TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Jigjiga : የሶማሊላንድ ም/ ፕሬዝዳንት እና ልዑካቸው ጅግጅጋ ገብቷል። በሶማሊላንድ ም/ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ የተመራው ልዑክ ዛሬ ከሰዓት ጅግጅጋ መግባቱን የሱማሊ ክልል ማስ ሚዲያ ዘግቧል። ለም/ፕሬዝዳንቱና ልዑካቸው በቶግወጃሌ ከተማ የሶማሊ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች አቀባበል እንዳደሩጉለቸው ተገልጿል። የሶማሊላንድ ምክትል ፕሬዝዳንት አብዱረህማን አብዱላሂ ሰይሊኢ…
#Somali : የሶማሌ ክልል መንግስት ምስረታ የምክር ቤት ጉባኤ በጅጅጋ ከተማ ዛሬ እየተካሔደ ነው።

ባለፈው መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም በክልሉ የተካሄደውን 6ተኛ አገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ነው በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጅግጅጋ ከተማ አዲሱ የክልሉ ምክር ቤት የሚመሰረተው።

272 መቀመጫዎች ያለውና ዛሬ የሚካሔደው የክልሉ የምክር ቤት መስራች ጉባኤ የምክር ቤቱን አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ ይመርጣል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ የክልሉን ርዕሰ-መስተዳድር የሚመርጥ ሲሆን የተመረጡት ርዕሰ መስተዳድርም የክልሉን መንግስት አስፈጻሚ አካላት ሹመት በምክር ቤቱ አቅርበው ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የክልሉን አዲስ መንግስት የምስረታ ጉባኤ ለመታደም ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የመጡ እንግዶች ጅግጅጋ ከተማ ገብተዋል።

Credit : ENA

@tikvahethiopia
#Somali : የሶማሊ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የመሩት የሶማሊ ክልል የፀጥታ ኮሚቴ ሳምንታዊውን ስብሰባ ዛሬ አካሂዷል።

በፀጥታ ኮሚቴ ስብሰባው ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የፀጥታ አካላት የተገኙ ሲሆን፣ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።

ስብሰባው አራት ነጥቦችን በማውጣት የተጠናቀቀ ሲሆን እነዚህም ፦

1ኛ. ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን ትኩረት መስጠት፤
2ኛ. የክልሉን ውስጣዊ ሰላምና ፀጥታ ማጠናከር፤
3ኛ. ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ድንበር በንቃት መጠበቅና ሽብርተኛ ቡድኖች ወደ ክልሉ እንዳይገቡ መከላከል፤
4ኛ. የብሄር ግጭቶችን የሚያነሱ አካላት መከላከል የሚሉት ናቸው።

Credit : SMMA

@tikvahethiopia
#Somali

በሶማሊ ክልል ድርቅ በተከሰተባቸው አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ 200 ሚሊዮን ብር ፀደቀ።

የሶማሊ ክልል መንግሥት ካቢኔ ዛሬ 7ተኛ መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል።

ስብሰባው በጎዴ ከተማ ነው የተካሄደው።

ካቢኔው በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ በተለይ ድርቅ በተከሰተባቸው አከባቢዎች አስቸኳይ መልስ መስጠት የሚችልበት ሁኔታ ላይ በስፋት መክሯል።

በዚህም ድርቅ የተከሰተባቸውን አከባቢዎች ፈጣን መልስ ለመስጠት እና አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረስ 200 ሚልየን ብር ካቢኔው አፅድቋል።

#SRMMA

@tikvahethiopia
#Somali

በሶማሊ ክልል ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታ ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ፡፡

ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታ ክትባት ዘመቻ በቀብሪ በያ ወረዳ በገብሪ እና በጊሎ ቀበሌዎች የፌደራልና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ዛሬ በይፋ የተጀመረው።

@tikvahethiopia
#Somali : የሶማሌ ክልል የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በህብረተሰቡ መካከል ግጭት ለመቀስቀስ የተንቀሳቀሱ ሚዲያዎች እና ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።

የክልሉ መንግስት ኮሚዮኒኬሽን ቢሮ በህዝቡ መካከል የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ከዚህ በኋላ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሣስቧል።

የሶማሌ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አብዲቃድር ረሺድ ዱዓሌ ፥ " እነኚህ አካላት ለረዥም ዘመናት በመከባበርና አብሮ በኖሩ ማህበረሰብ መካከል የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ግጭት መቀስቀስን ዓላማቸው አድርገው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል " ብለዋል።

የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 ተላልፈው በመገኘታቸው ምክንያት እነኚህን አካላት ለህግ ማቅረብ መቻሉን ኃላፊው አስታውቀዋል።

