TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሹፌሩን እና ረዳቱን #በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን " FSR መኪና " ይዘው ከተሰወሩ ተጠርጣሪ ወንጀለኞች አንዱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ።

እንደ ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መረጃ ፤ ድርጊቱ የተፈጸመው በምስራቅ ጎጃም ዞን  ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፤ አባጀምበር ቀበሌ ፤ " የጨረቃን ጎጥ " ነው።

ከ " ገንዳ ውሃ " ከተማ ወደ " አዲስ አበባ " አንድ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭነው ሲጓዙ የነበሩ  ሾፌርና ረዳቱን ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ሰኔ 28/2015 ዓ/ም ሰዓቱ በትክክል ባልታወቀበት ሁኔታ ገድለው በመጣል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ፡፡

የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው ክትትል ተጠርጣሪ ወንጀለኛቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ማሳደራቸው መረጃ ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ ተጠርጣሪ ወንጀለኞቹን ክትትል በማድረግ ላይ እያለ ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ/ም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ አንዱ ተጠርጣሪ ወንጀለኛ #ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ሌሎች ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ ነው ሲል የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል።

የጎንቻ ሲሶ እነሴና ግንደወይን ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ አካላት ላደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ልዩ ምስጋና ቀርቦላቸዋል።

መረጃው የምስራቅ ጎጃም ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopia