለሆነ " ሲሉ አስረድተዋል።
" ሶማሊያ እንደ ግጭት ሰፈር አድርጎ የመጠቀም ፍላጎት ከብዙ ኃይሎች ይነሳል፤ እኛ ለዓለም ህዝብ የቀይ ባሕር 'አክሰስ' ጥያቄያችን ህጋዊ መሆኑን አሳይተናል። ዓለም በሙሉ ይገባቸዋልኮ ግን፣ ግን ነው የሚለው ፤ የኛ ፍላጎት ባሕርን አክሰስ ማድረግ ብቻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ከኢትዮጵያ መውሰድ ሲሆን ችግር የለውም፤ ለኢትዮጵያ መስጠት ነው ነውሩ ፤ ዲፕሎማሲያችን እንደዚያ ነው፤ አሁን መልኩን እየቀየረ ነው " ብለዋል።
" በእኛ እና ሶማሊያ መካከል ችግር ይፈጠራል ብዬ ባላስብም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " በሕዝቦች መካከል ጥላቻ እንዳይፈጠር ቁርሾ እንዳይፈጠር በተረጋጋና በሰከነ መንገድ ውጫዊ አክተር በሚያሰክን መንገድ መምራት ይጠይቃል " ሲሉ ተናግረዋል። #PP

#ትግራይ #እስልምና
ለዓመታት የተቋረጠው ግንኙነት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱ ተነገረ።
በአስከፊውና ደም አፋሳሽ ጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮችና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግንኙነት የቀረበውን ይፋዊ ይቅርታ ተከትሎ ግንኙነቱ ወደ ቀድመው እንዲመለስ መወሰኑ ታውቋል።
የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 2014 ዓ/ም ላይ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተለይቶ ራሱን ችሎ እንደተቋቋመ በይፋ አስታውቆ ነበር።
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ጦርነቱ መቆሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም አልተሳካም ነበር።
ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በመቐለ ከተማ ባካሄደው #አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አቀረበ ባለው የይቅርታ ደብዳቤ ላይ ከተወያየ በኃላ በሙሉ ድምፅ በመቀበል ከሶስት አመታት በላይ የተቋረጠው ግንኙነት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል።
በደም አፋሳሹ እና አስከፊው የትግራይ ጦርነት ምክንያት በተፈጠረ መቃቃርና አለመጣጣም የትግራይ የኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ከኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን ተለይተው " መንበረ ሰላማ " በሚል የራሳቸው ቤተክህነት ማቋቋማቸው ይታወቃል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ሲሆን በነገው ዕለት ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

#Tecno Spark 20 pro plus
ለአስገራሚ ፎቶ ‘Spark 20 pro+’ ይሁን ምርጫዎ!
ከስፓርክ ሲሪስ ስልክዎች የመጀመሪያ በመሆን ከፍተኛ የካሜራ ጥራት ያካተተው አዲሱ ’spark20 pro+’ ስልክ በ108 ሜጋ ፒክስል አልትራ ሴንሲንግ ካሜራ እና በ32 ሜጋ ፒክስል ሰልፊ ካሜራ መልኮን እንደ መስታወት ቁልጭ አድርጎ ከማንሳቱ በተጨማሪ 900% አልትራ ሴንሴቲቭ (ultra-sensitive) ከሱፐር ፍላሽ ላይት በ ኤ.አይ (AI) በመታገዝ ፎቶ ሳይደበዝዝ የማንሳት አቅም አለው ።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Spark20pro+ #TecnoMobile #TecnoEthiopia