" እነኚህ አካላት ብሄርን ከብሄር ማጋጨት አላማቸው አድርገው ቢንቀሳቀሱም የሶማሌ ህዝብ ከመንግስት፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሀይማኖት አባቶች እና ከጎሳ መሪዎች ጋር በጋራ የሚሰራ በመሆኑ የታሰበው ግጭት ሳይከሰት ቀርቷል " ሲሉ ሀላፊው አክለዋል።

ድርጊቱ በተለይ ሀገሪቷ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ባለችበት ሰዓት መፈፀሙ ደግሞ ጉዳዩን አሳሳቢ እንደሚያደርገው ገልፀው መንግስት ከዚህ በኋላ በመሰል ተግባር ተሰማርተው የሚንቀሳቀሱ አካላትን እንደማይታገስ ሀላፊው መናገራቸው የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

የክልሉ ኮሚኒኬሽን እርምጃ ተውስዶባቸዋል ስለተባሉት ሚዲያዎች እና ግለሰቦች በግልፅ ያሰፈረው ነገር ያለው የለም።

@tikvahethiopia
#ድርቅ

በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ያለው የድርቅ ሁኔታ ፦

#Oromia 📍

• በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች ባሉ 14 ወረዳዎች ብቻ 61 ትምህርት ቤቶች በድርቅ ምክንያት ተዘግተዋል።

• በምስራቅ እና ምዕራብ ሀረርጌ ፣ በቦረና ፣ በምዕራብ ጉጂ ፣ በምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በሚገኙ 70 ወረዳዎች ውስጥ በ605 ቀበሌዎች 2.8 ሚሊዮን ሕዝብ የመጠጥ ውኃ ይፈልጋል።

• 257 ሺ እንስሳት አቅም አንሷቸዋል።

• በቦረና እና ምስራቅ ባሌ ዞኖች አካባቢዎች ከ 3.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ድጋፍ ይሻሉ። ከነዚህ ውስጥ 8 ሺህ 244ቱ በአዲሱ ድርቅ ተጠቂ የሆኑ ናቸው።

• የውኃ ችግር ለማቃለልል 100 ውኃ ጫኝ ቦቴዎች ውኃ እያሰራጩ ይገኛሉ።

• ለ2ቱ ዞኖች 254 ሺህ ኩንታል እህል ለ853 ዜጎች ተልኳል።

#Somali📍

• 915 ት/ቤቶች ከሥራቸው ተስተጓጉለዋል። ከነዚህ 316ቱ ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል።

• በ83 ወረዳዎች 3.1 ሚሊዮን ሕዝብ ለውኃ እጥረት ተጋልጧል።

• 2.4 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥት ተጋልጧል። ከእነዚህ እና አጠቃላይ 3 ሚሊዮን 360 ሺህ ሕዝብ የምግብ ድጋፍ እንደሚሻም ተናግረዋል።

• ከሀምሌ እስከ የካቲት ባለው የድርቅ ጊዜ 864 ሺህ 43 እንስሳት መሞተዋል።

• 58 ሺህ 305 ሰዎች በድርቁ ተጠቅተዋል። እነዚህ ሰዎች ወደ ሌሎች ድርቅ ወዳልተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲሄዱ ተደርጓል።

• መንግሥት ከመስከረም እስከ ጥር ድረስ ለ1.7 ሚሊዮን ሰዎች 530 ሺ ኩንታል እህል እንዲከፋፈል አድርጓል።

• አሁን ላይ 159 የውኃ መጫኛ ቦቴዎች ለ 81 ወረዳዎች ውኃ እንዲያሰራጩ እየተደረገ ነው።

[ የብሄራዊ አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን 👉 ለጀርምን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የሰጠው መረጃ ]

@tikvahethiopia
#Somali #Afar

በሶማሌ እና አፋር ክልል አዋሳኝ ቀበሌዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት መፍታት እንዲቻል 2ቱ ክልሎች ከስምምነት መድረሳቸውን አስታወቁ።

ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ያስችላል የተባለው መሠረታዊ ስምምነት የታጠቁ ኃይሎች ከግጭት አካባቢዎች እንዲወጡ እና የፌደራል ፀጥታ ኃይሎች ወደነዚህ ቦታዎች እንዲገቡ የሚፈቅድ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን መናገራቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

