TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መቐለ
 
ከመቐለ ከተማ ተሰርቃ ልትሰወር የነበረ አንድ ተሽከርካሪ በፀጥታ ኃይሎች ርብርብ ማትረፍ ተችሏል።

ዘረፋው አመሻሽ የተፈፀመ ሲሆን ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት በፓሊስ እርምጃ መመከን ችሏል።

ስርቆቱ እንዴት ተፈፀመ ?

መኪናዋ RAVA-4 ስትሆን በ " 03532 ኮድ-2 ትግ " የሰሌዳ ቁጥር የምትታወቅና ባለቤትነትዋ የመቐለ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የአቶ ሃይለ ገ/መስቀል የተባሉ ግለሰብ ናት።

እስካሁን በፓሊስ ቁጥጥር ስር #ያልዋሉት ተጠርጣሪዎች መኪናዋ ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም ቴድሮስ ከተባለ የመኪናዋ ባለቤት ልጅ #አፍነው በመቀማት ይዘዋት መሰወራቸው የተረዱ ባለቤቶች ወድያውኑ ወደ ፓሊስ ስልክ ደወሉ።

ፓሊስ ጊዜ ሳያጠፋ ተጨማሪ የፀጥታ ሃይሎች በማሰማራት ከመቐለ ወደ ሌሎች አከባቢዎች የሚያወጡ መንገዶች #እንዲዘጉ አደረገ።

ይህንን የተቀናጀና የተናበበ የፓሊስ የፀጥታ እንቅስቃሴ የተረዱ የሚመሰሉት መንታፊዎች መኪናዋን በአስፋልት መንገድ ጥለው ሸሽተዋል።

ፓሊስም መኪናዋን ከጥር 4 ወደ ጥር 5 /2016 ዓ.ም አጥቢያ ከሌሊቱ 8:00  በቁጥጥር ስር አውሏታል።

የሚሊዮኖች ብር ዋጋ ያላት መኪና ስርቀው ጥለዋት የጠፉት ተጠርጣሪዎች አድኖ በቁጥጥር ስር ለማዋል በከፍተኛ ጥረት ላይ እንደሆነ የገለፀው የመቐለ ከተማ ፓሊስ ፤ ባለቤቶች ንብረቶቻቸው በጥንቃቄ እንዲይዙ መክሯል።

ተጠርጣሪዎች በህግ ስር ውለው ቅጣታቸው እንዲቀበሉ ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩ እንዲያደርግ መጠየቁ መቐለ ኤፍ ኤምን ዋቢ በማድርግ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧን።

Photo Credit - FM መቐለ
                                     
@tikvahethiopia            
#ሶማሌ

በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ተቀጠፈ።

ዛሬ ከሰዓት በሶማሌ ክልል ፋፈን ዞን ፤ ሸበሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 12 ሰዎች ተጎድተው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።

አደጋው የደረሰው ከጅግጅጋ መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ " ሚኒባስ " ተሽከርካሪ እና ከሸበሌ አቅጣጫ ሲመጣ በነበረ " ሲኖ ትራክ " እየተባለ በሚጠራው ተሽከርካሪ መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው።

ፖሊስ የአደጋውን ምክንያት እያጣራ ሲሆን የሚደርስበትን ለህዝብ እንደሚያሳውቅ አመልክቷል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ሙስጠፋ ሙሁመድ በትራፊክ አደጋው ምክንያት በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ለቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ተመኝተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከክልሉ ቴሌቪዥን (ኤስአርቲቪ ሶማልኛ) ማግኘቱን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
የሳፋሪኮምን ያልተገደበ ኢንተርኔት ጥቅልን በቅናሽ በM-PESA ሳፋሪኮም App ላይ ብቻ  ያገኙታል::
🔗 የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ: https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#SafaricomEthiopia #MPESASafaricom  #FurtherAheadTogether
#ኤክሶደስ_የፊዝዮቴራፒ_ልዩ_ክሊኒክ

በውቢቷ ባህርዳር አዲስ ቅርንጫፍ ከፍተናል ፤ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች፦
- ለአንገት፣ ለትክሻ፣ለወገብ ህመም
- ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ   ችግር
- ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር
- ለፊት መጣመም
- ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል
- በአጠቃላይ ከነርቭ፣ ከጡንቻ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች
አድራሻችን፦ ቁጥር 1_ አዲስ አበባ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን ፤ ቁጥር 2_ ባህርዳር ቀበሌ 14 አልዋቅ ሆቴል አጠገብ ስልክ ቁጥር 0979099909 / 0911039377
በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://t.iss.one/ExodPhysioClinic
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ስርዓተ ቀብርን ክብሩን በጠበቀ ደረጃ እንዲፈፀም ለማድረግ ኮሚቴ እንደተቋቋመ አሳውቋል።

