TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JasiriTalentInvestor

Attention all aspiring entrepreneurs in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹!
Join us for an in-person information session to share knowledge about the Jasiri Talent Investor program offerings, the application process, and answers to any questions you might have

📅 26th January 2024 at 6:00pm.
📍 To be shared with those who RSVP
RSVP Link- https://bit.ly/421zcE

Make sure to mark your calendars! We are excited to get to know you and answer any questions you may have about the program.

#Jasiri4Africa
#JasiriTalentInvestor
#highimpactentrepreneurship
#marketcreatinginnovations
#Safaricom

M-PESAን በማውረድ ፤ አዳዲስ መኪኖች፣ ባጃጆችን፣ እንዲሁም ሌሎችም ብዙ ሽልማቶችን የማሸነፍ ዕድል እናግኝ።
እንዴት እናሸንፋለን?
• M-PESA ላይ በመመዝገብ
• ገንዘብ ወጪ እና ገቢ በማድረግ
• የአየር ሰዓት እና ጥቅሎችን በመግዛት
• ለነጋዴዎች እና ለቢዝነሶች በM-PESA በመክፈል
• ገንዘብ በመላክ
• ገንዘብ ከባንክ ወደ M-PESA እና ከ M-PESA ወደ ባንክ በማስተላለፍ
• ከውጭ ሀገር በM-PESA ገንዘብ በመቀበል
M-PESA ላይ እንመዝገብ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ ቀጣይ እድለኛ አሸናፊዎች እንሁን።
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።

Via EPA

@tikvahethiopia
የታሕሳስ ወር የዋጋ ግሽበት ጭማሪ አሳየ።

የታሕሳስ ወር ሀገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 28.7 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አሳውቋል።

በወሩ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ምግብ ነክ ዕቃዎች (food items) 30.6 በመቶ ድርሻ የያዙ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች (Non-food Items) 26.1 በመቶ በመሆን ተመዝግቧል፡፡

በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በህዳር ወር ከነበረበት 28.3 በመቶ ወደ 28.7 በመቶ በመሆን የተመዘገበ ሲሆን በዓላቱን ተከትሎ መጠነኛ ጭማሪ መኖሩን አገልግሎቱ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ መሪ ምን አሉ ? የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል። " ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር…
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ስለ ግብፅ ምን አለች ?

" በስምምነቱ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛውንም የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንቃወማለን " - ሶማሌላንድ

ዛሬ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጣለች። በዚህ መግለጫም ስለ ለሰሞነኛው የግብፅ ሁኔታ ምላሽ ሰጥታለች።

ምን አለች ?

ሶማሌላንድ ፤ ከግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ያላትን ስጋትም እውቅና እንደምትሰጥ ገልጻለች።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከሰቱ ክስተቶች አንፃር ቀጠናዊ ጉዳዮችን በውይይት እና በትብብር ለመፍታት ያለኝን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ " ብላለች።

ይሁን እንጂ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እና በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከል ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በኋላ የሚነሱ ማንኛውንም አይነት የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንድምትቃወም በድጋሚ አረጋግጣለች።

በመግለጫዋ ፤ " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር በተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አከብራለሁ " ስትል ገልጻለች።

" ሁሉም ፍላጎት ያላቸው አካላት ቀጠናዊ መረጋጋትን እና ገንቢ አጋርነትን በማስፈን ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታለሁ " ያለችው ሶማሌለንድ ፤ " በዚህ መንፈስም #ግብፅ በቅርብ ጎረቤቶቿ እንደ ፦
* #ሱዳን
* #ሊቢያ
* #ጋዛ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫዋን እንድትቀይር እናበረታታታለን " ብላለች።

" እነዚህ አካባቢዎች (ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ጋዛ) በአሁኑ ጊዜ ጉልህ ከሆኑ ተግዳሮቶች ጋር #እየታገሉ ነው ፤ እናም የግብፅ ገንቢ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለን እናምናለን " ስትል ገልጻለች።

የሶማሌለንድ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ከሁሉም ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን እና ትብብርን ያደርጋል ስትል አሳውቃለች።

" የጋራ ጂኦፖለቲካዊ አካባቢያችንን ሁኔታ ለማሻሻል ከግብፅ እና ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር #በመከባበር እና #በጋራ_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ገንቢ ግንኙነትን ለመፍጠር እንሰራለን " ስትል ገልጻለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በደበሶ ከተማ በመኪና አደጋ የሞቱ ምእመናን ዛሬ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

በምዕራብ ሐረርጌ ደበሶ ከተማ ትላንት ጥር 12/05/2016 ዓ/ም የቃና ዘገሊላ ክብረ በዓል ዕለት ታቦታትን አጅበው በመጓዝ ላይ የነበሩ ምእመናን ላይ ከድሬደዋ የሚመጣ ከባድ የጭነት መኪና ባደረሰው አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ሰብከት ማሳወቁ ይታወሳል።

ሕይወታቸው ያለፈው ምእመናን ዛሬ ልባቸው በሀዘን የተሰበረ እጅግ በርካታ ምእመናን በተገኙበት ከቀኑ በ7:45 ላይ ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።

ሀገረ ስብከቱ ፤ " ከተቀበሩት መካከል ሦስቱ ጨቅላ ህጻናት ሲሆኑ አንዱ ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ የቀበሌው ሚኒሻ ሃይማኖቱ #ሙስሊም ስለሆነ በወገኖቻችን በሙስሊሞች የቀብር ስፍራ ተቀብሯል። " ሲል አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ሰብከት ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#አክሱምኤርፖርት

የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ ለማደስ በጨረታ ላሸነፈው የኮንስትራክሽን ድርጅት ይፋዊ የርክክብ ስነ-ሰርዓት አላካሄደም ተብሏል።

ይህ ሁኔታ ደግሞ የእድሳት ሰራው በፍጥነት በሙሉ አቅም እንዳይሰራና እንዲዘገይ ምክንያት እየሆነ ነው በሚል ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕረዚደንት ለአንድ ጊዜ ፤ ከ7 ዓመታት በላይ ድግሞ የትግራይ የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕረዚደንት በመሆን አገልግለዋል።

መምህሩ ከሽረ ከተማ መልስ ወደ ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ አክሱም ጎራ ብለው ባዩት ነገር ባለመደሰታቸው የሚከተለው አስተያየት በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ላይ አጋርተዋል።

" በአካል ሄጀ እንዳረጋገጥኩት የአክሱም ሃፀይ ዮሃንስ አውሮፕላን ማረፍያ የመሬት (site) ርክክብ አስከ አሁን አልተተገበረም።

ርክክቡ የሚያከናውኑው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን ኮንሰልታንቱ እስከ አሁነን ቦታው ላይ አልተገኙም። ርክክቡ ስላልተፈፀመ ደግሞ የእድሳት ስራው በተሟላ መልኩ አልተጀመረም።

እርግጥ ነው እድሳቱ ለማካሄድ ጨረታው ያሸነፈው የኮንስትራክሽን ድርጅት ቦታው የማጥራት የመሰለ ቀላል ስራ እየሰራ ነው። ይፋዊ የርክክብ ስነ-ስርዓት ሳይካሄድ ግን ስራው አይጀመርም። እና አስረካቢው አካል ለምን ዘገየ ? " ብለዋል። 

የመምህሩ አስተያየት ደግፈው አስተያየት የሰጡ ሰዎች ደግሞ ፤ " እድሳቱ በይፋ መጀመሩ በሚድያ መስማታቸው እንዳስደሰታቸው አስታውሰው ፤ ዜና ከተነገረ አንድ ወር አስቆጥሮ ስራው በጊዜው አለመጀመሩ አሳዝኖናል " ብለዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ አክለው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትና ኮንሰልታንቱ ለምን ርክክቡ እንዳልፈፀሙ እንዲጠየቁላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።

ዘግይቶ ከምንጮች በተገኘ መረጃ ታህሳስ 2016 ዓ.ም አጋማሽ እድሳቱ እንደሚጀመር በሚድያዎች የተነገረለት አውሮፕላን ማረፍያው ፤ ጥር 14/2016 ዓ.ም የመሬት (site) ርክክብ ተፈፅሞ በሙሉ እቅም ወደ ስራ ይገባል መባሉ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
                                       
@tikvahethiopia            
#CPJ

ኤርትራ 16 #ጋዜጠኞችን_በማሠር ከአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ እንደምትይዝ በጋዜጠኞች መብት ላይ አተኩሮ የሚሠራው ሲፒጄ ያለፈውን የፈረንጆቹ 2023 ዓ/ም በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

16 ጋዜጠኞችን አሥራ የያዘችው ኤርትራ፣ በዓለም 7ኛ ደረጃን እንደምትይዝም ሲፒጄ ገልጿል።

አንዳንዶቹ ጋዜጠኞች በዓለም ለረጅም ግዜ የታሠሩ እንደሆነም ሪፖርቱ አመልክቷል።

በሁሉም ጋዜጠኞች ላይ ክስ ተከፍቶ እንደማያውቅም ሪፖርቱ ጠቁሟል።

እስካለፈው ወር ድረስ በአፍሪካ የታሠሩት ጋዜጠኞች ቁጥር 47 እንደነበር ያመለከተው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ 8 ጋዜጠኞችን በማሠር፣ ካሜሩን ደግሞ 6 በማሠር የሁለተኛና እና ሶስተኛ ረድፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

" በኢትዮጵያ በእሥር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች ቁጥር፣ በአገሪቱ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃን የሚገኙበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያስያል ሲል " ሲፒጄ በሪፖርቱ አመልክቷል።

ባለፈው ዓመት በሰሜን ኢትዮጵያ የነበረውን ጦርነት ያስቆመ የሠላም ስምምነት ቢፈረምም፣ በአማራ ክልል በአካባቢው በሚገኙ ኃይሎች እና በፌዴራሉ ኃይሎች መካከል የሚካሄደው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው ያለው ሲፒጄ፣ ስምንቱም ጋዜጠኞች የታሠሩት ግጭቱን በተመለከተ ዘገባ ካወጡ በኋላ መሆኑን አስታውቋል።

ባለፈው ዓመት በመላው ዓለም ላይ የታሠሩ ጋዜጠኞች ቁጥር እስከአሁን ከታዩት ከፍተኛ ሆኑ ከተመዘገበው ዓመት ጋር እንደሚቀራረብ ያመለከተው ሲፒጄ፣ የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ባለፈው ጥቅምት መጀመሩን ተከትሎ፣ እስራኤል ጋዜጠኞችን በብዛት ካሰሩ አገራት ጎራ መቀላቀሏን አስታውቋል።

ቻይና 44 ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚውን ሥፍራ ስትይዝ፣
ሚያንማር 43 በማሠር ሁለተኛ
➡️ ቤላሩስ 28 ጋዜጠኞችን በማሠር ሶስተኛ ሥፍራን ይዘዋል።

#VOA #CPJ

@tikvahethiopia