#አቢሲንያ_ባንክ
አሁን ባሉበት ሆነው የአፖሎ አካውንት ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቁጥር ብቻ በቂ ሆኖዋል። የባንክ አካውንት ለመክፈት ይህን ያህል ቀሏል።
አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ የ9% ወለድ፣ አነስተኛ ብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን ያግኙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ ፤ በተለያዩ ጊዜያት የጅምላ እስር እና አፈሳ ይደረጋል በሚል ቅሬታዎች ሲነሱ ቆይተዋል። የመንግስት ምላሽ ደግሞ " በከተማው እንዲህ ያለው ነገር የለም " የሚል እንደነበር አይዘነጋም።
ይኸው የአፈሳ ነገር ሰሞኑን ከነበረው በዓል ጋር ተያያዞ ቀጥሎ በርካታ ወጣቶች " በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እየታፈሱ ታስረዋል " በሚል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታዎች ደርሶት ተመልክቷል።
አንድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የታሳሪ ቤተሰብ ፤ ከሰሞኑን የአማራ ብሄር ተወላጆች የሆኑ 32 ሰዎች ተይዘው መታሰራቸውን ፤ እነዚህ ሰዎች ሥራ ሰርተው ልጅ የሚያሳድጉ፣ ቤተሰብ የሚረዱ ሰዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።
የት ነው የታሰሩት ? ምን አድርገውስ ነው ? ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የታሳሪ ቤተሰብ፣ " ንፋስ ስልክ ላፍቶ ሆኖ ወረዳ 12 የሚባል ነው ልዩ ቦታው " ሲሉ መልሰዋል።
ከታሳሪዎቹ አንዱን ሄደው እንደጠየቁና " እሱም የከሰሱን ሁላችንንም ‘ ፋኖ በሚል ነው ’ " እንዳሏቸው ገልጸዋል።
" ፓሊስም ብናናግር ‘እኛ መፍትሄ አንሰጥም’ ነው የሚሉት " ያሉት እኚሁ ቤተሰብ ፤ ከታሳሪዎቹ መካከል አራቱ በባጃጅ ሥራ የሚተዳደሩ ቤተሰቦቻቸው መሆናቸውን ተናግረዋል።
ታሳሪዎቹን ፓሊስ እንዴትና የት እንደያዟቸው ጠይቀናቸው ፤ " ከላፍቶ ሚካኤል፣ ሚካኤልን ወስደው ከባህረ ጥምቀቱ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው የያዟቸው የሃና ማርያም ፓሊሶች " ብለዋል።
ስለጉዳዩ ምን ምላሽ እንዳላቸው ለመጠየቅ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰዎቹ ታስረውበታል ወደ ተባለው ላፍቶ ወረዳ 12 ፓሊስ ጣቢያ ያደገው የስልክ ሙከራ አልተሳካም።
የንፋስ ስልክ ፓሊስ መምሪያ ኮማንደር ዘለቀ ግን " እኛ ጋ በእንደዚህ አይነት ጉዳይ የታሰረ የለም " ብለው ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት ተቆጥበዋል።
በሌላ በኩል ፤ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ኮተቤ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ የጥምቀት በዓል በተፈጠረ ረብሻ በበዓሉ አክባሪዎች ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልክቶ ነበር።
ረብሻው የተፈጠረው ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2016 ዓ/ም ታቦተ ፅላቱ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ሊገባ ሲል በበዓለ ጥምቀቱ ሲሳተፉ የነበሩ ወጣቶች የዘመኔ ካሴና ምሬ (ምህረት) ወዳጆን ሥም በመጥራት ስለፋኖ እያቀነቀኑ በነበረበት ወቅት ሲሆን ፣ በበዓሉ ታዳሚዎች በኩልም ወደ ፀጥታ አካላት የድንጋይ ውርወራ ሲደረግ ተስተውሏል።
የአይን እማኞች በወቅቱ የተሳሰቡ ወጣቶች የፖለቲካ ይዘቶችን ያያዙ መልዕክቶችን ሲያስተጋቡና ፖሊስም ቆሞ ሲመለከታቸው ከቆየ በኃላ ወደ እርምጃ መሄዱን ተናግረዋል።
በወቅቱም በርካታ ወጣቶች በፓሊስ አባላት ታስረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው የአንድ ወጣት እናት ልጃቸው እንደተወሰደ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩንና በወቅቱ ስለተፈጠረው የፀጥታ ሁኔታ ለማጣራት ወደ አዲስ አበባና ፌደራል ፓሊስ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።
ነገር ግን ከበዓሉ ቀደም ብሎ ፖሊስ በእንዲህ ያለው በዓል እንዲጎላ የምንፈልገው ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስነስርዓቱን ብቻ እንዲጎላ ፣ የፖለቲካም ይሁን ማንኛውም መልዕክት እንደማይታገስ አስጠንቅቆ ነበር።
ዘገባውን የላከው የአዲስ አበባ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።