ኮሚቴው ይፋዊ መግለጫ ይሰጣልም ተብሏል።

ከሚሰጠው መግለጫ በኃላ የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ አስክሬን ወደ ሀገር ቤት መጥቶ የቀብር ስነስርዓቱ እንደሚፈፀም የቴሌቪዥን ጣቢያው አሳውቋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያው ፤ የጋዜጠኛ አስፋው አስከሬን ረቡዕ ጥር 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ቤተሰቦቹ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ በተገኙበት የሥንብት ሥነስርዓት ይካሄዳል ብሏል።

ሃሙስ ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሜሪላንድ በሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተክርስቲያን የፍትሃት ሥርዓት እንደሚከናወንለትና ቅዳሜ ጥር 11 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የአስከሬን ሽኝት ይደረግለታል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክቷል።

በአዲስ አበባም ሊካሄደው የቀብር ሥነስርዓቱ የተዋቀረው ኮሚቴ ደግሞ የቀብሩን ቀንና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎች በይፋ ይሰጣል ብሏል።

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ሀገር ዲሲ የጆርጅ ዋሽንግተን ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ባለፈው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ከወራት በፊት ስትሮክ አጋጥሞት ለተጨመሪ ህክምና ወደ አሜሪካ ሄዶ የነበረ ሲሆን ተደጋጋሚ ምርመራ ተደርጎለት የጭንቅላት ካንሰር እንዳለበት ተነግሮት ህክምናውን ሲከታተል ቢቆይም ህይወቱ ሊተርፍ አልቻለም።

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እና ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ነው።

@tikvahethiopia
" ... 49 የንግድ ቦታዎች በታላላቅ ባለሀብቶች እጅ የተገኙ ሲሆን 17 ቦታዎችም በአመራሩና የመንግስት ሰራተኛዉ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ እጅ ብቻ 32  ሼድና ኮንቴነሮች  ተይዘዉ ተገኝተዋል " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች

በሀዋሳ ከተማ ለወጣቶች ከተላለፉ የንግድ ቦታዎች  ሰባ በመቶው (70%) በህገወጥ መንገድ ላልተገባ አገልግሎት መዋሉን የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

በኦዲት ሪፖርት መሰረት ከ1525 ኮንቴነርና ሸዶች ወስጥ ወጣቶች በአግባቡ እየተጠቀሙባቸዉ ያሉት 342 ብቻ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያው የገለጹት የቢሮዉ ኃላፊ ወይዘሮ ሀገረጺዮን አበበ ቀሪዎቹ 1183 ሸዶችና ኮንቴነሮች #ላልተፈቀደለት አገልግሎት መዋላቸዉን ገልጸዋል።

በ5 አመት መመለስ የነበረባቸዉ የመስሪያ ቦታዎች ሼዶችና ኮንቴነሮች እስከ 20 አመታት ድረስ በግል ይዞታነት መቆየታቸውን የሚገልጹት ኃላፊዋ አሁን ላይ አንዳንዶቹ ቦታዎች ላይ በብሎኬት ገንብተዉ በማጭበርበር " ህጋዊ ነን " የሚሉ መኖራቸዉን ያነሳሉ።

በሌላ በኩል በማህበር ተደራጅተዉ የተቀበሉትን የመስሪያ ቦታ በማከራየት እንደገና በስራ ፈላጊ ከሚመዘገቡት በተጨማሪ የተሰጣቸውን የንግድ ቦታ #ወደመኖሪያ ቦታነት የቀየሩ እንዳሉም የኦዲት ግኝቱ ይጠቁማል።

ከዚህ በተጨማሪም 49 የንግድ ቦታዎች በታላላቅ ባለሀብቶች እጅ የተገኙ ሲሆን 17 ቦታዎችም በአመራሩና የመንግስት ሰራተኛዉ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ እጅ ብቻ 32  ሼድና ኮንቴነሮች  ተይዘዉ ተገኝተዋል።

የኦዲት ግኝቱ ካመላከታቸዉ ህገወጥ ድርጊቶች ውስጥ በከተማዉ ለወጣቶች ከተሰጠ 15 ሄክታር መሬት አንድም ቦታ በወጣቶች እጅ አለመገኘቱና መቶ በመቶ በባለሀብቶች እጅ መገኘቱን የሚያነሱት ወይዘሮ ሀገረጺዮን አሁን ላይ እንዲህ ያሉትን ወንጀሎች ተከታትሎ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጉዳዩ ለከተማ አስተዳድሩ መሰጠቱን ገልጸዋል።

በመሆኑም ወጣቶች የተሰጣቸዉን ጥሩ እድል አሳልፈዉ ከመስጠት ተቆጥበዉ ራሳቸውን እንዲቀይሩ ጥሪ ያቀረቡት ኃላፊዋ ይህ የክትትልና የማጣራት ስራ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ተደራሽ እንደሚደረግ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

መረጃው ተዘጋጅቶ የተላከው በሀዋሳው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#JASIRI

Application for the Jasiri Talent Investor Program Cohort 6 is now open. Jasiri calls on aspiring entrepreneurs from Kenya, Rwanda, and Ethiopia to apply.

PRESS RELEASE : https://telegra.ph/ANNOUNCEMENT-01-15-3

Join us on telegram https://t.iss.one/jasiri4ethiopia

#jasiri4africa
“ ‘ የሚቀርቡት ነገሮች ሕዝብን በመንግሥት ላይ የሚያነሳሱ ናቸው ’ ተብለን ታግደናል ” - የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ

በደራሲ አቶ በረከት በላይነህና ተዋናይ ግሩም ዘነበ አማካኝነት ዘወትር በሳምንት ሁለት ቀናት በዓለም ሲኒማ ሲቀርብ የነበረው “ እያዩ ፈንገስ፣ ቧለቲካ ” ቴያትር ከሐሙስ ጥር 2 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንዳይታይ “ታገደ” መባሉን ተከትሎ ከፊሎቹ ቁጣቸውን ከፊሎቹ ደግሞ መዘጋቱ ልክ እንደሆነ በማኀበራዊ ሚዲያዎች ሀሳብ ሲለዋወጡ ተስተውለዋል።

ቲያትሩ “ ታገደ ” ከተባለ በኋላ ከፊሎቹ ‘ ሌሎች ተውኔቶችስ ያለመዘጋት ዋስትናቸው ምንድነው?’፣ ከፊሎቹ ደግሞ ማንም እየተነሳ ‘መንግሥትን መተቸት አይችልም’ የሚሉት ሀሳቦች በየፊናቸው ሲወራወሯቸው ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

አንድ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን የሰጡ ቤተሰብ፣ “ ይህ ቲያትር እኮ መሬት ላይ ያለውን እውነታ በጨዋታ እያዋዛ ቁም ነገር የሚያስጨብጥ፣ መንግሥትም ቢሆን ሊማርበት የሚገባ ነበር እንጂ መዘጋቱ ስህተት ነው ” ብለዋል።

ሌላኛው አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው፣ “ መንግሥትን በተዘዋዋሪ ከመተቸት በቀጥታ መንገር ይቻላል፣ ይህ የመንግሥትና የሕዝብን ግንኙነት ሲያሻክር የኖረ ቲያትር ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ቲያትሩ ከመታገዱ ከአንድ ቀን በፊት በ “ እያዩ ፈንገስ፣ ቧለቲካ ” የማኀበራዊ ትስስር ገጽ እንደተገለጸው ከሆነ፣ ቲያትሩ እንዳይታይ የተከለከለው፣ “ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የሥራ ኃላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ ” መሠረት ነው።

በገለጻው መሠረት፣ “ ቴአትር ቤቱም ይህንኑ የመንግሥት የጸጥታ ኃላፊዎች ትእዛዝ ለቴያትሩ አዘጋጆቹ በማሳወቅ ውሉን ማቋረጡን ገልጿል። ” ተብሏል።

ይህንኑ መረጃ መሠረት በማድረግ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከዓለም ሲኒማ ማብራሪያ ለማግኘት ባደረገው ማጣራት፣ “ የሚቀርቡት ነገሮች ሕዝብን በመንግሥት ላይ የሚያነሳሱ ናቸው ተብለን ታግደናል ” የሚል ምላሽ ከአንድ ምንጭ ሰምቷል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጭ፣ ቲያትሩ መታዬት እንዳቆመ፣ ይህ የሆነው በቃል በተሰጣቸው ትዕዛዝ እንደሆነ፣ ሙሉውን መረጃ ደግሞ አቅራቢውንና ደራሲውን መጠየቅ እንደሚገባ ከመግለጽ ባለፈ ካላቸው ስጋት አንጻር ተጨማሪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በተጨማሪም አቅራቢውና ደራሲው በጉዳዩ ዙሪያ ምን ምላሽ እንዳላቸለው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

