TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#USA #IGAD

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ካምፓላ እና አዲስ አበባን ይጎበኛሉ ተብሏል።

ማይክ ሐመር መጀመሪያ ካምፓላ ገብተው በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ እንዲሁም በሱዳን ጦርነት ላይ በሚመክረው የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ላይ ይሳተፋሉ።

ከዛም ወደ ኢትዮጵያ፣ አዲስ አባባ ይመጣሉ።

ልዩ መልዕክተኛው በአዲስ አበባ ቆይታቸው፦

" - ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በተለይ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ስላለው ግጭት ውይይት ያደርጋሉ።

- በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ።

- ሰላማዊ ሰዎች እንዲጠበቁ እንዲሁም ሰብዓዊ መብት እንዲከበር ጥሪ ያቀርባሉ።

- ከአንድ ዓመት በፊት በስምምነት የተቋጨውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ የሚከናወነውን ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ተሃድሶ እና ማሰናበትን በተመለከተ እንዲሁም ተጎጂዎችን መሠረት ስላደረገው የሽግግር ፍትህ ሂደት ይወያያወሉ። " ሲል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ቢቢሲ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን ዋቢ አደርጎ ካሰራጨው ዘገባ ነው የወሰደው።

@tikvahethiopia
" ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች " - አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ

የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ መግለጫን አጥብቃ ትቃወማለች ብለዋል።

የአረብ ሊግ መግለጫ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ እና ሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የመግባት ሙከራ ነው ብለዋል።

" ኢትዮጵያ ከብዙ የአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት አላት። " ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው " ሆኖም ግን የአረብ ሊግ የጥቂቶችን ጥቅም ብቻ እያስከበረ ይገኛል " ሲሉ ገልጸዋል።

የአረብ ሊግ ትናንት በግብጽ ካይሮ የሚኒስትሮች ልዩ ስብሰባ አካሂዶ ነበር።

በዚህም ስበሰባ ፤በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ዓለም አቀፍ ሕግን በግልፅ የጣሰ በሚል አውግዟል። ስምምነቱ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሚፃረር ነው በሚል ተቃውሟል። የአረብ አፍሪካና የዓልም አቀፍ መርሆች ላይ በግልፅ የተሰነዘረ ጥቃት ነውም ብሏል።

የዚሁ የአረብ ሊግ አባሏ ግብፅ ኢትዮጵያ በአካባቢው #የአለመረጋጋት ምንጭ አይሆነች ነው ማለቷም ተሰምቷል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ልታገኝ የሚያስችላት የኢትዮ ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት በተፈረመ ማግስት በቅድሚያ ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ናት። የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ጉዳዩን አስመልክቶ ቀድመው ስልክም የደወደሉት ወደ ግብፅ ነበር።

ኢትዮጵያ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ህግን እንዳልጣሰና የትኛውንም ሀገር/አካል የሚጎዳ እንዳልሆነ በተደጋጋሚ አሳውቃለች።

ሶማሌላንድ በበኩሏ፤ ከሶማሊያ ከተነጠለች ሶስት አስርት ዓመታት ማለፉንና ሉዓላዊት ነፃ ሀገር መሆኗን አመልክታ የትኛውንም ዓለም አቀፍ ስምምነት ለመፈረም ከሶማሊያ ፍቃድ መጠየቅ እንደማይጠበቅባትና ሶማሊያንም እንደማይመለከት አሳውቃለች። ስምምነቱ ሌሎች ሀገራት ከሚፈፅሙት የሊዝ ስምምነት ምንም የተለየ ነገር እንደሌለውም አሳውቃለች።

(ከላይ የተያያዘው የአረብ ሊግ አቋም ነው)

@tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሠ ምን አሉ ?

" ለኢትዮጵያ ዕድገት እንቅፋት ለመፍጠር የሚጥሩ በአካባቢያችን ያሉ #ታሪካዊ_ጠላቶቻችን እና #አዳዲስ_ኃይሎች እየተሰባሰቡ እንዳለ እያየን ነው።

እነኝህ ጠላቶች ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ በቅርበት እየተከታተልን እንገኛለን።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የማንንም ሃገር ብሔራዊ ጥቅም መንካት ተገቢ አለመሆኑን በማመን በዘመኗ የሌላ ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ነክታ አታውቅም አሁንም አትነካም ታሪኳም አይደለም።

የሌላን ሀገር ብሔራዊ ጥቅም እንደማንነካው ሁሉ እኛም የሃገራችንን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈን አንሰጥም።

ለሃገራችን ሁለንተናዊ ብሔራዊ ጥቅም እንደወትሮው ሁሉ ዛሬም ዘብ እንቆማለን። "

ጄነራሉ ይህን የተናገሩት " አዋሽ አርባ " የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሜካናይዝድ ጦርን እና እየወሰደ ያለውን ስልጠና ከጎበኙ በኃላ ነው።

ሰልጣኞቹ በስነ-ልቦና ዝግጁነት ብቁ በመሆን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እና ክብር መረጋገጥ ሲባል የሚወስዱትን ሙያዊ ስልጠና በፍጥነት ማጠናቀቅና ለሚሰጣቸው #ማንኛውም_ግዳጅ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው #አፅንኦት ሰጥተዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#CBE

በርካታ አማራጮች...
***
ለጥምቀት በዓል ከውጭ ሀገር በመረጡት
ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ገንዘብ ያስልኩ!

መልካም የጥምቀት በዓል!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
***

የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!  
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh  
• Telegram፡- https://t.iss.one/combankethofficial
TIKVAH-ETHIOPIA
" ጋሞ ዞን፣ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ከመባባሱ በፊት አስቸኳይ ምላሽ ይሻል " - ኢሰመኮ ኢሰመኮ አሰባሰብኩ ባለው መረጃ እና አነጋገርኳቸው ያላቸው የአስተዳድር መዋቅር ጠያቂዎች እንደገለፁት በጋሞ ዞን ፣ አርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ሥር የሚገኙ ፦ * ኤልጎ * ወዘቃ * ደምብሌ እና ጫሞ 01 የተባሉ አራት ቀበሌዎች ከጋሞ ዞን በመውጣት ልዩ ወረዳ ሆነው ለመደራጀት በተለያየ…
#ደቡብኢትዮጵያክልል:- ከአስተዳደራዊ መዋቅር ጋር የተያያዙ አለመግባባቶች ነዋሪዎችን ያሳተፈና አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔ ይሻል ሲል ኢሰመኮ አሳውቋል።

በነሐሴ ወር 2015 በቆላ ሻራ ቀበሌ ለደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ከኃይል እርምጃዎች መቆጠብን ጨምሮ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በአፋጣኝ ማስጀመር እና በሀገራዊ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች የመሳተፍ መብት ሊረጋገጥ ይገባል ብሏል።

ኢሰመኮ የላከልን ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
 
" ፍተሻው መጠንከር አለበት ብለን ካመንን እናጠናክራለን ፤ የፍተሻ መጠናከር የሚከፋው ሰው ይኖራል ብለን አንገምትም " - ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ

የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላምና በድምቀት እንዲከበር በፀጥታው ኃይል በኩል በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን አሁን በዓሉን እየተጠባበቀ ይገኛል።

የኮሚሽኑ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ፤ " የአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆ የፀጥታ እና የደህንነት የጋራ ግብረኃይል በዛ ስር ያሉ የፀጥታ ተቋማት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ስራ ላይ ናቸው " ብለዋል።

" በመዲናዋ ታህሳስ ወር ውስጥ በተካሄዱ የህግ ማስከበር ዘመቻዎች በርካታ ግኝቶች ተገኝተዋል ፣ ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል የነበሩት ኦፕሬሽኖች የከተራ እና የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ትልቅ አውንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

የፀጥታ ኃይሉ ከእምነት አባቶች ጋር ጠለቅ ያለ ውይይት ማድረጉንም ጠቁመዋል።

" የተለየ ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች በተለያየ መንገድ ፍላጎታቸውን ለማንፀባረቅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ፤ በተለይ ህትመት ቤቶች አካባቢ በፅሁፍ ፣ በምስል ሊሆን ይችላል የተለያዩ ነገሮችን በመቅረፅ ህገወጥ መልዕክቶች እንዳይተላለፉ ከእምነት አባቶች ጋር ውይይት እና መግባባት ተደርሷል " ብለዋል።

ከበዓሉ ዝግጅት ጋር በተያያዘ ወጣቶች እየተያዙ ነው፣ ፍተሻዎችም ጠንክረዋል በዚህ ላይ ፖሊስ ምን ይላል ሲሉ የተጠየቁት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ " ፖሊስ በተለያዩ ቦታዎች ያለውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የት ቦታ ፍተሻ መደረግ አለበት ?  ... ፍተሻው መጠንከር የሚገባው ከሆነ እናጠናክረዋለን  ፤ ፍተሻ መጠናከሩ የሚከፋው ሰው ይኖራል ብለን አንገምትም " ሲሉ መልሰዋል።

" ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተገናኘ በሚደሩ ፍተሻዎች ለወንጀል መፈፀሚያ የሚሆኑ ስለቶች፣ የጦር መሳሪያዎች ሳይቀር በቁጥጥር ስር እናውላለን ፣ የተሰረቁ ሰሌዳዎች፣ መታወቂያ የሌላቸውን ሰዎች የምናገኝበት ሁኔታ አለ " ያሉት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ " በሃይማኖታዊ በዓላት በርካታ ሰው አደባባይ ወጥቶ በሚያከብርበት ወቅት ህግ ማስከበራችን ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ማንም ሰው ካጠፋ መያዝ ካለበት በህግ አግባብ ይያዛል ፣ እኛ የምንፈልገው ባህላዊና ሃይማኖታዊ ገፅታው ብቻ እንዲጎላ ነው ሌሎች መልዕክቶች በፍፁም እንዲተላለፉ አንፈቅድም ፖሊስም አይታገስም " ሲሉ አሳስበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምክትል ኮንደር ማርቆስ የሰጡትን ቃል ያዳመጠው ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ከሰጡት ማብራሪያ መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
#Mekelle #ኣሉላ_ኣባነጋ_ኤርፖርት

" በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም " - ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ግለሰብ

ተሳፋሪዎች የጫነ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ከቀኑ 8:00 ሰዓት አከባቢ አደጋ እንደገጠመው ተሰምቷል።

ለአውሮፕላን ማረፍያው ቅርበት ያላቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ ግለሰብ ለመቐለ ኤፍኤም 104.4 በሰጡት ቃል ፤ አውሮፕላኑ መንሸራተት አጋጥሞት ከዋናው መንገድ መውጣቱንና በሰው ህይወት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተናግረዋል።

የአውሮፕላን የአደጋው መነሻ በመጣራት ላይ መሆኑም አስተያየት ሰጪው አክለው ገልፀዋል።

መረጃውን የመቐለ ኤፍ ኤምን ዋቢ በማድረግ ያደረሰን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia