TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደበሶ

ዛሬ 8 ሰዓት ላይ በደበሶ ደብረ ልዕልና ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መነሻውን ከድሬደዋ ያደረገና ወደ ጭሮ ጭነት ይዞ ሲጓዝ የነበረ ከባድ የጭነት መኪና የቃና ዘገሊላ በዓል እያከበሩና ታቦት ከባሕረ ጥምቀት ወደ መንበረ ክብሩ በዝማሬ ፣ በሆታና በዕልልታ እያጀቡ ባሉ ምዕመናን ላይ በፍጥነት በመውጣት ባደረሰው ገዳት  7 ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አሳውቋል።

ሀገረ ስብከቱ ፤ ከ7 በላይ ሰዎች ከባድ ጉዳት ፣ ወደ 10 የሚደርሱ ከቀላል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑንና አሁን ላይ በጭሮ ሆስፒታል በድንገተኛ ጽኑ ሕሙማን ክፍል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሟቾች መካከል ህፃናት እና የፀጥታ አካላት ይገኙበታልም ብሏል።

ጉዳቱን ያደረሰው መኪና መንሥኤው ምን እንደሆነ በባለሙያዎች ይጣራል ሲልም አሳውቋል።

የምዕራብ ሐረርጌ ዞን በበኩሉ በጦሎ ወረዳ ደበሶ ከተማ ዛሬ ከሰዓት በተከሰተው የትራፊክ አደጋ 5 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲል ለኤፍቢሲ ተናግሯል።

5 ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

" አደጋው የተከሰተው ከድሬዳዋ ወደ ጭሮ ሲጓዝ የነበረ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ #ፍሬን አስቸግሮት ፍጥነቱን መቆጣጠር ባለመቻሉ በመንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችን በመግጨቱ ነው " ሲል ዞኑ ስለ አደጋው መንስኤ አብራርቷል።

በተያያዘ መረጃ ትላንት በጥምቀተ ባህሩ ስፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት አሳውቋል።

@tikvahethiopia