“ እያዩ ፈንገስ ” በመጋቢት ወር 2006 ዓ/ም መታየት እንደጀመረ፣ በዚህም በ “ እያዩ ፈንገስ ” ቁጥር 1 “ ፌስታሌን ”፣ ቁጥር 2 “ አጀንዳዬን ” ተውኔቶች እንደታዩበት፣ ከዚያ በኋላ ደግሞ ከጥቅምት 15/2016 ዓ/ም ጀምሮ ደግሞ “ እያዩያዩ ፈንገስ ” ቁጥር 3 “ ቧለቲካ ” በየሳምንቱ ሀሙስና እሁድ ለሕዝብ እይታ ሲቀርብ ነበር።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#ቻይና

ኢትዮጵያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ አሁንም አቋሟ ያልተቀየረና የፀና መሆኑን አሳውቃለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአንዲት ቻይና ፖሊሲን ለረጅም ዓመታት ስታራምድ መቆየቷን አስታውሰው ይህ አቋሟ በዘመናት መካከል መንግስታት አፅንተው የያዙት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከሰሞኑን ራሷን ከቻይና ነጥላ እንደ ነፃ ሀገር በምትቆጥረው ታይዋን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተደርጎ ነበር።

በዚህ ምርጫ ቻይና አትወዳቸውም የሚባሉት፣ አስቸጋሪና አደገኛ ሰው ብላቸው የምትጠራቸው በሙያቸው ሐኪም የሆኑት ዊሊያም ላይ ማሸነፋቸው ተዘግቧል።

ዶክተሩ " ለቻይና አንንበረከክም !! " በሚል አቋማቸው ነው የሚታወቁት።

ቻይና ከምርጫው በፊት አምርራ ለምትጠላው ለገዢው ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ (ዲፒፒ) ህዝቡ ድምጽ እንዳይሰጡ አሳስባ የነበረ ቢሆንም የዚሁ ፓርቲ አባል የሆኑት የሕክምና ዶክተሩ ዊሊያም ላይ ቺንግ አሸንፈዋል።

ሰውየው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " ታይዋን ነጻ አገር መሆኗን ማወጅ አያስፈልጋትም፣ ምክንያቱም ታይዋን ሉአላዊና ነጻ አገር ስለሆነች " ብለዋል።

ይህንን ምርጫ ተከትሎ ሀገራት አቋማቸውን እና አስተያየታቸውን ሲሰጡ ነበር።

አሜሪካ በምርጫው ላሸነፉት ፕሬዜዳንት በይፋ የ" እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት አስተላልፋ ፤ ከታይዋን እና ከገዢው ፓርቲ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታጠናክር አሳውቃለች።

ከምርጫው በኃላ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ፤ " እኛ ነፃነትን አንደግፍም ... " የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

አሜሪካ ከታይዋን ጋር ይፋዊ ያልሆኑ ግንኙነቶች ያሏት ሲሆን ታዋይም የአሜሪካ ድጋፍ እንዳላት በተለያየ ጊዜ ተናግራለች ፤ የአሁኑን ምርጫም ተከትሎ የቀድሞ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ስቴፋን ሃድሌይ ጭምር ያሉበት ይፋዊ ያልሆነ ልዑክ ወደ ታይዋን ልካ ከአሁኑ ተመራጭ ፕሬዜዳንት እና ከቀድሞ ጋር ውይይት አድርጋለች።

ከአሜሪካ በተጨማሪ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ የአውሮፓ ህብረት፣ እንዲሁም ካናዳ ፣ ጃፓን ለገዢው ፓርቲ ደስታ መልዕክት አስተለልፈዋል።

በሌላ በኩል፤ ሩስያ ምርጫውን ተከትሎ ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗን ገልጻለች። ኢራን ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቬትናም ፣ታጃኪስታን " የአንድ ቻይና " ፖሊሲን እንደምትደግፍ አረጋግጣለች።

ከአፍሪካ ደግሞ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሶማሊያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ድጋፍ በማሳየት ፤ ታይዋን የቻይና ግዛት ናት ስትል መግለጫ አውጥታለች። ከቀናት በፊት ቻይና " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት " ማለቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ስለምርጫው ምንም ባትልም አሁንም " የአንድ ቻይና " ፖሊሲዋ እንዳልተቀየረ አሳውቃለች።

ቻይና ታይዋንን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

ለጥያቄና መልስ ውድድራችን ዝግጁ ነዎት?
7ኛ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር ሐሙስ ጥር 9 ከቀኑ 6:30 በቴሌግራም ቻናላችን ይደረጋል፡፡ ቀላል ጥያቄዎች በመመለስ ይሳተፉ፤ ይሸለሙ፡፡ በየሳምንቱ አምስት አምስት አሸናፊዎች ይሸለማሉ! ዛሬውኑ የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ይሸለሙ!

የቴሌግራም ሊንክ https://t.iss.one/BoAEth

#telegram #giveaway #contest #Boa #bankinginethiopia #banksinethiopia #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
" በር ዘግተው መፈተሽ ጀመሩ የተወሰነውን ሰው እቃውን ወሰዱ የተወሰነውን መታወቂያውን ኮፒ አደረጉ። ፖሊሶች ናቸው " - የባህል ልብስ ነጋዴ

" ለእኔ መረጃው አዲስ ነው፣ ..ከታወቀ በኋላ ቦታው ላይ ይደወላል" - ፓሊስ

ሽሮ ሜዳ የሚገኙ አንዲት የልብስ ነጋዴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " አራት ሆነው መጥተው በሩን ዘጉት። በአንድ በኩል ብቻ በመሰላል መውጣት መግባት ይቻላል። ሌላውን በር ዘግተው መፈተሽ ጀመሩ የተወሰነውን ሰው እቃውን ወሰዱ የተወሰነውን መታወቂያውን ኮፒ አደረጉ " ብለዋል።

ፍተሻ ያደረጉት ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የባህል ልበስ መሸጫ የሚገኙ ከ280 በላይ ሱቆችን ዘግተው እንደሆነ፣ ከዚህ ውስጥ ከ10 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎችን እቃ፣ መታወቂያ ኮፒ አድርገው እንደወሰዱ ገልጸዋል።

እንዲህ ያደረጉት እነማን ናቸው ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ " ፓሊሶች ናቸው " የሚል ምላሽ ሰጥተው፣ " የኢትዮጵያ ባንዲራ እንሸጣለን። ባንዲራውን የምንሸጠው ለብቻው ሳይሆን ልብሱ ላይ ባንዲራ (ቲሸርቶች ላይ፣ የሀገር ባህል ልብስ ላይ) ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

የፓሊስ አባላቶች ምን እንድታደርጉ ነው የፈለጉት ? አታድርጉ የተባላችሁት ጉዳይ አለ ? ተብለው ሲጠየቁም፣ " ሥራውን አቁሙ አይሉም። ፍተሻ ይፈትሻሉ 'ባንዲራ አለወይ' ይላሉ ዞርዞር ብለው ያያሉ ያገኙባቸውን ሰዎች 'ምንድን ነው?' ይላሉ ነጋዴዎቹ ደግሞ 'የባንዲራ ልብስ ነው' ይላሉ። ከዚያ መታወቂያ ኮፒ ያደርጋሉ መታወቂያ፣ ስልክ ቁጥር ተቀብለው መዝግበው ይሄዳሉ " ብለዋል። 

ሌላኛዋ ቅሬታ አቅራቢ በበኩላቸው፣ " የባንዲራ ኅትመት ቲሸርት፣ የባህል ልብስ መሸጥ የጀመርነው ዛሬ አይደለም። ወይ አትሽጡ ብለው ማስጠንቀቂያ አልሰጡም፣ ሲጀመር መሸጣችንም ወንጀል አይደለም። ነገር ግን በፍተሻ ሰበብ ልብስ እየተወሰደብን ነው " ሲሉ አማረዋል።

የመጀመሪያዋ ቅሬታ አቅራቢ በበኩላቸው፣ "በህግ ላይ ያላቸው ግንዛቤ ምድነው? ህዝብ የሚያስተዳድሩት በህግ ነው ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም አይደል? ህዝብን ማስተዳደር የሚችለው አካል ግን ምንድነው እንዲህ ብጭርቅ ያለ ሀሳብ?" ሲሉ ጠይቀዋል።

