TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ አሴት (ካፒታል) ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በደብረ ማርቆስ ኢንዱስትሪ ፓርክ #ሊሰማሩ ነው፡፡ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን #ደብረ_ማርቆስ ቅርንጫፍ ጽ.ቤት ለ12 ባለሀብቶች ቦታ፣ ካርታና የቦታ ፕላን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ብርሃን🔝"የጉዞ አድዋ" የእግር ተጓዦች #ደብረ_ብርሀን ከተማ ገብተዋል።

ፎቶ፦ ጌትነት አሰፋ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› ሕወሓት

‹‹ትዕግሥት ሁሌ ስለማይሠራ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል›› ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል
.
.
የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር #ደብረ ጽዮን_ገብረሚካኤል ‹‹ሕገ መንግሥቱ እየተጣሰ ትዕግሥት የሚባል ነገር ሁሌ አይሠራም፣ ዕርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፤›› ሲሉ ለክልሉ ቴሌቪዥን ተናገሩ፡፡

በአገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ሕገ መንግስቱ የሚጣስበት እና በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ #ጥቃቶች የሚሰነዘሩበት ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ፡፡

ሕወሓት 44ኛ አመት የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ድርጅቱ እና ደጋፊዎቹ የምሥረታ በዓሉን የሚያከብሩት በኢትዮጵያ የተጀመረው ዕድገት ወደ ኋላ እየተቀለበሰ ባለበት ወቅት ነው ብሏል፡፡

ለተጠቀሰው ችግር ዋነኛው መንስኤ የኢሕአዴግ አመራር ውስጥ የተፈጠረው #አለመግባባት እና የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነት መሆኑንም መግለጫው ይናገራል፡፡

‹‹የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል›› የሚለው የሕወሓት መግለጫ ትችቱን እንደሚከተለው ያቀርባል፡፡

‹‹በስመ ለውጥ ለአገራቸው ክብርና ሉዓላዊነት መረጋገጥ ዕድሜ ልካቸውን የደከሙና የለፉ የሚረገሙበትና የሚብጠለጠሉበት፣ በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በዜጎች ላይ የተለያዩ በደሎችና ግፍ የፈጸሙ፣ እንዲሁም የአገራቸውን ሉዓላዊነት አሳልፈው የሰጡ ብቻ ሳይሆን፣ ከሌሎች የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አብረው አገርና ሕዝብ የወጉ የሚመሠገኑበትና ክብር የሚሰጥበት የክህደት ዘመን ላይ ደርሰናል፤››

ይሁን እንጂ የአገሪቱ ሁኔታ ሕወሓት ካወጣው መግለጫ በተቃራኒ እንደሆነ በርካቶች ይገልጻሉ።

ከምንጊዜውም የተሻለ ዴሞክራሲ የሰፈነበት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የቆሙበትና ቀደም ሲል ለተፈጸሙ ጥሰቶችም ፍትሕ የተሰጠበት መሆኑን የአገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ የውጭ መገናኛ ብዙኃንና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በይፋ እየተናገሩ ናቸው።

በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችና የዜጎች መፈናቀል መኖር እርግጥ ቢሆንም፣ የፖለቲካ ሽግግር ከዚህ የፀዳ ሊሆን እንደማይችል ነገር ግን ይህ ችግር እየደበዘዘ መሄድ እንዳለበትና በአሁኑ ወቅትም መረጋጋት መኖሩን ያስረዳሉ።

ሕወሓት በፖለቲካ ማዕከሉ ላይ የነበረው ተፅዕኖ በመቀነሱ የመገፋት ስሜት ሊጫነው እንደሚችል፣ ይኼንንም የሚያባብሱ የፖለቲካ ትግሎች በኢሕአዴግ ውስጥ መቀጠላቸው በግልጽ የሚታይ ቢሆንም፣ ጉዳዩን ከሕዝብ ጋር ማገናኘት ስህተት እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ልሂቃን በተለያዩ መድረኮች በተደጋጋሚ የሚያነሱት ሐሳብ ነው።

የካቲት 13፣ 2011

ምንጭ - ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀን ማስተካከያ፦

#StopHateSpeech በዚህ ሳምንት የሚደረጉት መድረኮች ላይ የቀን ማስተካከያ ተደርጓል። በዚህም መሰረት፦

#ረቡዕ የጉዞ መነሻ ከሀዋሳ፣ወልቂጤ፣ ከአርባ ምንጭ፣ ከወ/ሶዶ ከተሞች --- #ደብረ_ብርሃን ይታደራል።

√ሀሙስ - ወሎ ዩኒቨርሲቲ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

√አርብ - ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጋር ውይይት ይደረጋል።

√ቅዳሜ - መቐለ ዩንቨርስቲ ልዩ ዝግጅት ተዘጋጅቷል።

አዲስ ነገር...👇

በዚህ ዘመቻ ላይ በወጣቶች ብቻ የተመሰረተ የሙዚቃ ባንድ ይቀላቀለናል፤ በረቂቅ ሙዚቃም ፍቅር እና ሰላምን ይሰብካሉ። እንዲሁም በሴቶች ላይ ስለሚነገሩ እና ስለሚሰነዘሩ የጥላቻ ንግግሮች ግንዛቤ ለመስጠት #መራሂት እና #ያንቺ_ንቅናቄ በሴቶች ላይ የሚሰሩ ቡድኖች አብረውን ይጓዛሉ።