በአዋሳኝ ቀበሌዎች በየቦታው ተኩስ ፣ ስርቆት እና መፈናቀል ይከሰቱ እንደነበር የተናገሩት አቶ ኢብራሂም ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀያቸው መመለስ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ኢብራሂም « ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ችግር እንዳይከሰት፣… ዘላቂ የሆነ ሰላም እንዲመጣ እና ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ሚና መሆን እንዳለበትም ነው ትናንት ከስምምነት ላይ የደረስነው።» ብለዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን ማሣረጊያ እንዲሆን የሁለቱ ክልሎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ኮንፈረንስ እንደሚያካሂዱም ተናግረዋል።

በሶማሌ ክልል መቀመጫ ጅግጅጋ በተካሄደው ውይይት የሰላም ሚንስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ጨምሮ የአፋር እና የሶማሌ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት ተገኝተው እንደነበር ሬድዮ ጣቢያው ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION ከ8 ወር በላይ ወደ ቄያቸው ያልተመለሱት የገደማይቱ ተፈናቃዮች የመፍትሄ ያለ እያሉ ነው። በገደማይቱ ሀምሌ 17 ቀን በነበረው ግጭት ምክንያት ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ በርካታ ዜጎች እስካሁን ወደ ቄያቸው መመለስ አልቻሉም። እነዚህ ዜጎች በየመጠለያው ካምፕ እና በየዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው ወራት ማለፋቸውን ገልፀውልናል። " ዞር ብሎ የሚያየን እና የሚጠይቀን አጥተናል " ያሉት…
#Afar #Somali

ዛሬ በአዳማ ከተማ የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ መሆኑን ለመስማት ተችሏል።

መድረኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

በውይይቱ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ፣የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሐመድና የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ይህን የሰሙ ከ9 ወር በላይ በግጭት ምክንያት ከገደማይቱ የተፈናቀሉ ወገኖች መፍትሄ እንዲያገኙ አቤት በለዋል። ችግር ተፈቶ ወደ ቀደመው ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱም ፣ ፍትህም እንዲያገኙ ጠይቀዋል።

በገደማይቱ ሀምሌ 17 በነበረው ግጭር ከመኖሪያ ቄያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች ወደቄያቸው አልተመለሱም።

እነዚህ ዜጎች በየመጠለያ ጣቢያ እና ዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት የተጠለሉ ሲሆን ዞሮ ብሎ የሚያያቸው እና የሚጠይቃቸውን እንዳጡ ለ20 እና 30 ዓመታት ከኖሩበት ቄያቸው ተፈናቅለው ያለፍትህ ሜዳ ላይ መቅረታቸውን ገልፀው እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬም ድረስ ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖች መፍትሄ እና ፍትህን ይሻሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somali #Afar #ሰላም #ውይይት

ትላንት የአፋርና የሱማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ኮንፈረንስ በአዳማ ተካሂዶ ነበር።

የሰላም ኮንፈረንሱ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት ዓላማ ያደረገ ነው መሆኑን ሰላም ሚኒስቴር አሳውቋል።

በአካባቢዎቹ የሚታዩ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ሰላምን ለማምጣት ወደ ግጭት ለሚያመሩ ጉዳዮችም መፍትሔዎች ተለይተው የተቀመጡበት መድረክ ነው ተብሏል።

የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ ማድረግ፤ በግጭት ምክንያት ከኖሩበት ቀዬአቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በዘመድ አዝማዶቻቸው ቤት ተጠልለው እየኖሩ ችግሮችን እየተጋፈጡ ያሉ ወገኖች ወደ ቀደመው ሰላማዊ ህይወታቸው እንዲመለሱ ሊደረጉ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችንም በመድረኩ መነሳቱን ከሰላም ሚኒስቴር በኩል የወጣው መረጃ ያሳያል።

ባለፈው ዓመት በተነሳ ግጭት ከዘጠኝ ወር በላይ ቤታቸው ተፈናውለው በየመጠለያ ጣቢያ እና በየዘመዶቻቸው ቤት የተጠለሉ በርካታ ወገኖች እንዳሉ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Somali

የሶማሌ ክልል ፀጥታ ቢሮ ፤ ከሰሞኑን በጅግጅጋ ኤርፖርት በፀጥታ ኃይል ከተገደሉት ጄዌሪያ መሀመድ ጋር በተያያዘ ህዝቡን እና ከተማውን ለማበጣበጥ ፣ ሁከት እና ግርግር ለመፍጠር እንዲሁም ሌብነትና ዘረፋ ለመፈፀም ፍላጎት ያላቸው አካላት መኖራቸውን ጠቁሞ ህዝቡ እነዚህን አካላት አይሆንም ሊላቸው/ሊገስፃቸው እንደሚገባ መንግስት ግን እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ቢሮው የጄዌሪያን መሀመድ መገደልን ተከትሎ የተለያየ አይነት ስሜትና ፍላጎት ያላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ይስተዋላሉ ብሏል።

አንደኛ፦

በድርጊቱ በጣም ያዘኑ እና ሀዘናቸውንም በአግባቡ መግለፅ የሚፈልጉ ፍትህ እንዲገኝ የሚጠይቁ ናቸው።

ሁለተኛ፦

በዚህ የሀዘን ድባብና ክፉ ድርጊት ጥቅማቸውን የሚፈልጉ ሁከት እና ግርግር እንዲባባስ የሚፈልጉ በዚህ አጀንዳ ተሸጋግረው ሌላ ጥቅም የሚፈልጉ ናቸው።

ሶስተኛ፦

ፖለቲካዊ ፍላጎት ባይኖረውም ግን የሌብነት፣ ዘረፋ እና ብጥብጥን በውስጡ የያዘ ነው፤ ቢሮው፤ እንደዚህ አይነት ፍላጎት ያላቸው አካላት በዚህ አይነት ምክንያት ሌላው ላይ ተፅእኖ በመፍጠር ትላንት በባለፈው ስርዓት ጊዜ እንዳደረጉት ህዝብና ከተማን መበጥበጥ እና መዝረፍ የሚሹ አካላት የሚታወቁና ያልተደበቁ ናቸው ብሏል።

ትላንት የደረሰው ግፍና ተፅእኖ፣ መከራ እና ችግር ከግምት በማስገባት መንግስት የሚያደርገውን ትዕግስት ወደ ጎን በማየት በዚህ አይነት ተልዕኮ የሚሰማሩትን ህዝቡ የትላንቱን አይነት ጥፋት መድገም የለባችሁም በማለት ሊገስፃቸውና አይሆንም ሊላቸው ይገባል ብሏል ቢሮው።

ለክልሉ ህዝቦች አብሮነት ማይጠቅም፤ የነበረውን አንድነትና ህብረት የሚያበላሽ አይነት ፍላጎት ለ2ኛ ጊዜ እንዲመለስ መንግስት አይፈቅድም ያለው የፀጥታው ቢሮ እንዲህ አይነት አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Afar #Somali🚨

" የግጭቱ ማገርሸት ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት ሆኗል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ማገርሸቱ ገልጿል።

ኮሚሽሙ ግጭቱ እንዳሳሰበውም አመልክቷል።

ኢሰመኮ በቅርቡ በሚያዚያ ወር የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በሶማሊ ክልል ሽንሌ ዞን እና አፋር ክልል አዋሳኝ ያገረሸው ግጭት አሳሳቢ ነው ብሏል።

ግጭቱ ለሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀል ምክንያት እንዳሆነ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሰኢድ ደመቀ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃል ፤ " የአሁኑ ግጭት የተጀመረው ከግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም 2024 ወዲህ ነው " ብለዋል።

" በግጭቱ የተወሰኑ ሰዎች ሞት፤ መፈናቀል እና የአካል ጉዳት፤ የንብረት መውደም እንደደረሰ ነው ያለው መረጃ በእኛ በኩል ግጭቱ እንዳገረሸ። በትክልል ስንት ሰው ሞተ፤ ቆሰለ የሚለውን ገና በምርመራ የምናጣራው ነው " ብለዋል።

" በአሁኑ ወቅት ግን ጠቅለል ባለ መልኩ የሰው መፈናቀል፤ ሞት እና ጉዳት እንዳለ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኢሰመኮ ከሁለቱ ክልሎች የመንግስት አስተዳዳሪዎች ተረዳሁት ባለው መሠረት ፥ በሁለቱም ክልሎች በኩል የሰላማዊ ሰዎች ግድያ እና መፈናቀሎች ተፈጽሟል።

በቅርቡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለተገኘው አዎንታዊ የሰላም ማስፈን ሂደት ሁለቱ ክልሎች ያሰጡትን አዎንታዊ ምላሽ ያደነቀው ኢሰመኮ፤ የተጀመረው የሰላም ጥረት እንዲቀጥል የፌዴራልም ሆነ የሁለቱ ክልሎች መንግስታት የቀጠለውን ግጭት እንዲያስቆሙት ጥሪውን አቅርቧል።

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የፌዴራል መንግስት አስቸኳይ የግጭት ማስቆም ጥረት እንዲያስደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሁለቱ ክልሎች አስተዳዳሪዎች በቀጣይ ሕዝበ ሙስሊሙ ከሚያከብረው የኢድ አል-አደሃ በዓል አስቀድሞ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

#DWAmharic #EHRC

@tikvahethiopia