አክለውም፣ "እንዲህ አይነት ነገር ሲደረግ ቅድመ ማስጠቀቂያ አይኖረውም ወይ? ኖርማሊ ባንዲራ መሸጥ በምን ዓይነት ህግ ነው ሰውን ሊያስጠይቅ የሚችለው?" የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

ነጋዴዎቹ፣ "ሌጋሊ የሆነ አሰራር ከሆነ እኛም ከመንግሥት ጋር እሰጣ አገባ አንፈልግምም፤ እንዲህ አይነት ነገር ሲደረግ ቅድመ ማስጠቀቂያ አይኖረውም? ግን የባህል ልብስ ላይ አድርጎ ባንድራ መሸጥ በምን ዓይነት ህግ ነው ሰውን ሊያስጠይቅ የሚችለው?" ሲሉ ጠይቀው፣ የአዲስ አበባ ፓሊስ መፍትሄ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ "ለእኔ መረጃው አዲስ ነው" የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም፣ "የአዲስ አበባ ፓሊስ ነው? የፌደራል ነው? ወይስ ከሌላ ቦታ የመጣ ፓሊስ ነው? የሚለው ከታወቀ በኋላ ቦታው ላይ ይደወላል” ብለዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በበኩላቸው እንዲህ የሚያደርጉት በወረዳው የሚገኙ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን አባላት መሆናቸውን አስረድተዋል።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC " ሀገራችን ሰላም ትሁን፤ የሃይማኖት ሰዎች እንደ ሃይማኖት እናስብ፣ እንደ ሃይማኖት እንናገር፣ አላስፈላጊ ጀግንነትን እንርሳው " - ብፁዕነታቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምን አሉ ? - የማይደፈር ሲደፈር አይተናል፤ ቤተክርስቲያን ስትደፈር ዝም አንልም። - " ፖለቲካው የፖለቲካው መስመር ሲደፈር ዝም እንደማይል ሁሉ እኔም ደግሞ የመጀመሪያዋም የመጨረሻዋም…
#ጥምቀት

" በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፈ ያለውን የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን አይወክሉም " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

በዓለ ጥምቀትን አስመልክቶ የሚተላለፉ መልእክቶች የቤተክርስቲያንን አስተምህሮ ላይ ብቻ ያተኮሩ እንዲሆኑ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መመሪያ አስተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው በተለያዩ ቋንቋዎች ለተለያዩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ቃለ መጠይቅና ምላሽ እንዲሰጡ ለተመረጡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰጡት አባታዊ መመሪያ የቅድስት ቤተክርስቲያን መልእክት የሚተላለፈው በማእከል በመሆኑ የማእከሉን መልእክት ብቻ እንዲያስተላልፉ መመሪያ የሰጡ ሲሆን ከግል አስተያየት መቆጠብ እንደሚገባም አበክረው አሳስበዋል።

ቤተክርስቲያኗ የሰላም ሰባኪ እንደመሆኗ መጠን የቤተክርስቲያን መልእክት ሲተላለፍ ሰላም ላይ ማተኮርና በዓል ለማክበር የሚወጡ ምእመናን በዓሉ በሰላም አክብረው እንዲመለሱ መልእክት ማስተላለፍ እንደሚገባ ግልጽ መመሪያ ሰጥተዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያዊ ሁሉም ሃይማኖቶች ተከባብረው የሚኖሩባት ሀገር መሆኗ ከሚገለጽባቸው መንገዶች አንዱ ይህ በዓል የሚከበርባቸውን ቦታዎች ለማጽዳትና ሥርዓት ለማስከበር ጥረት እያደረጉ ያሉ የሌሎች ሃይማኖት አባላትን በአባትነት ያመሰገኑት ብፁዕነታቸው ታቦታቱ በሚያልፉባቸው መንገዶች የሚገኙ የሌሎች ቤተ እምነቶችን ማክበር እንደሚገባ ለሁሉም ካህናትና ምእመናን አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፈ ያለውን የበዓል አከባበር ክልከላን የሚገልጹ የሐሰት ዜናዎች ቤተክርስቲያንን የማይወክሉና ቤተክርስቲያናችን በዓሉን በሰላም ለማክበር ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እያደረገች ያለውን ጥረት ከግንዛቤ ያላስገባ መሆኑን ብፁዕነታቸው አሳውቀዋል።

#EOTCTV

@tikvahethiopia