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረ_ማርቆስ

በሕገ-ወጥ መንገድ 192 ኩንታል ማኛ ጤፍ ያከማቸው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ተመስገን ያዬ እንደተናገሩት የጤፍ ምርቱ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ያወጣል፡፡ ግለሰቡም የንግድ ፈቃድ እንደሌለው ነው ያስታወቁት፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋለውም በኅብረተሰቡና በፖሊስ ትብብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምርትን በሕገ ወጥ መንገድ በመከዘንና የዋጋ ግሽበትን በማባባስ ኅብረተሰቡን የሚያማርሩ ግለሰቦችን ለማስተካከል በከተማ አስተዳድሩ የመቆጣጠሪያ አሠራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሆነም ነው አቶ ተመስገን የተናገሩት፡፡ ሕገ-ወጥ ንግድን በመከላከሉ ተግባር ኅብረተሰቡም ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

Via #AMMA
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረ_ብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

ተመራቂዎች በኢትዮጵያ እየታዬ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና ዘረኝነት እንዲታገሉ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አሳሰበ፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተከታታይ ሶስትና ከዚያ በላይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን ከ3 ሺህ በላይ ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 64 ተማሪዎች ማስመረቁ ታውቋል፤ 1 ሺህ 226 የሚሆኑት ደግሞ ሴቶች ናቸው፡፡

የዩኒቨርሲቲው ተወካይ ፕሬዝዳንት ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ ተመራቂዎች ያካበቱትን እውቀት ተጠቅመው ሕዝባቸውን እና ሀገራቸውን በታማኝነት እና በቅንነት እንዲያገለግሉ መልዕክት አስተላፈዋል፡፡

በኢትዮጵያ እየታዬ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና ዘረኝነት ለመታገልም በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮውን ሳይጨምር ከ26 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ማስመረቁ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🎂TIKVAH ETHIOPIA~2 ዓመት🎂

#ደብረ_ብርሃን #ወሎ #ጅማ #ሀረማያ #ሀዋሳ #ወልቂጤ #መቐለ #ወልዲያ #ወላይታ_ሶዶ #አርባምንጭ #ሆሳዕና/#ዋቸሞ/

📎የሰውልጅ በሰውነቱ የሚከበርበት፤ የግለሰቦች አመለካከት፣ እምነት፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ የኔ ነው የሚሉት ሁሉ የሚከበርበት፤ ፍቅር፣አንድነትና መተባበር የነገሰበት፣ የሰው ልጅ ሁሉ መሰብሰቢያ የሆነች ከጥላቻ የራቀች ሀገር እንገነባለን!! ተባብረን እንሰራለን፤ ለመጭው ትውልድ ኢትዮጵያን እናወርሳለን!!

እኛ ስንኖር ኢትዮጵያ ትኖራለች፤ ኢትዮጵያ ስትኖር እኛም እንኖራለን!

#ድፍን_ሁለት_ዓመት_በፍቅር_በመተባበር!

ነገ 6:00 አበበች ጎበና የህፃናት እንክብካቤ እና ልማት ድርጅት እንገናኝ፤ ከእናታችንም ምርቃት እንቀበል!! ሁላችሁም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ናችሁ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ደብረ_ማርቆስ_ዩንቨርስቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ከዳያስፖራው ጋር በመተባበር የአዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገንባት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ እንዳስታወቁት፣ ዩኒቨርሲቲው የአዳሪ ትምህርት ቤቱን ለማስገንባት መሬት ተረክቧል፤ የሕንፃው ዲዛይን ሥራ እያሰራ ይገኛል፡፡ በቅርብ የዲዛይን ሥራው ተጠናቆ በ2012 ዓ.ም የግንባታ ሥራው ይጀመራል። ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ለሚያሰራው የአዳሪ ትምህርት ቤት የሥርዓተ ትምህርት ጥናት አስጠንቶ መጨረሱን የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ከዚህም በተጨማሪ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ዳያስፖራው ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛ በመሆኑ ትምህርት ቤቱ ጠንካራና የተሻለ ሀገራዊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ? የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። #ባህርዳር ነዋሪ 1 " ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ። መከላከያው…
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ?

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

#ባሕርዳር

ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ' ኢትዮጵያ  አየር መንገድ በረራ ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

#ደብረ_ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

" ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው። " ያሉ አንድ ነዋሪ " ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

#ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

#ጎንደር

ከትላንት #ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

#ላሊበላ

" ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም " የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

#ደብረታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ  ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም  በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስለ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

NB. የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦
- በባህር ዳር ፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በደብረ ብርሃን፣
- በላሊበላ ፣
- በጎንደር ፣
- በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት #ግዴታ_እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia