TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#IFTAR

ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል።

ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ።

ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ አርብ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል።

በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን 15 (ሚያዚያ 8) በድሬዳዋ ከተማ " የአብሮነት ኢፍጣር በድሬዳዋ " በሚል በምድር ባቡር ለገሃር አደባባይ ይካሄዳል፤ በዕለቱ በአብሮነት ከማፍጠር ባለፈ የቁርዓን እጥረት ላለባቸው ከተሞች ቁርዓን የሚሰበሰብ ሲሆን እስከ 1000 ቁርዓን ለማሰባሰብ ታቅዷል።

በተጨማሪ የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 9 በኮምቦልቻ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት መዘጋጀቱ ተሰምቷል።

እንዲሁም በሀረር ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር ሚያዚያ 9 ከራስ ሆቴል እስከ ጁምዓ መስጂድ ድረስ ይካሄዳል ተብሏል።

በሌሎችም የሀገራችን ከተሞች ላይ ተመሳሳይ ስነ ሥዓቶችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

ፎቶ ፦ ደሴ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#IFTAR ዛሬ በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ይካሄዳል። ለዚህም ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ። ከደሴ ከተማ ኮሚኬሽን ቢሮ ባገኘነው መረጃ ዛሬ አርብ የሚካሄደው ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት እንደ አምናው " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ሲሆን ለደሴ ከተማ የክርስትና እምነት የተከታዮችም " ኑ በጋራ እናፍጥር " ውብ የሆነውን የወሎን እሴት እናስቀጥል የሚል ጥሪ ቀርቧል። በሌላ መረጃ ነገ ቅዳሜ ረመዳን…
#IFTAR

በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሄደ።

በደሴ ከተማ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ተካሂዷል።

የኢፍጣር ስነስርዓቱ ከ " ፒያሳ እስከ መናኸሪያ " ባለው ጎዳና ላይ የተካሄደ ሲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የደሴ ከተማ ነዋሪ ታድሟል።

በሌላ በኩል ደሴ የረመዳንን በዓል አስመልክቶ " ከኢድ እስከ ኢድ " በተሰኘው መርሃ ግብር ደሴ የሚገቡ እንግዶችን ለማስተናገድ እየተዘጋጀች ትገኛለች።

ፎቶ፦ ሶሻል ሚዲያ የተሰባሰበ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ "ነሲሓ" ኢፍጣር ፕሮግራም ! «ነሲሓ» የተሰኘ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት፤ በዛሬ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ጎዳናዎች ላይ 12 ኪ.ሜ የሸፈነ ጾመኞችን የማስፈጠር መርሃ ግብር አካሂዷል። የቦታዎቹ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው። ①) ዓለም ባንክ ከሚገኘው ኢማሙ አሕመድ መስጂድ አደባባይ ጀምሮ እስከ ቤተል ባለው መንገድ፣ ②) ከቢላል ኮካ መስጂድ ወደ አብነት ባለው መንገድ በጭድ ተራ…
#Iftar

በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት (NCDO) አስረባባሪነት ዛሬ በመዲናችን አዲስ አበባ በተመረጡ 11 ጎዳናዎች ላይ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ይካሄዳል።

«ኑ አብረን በጋራ እናፍጥር!» በሚል የሚካሄደው ይህ የኢፍጣር መርሃ ግብር 35 ኪሎ ሜትር ገደማ ይሸፍናል።

የሚያካትታቸው 11 ጎዳናዎች ዝርዝር ፦

1) ከኮካ ቢላል መስጂድ - ተክለሃይማኖት
2) ከእህል በረንዳ - ቢላል መስጂድ
3) ከቢላል መስጂድ - እፎይታ
4) ከኮልፌ ቀብር - ሎሚ ሜዳ
5) ከአስኮ አዲስ ሰፈር - በድር መስጂድ
6) ከመንዲዳ - ኢማሙ አሕመድ መስጂድ
7) ከአየር ጤና - ግራር
8) ከግራር - ስልጤ ሰፈር
9) ከጀሞ 2 አደባባይ - ኖክ
10) ከረጲ ትም/ቤት - አጃምባ ማዞሪያ
11) ከአየር ጤና እስከ አለም ባንክ
አቅሙ ያለው ሰው በዕለቱ ኢፍጣር በሚካሄድባቸው ጎፋናዎች ሲያቀና እንደ ውሃና ቴምር ያሉ ቀለል ያሉ ማስፈጠሪያቸውን ለሌሎች ቢይዝ መልካም ነው ተብሏል።

ነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ባለፈ አመት በ6 ጎዳናዎች ላይ ደማቅ የኢፍጣር ፕሮግራም ማካሄዱ ይታወሳል።

ተቋሙ በዚህም አመት ረመዷን ከገባ ጀምሮ በየቀኑ 250 ሰዎችን በቋሚነት እያስፈጠረ ሲሆን በክልል ከተሞች በሚገኙ ቅርንጫፎቹ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በትጋት እየሠራ እንደሚገኝ ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ዛሬ በሚካሄደው የኢፍጣር ፕሮግራም አጋር መሆን የሚፈልጉና አቅመ ደካሞችን ማስፈጠር ለሚፈልጉ 0972747474 ላይ መደወል ይችላሉ ተብሏል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#IFTAR በደሴ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሄደ። በደሴ ከተማ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት " ኑ በጋራ እናፍጥር" በሚል ተካሂዷል። የኢፍጣር ስነስርዓቱ ከ " ፒያሳ እስከ መናኸሪያ " ባለው ጎዳና ላይ የተካሄደ ሲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የደሴ ከተማ ነዋሪ ታድሟል። በሌላ በኩል ደሴ የረመዳንን በዓል አስመልክቶ " ከኢድ እስከ ኢድ " በተሰኘው መርሃ ግብር ደሴ የሚገቡ…
#Iftar

የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው።

አርብ በደሴ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጧር መካሄዱ ይታወሳል።

ትላንት ደግሞ በቡታጅራ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ኢፍጧር ከማርስ ታወር ህንፃ - መናኸሪያ ድረስ ተካሂዷል (ፎቶው ከላይ ተያይዟል) ። ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኢኽላስ በጎ አድራጎት ማህበር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀውልናል።

በአሁን ሰዓት ደግሞ በኮምቦልቻ እና ሀረር ከተማ የኢፍጣር ስነ ስርዓት ለማካሄድ ዝግጅት እየተካሄደ ነው የሚገኘው።

(በሌሎች አካባቢዎች ላይ ያለውን ተከታትለን እናሳውቃለን)

ፎቶ ፦ ከቡታጅራ (ሚያዚያ 8)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Iftar የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት በተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ነው። አርብ በደሴ ለሁለተኛ ጊዜ ታላቅ የሆነ የጎዳና ላይ ኢፍጧር መካሄዱ ይታወሳል። ትላንት ደግሞ በቡታጅራ ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ኢፍጧር ከማርስ ታወር ህንፃ - መናኸሪያ ድረስ ተካሂዷል (ፎቶው ከላይ ተያይዟል) ። ዝግጅቱን ያዘጋጀው ኢኽላስ በጎ አድራጎት ማህበር መሆኑን አዘጋጆቹ ገልፀውልናል። በአሁን ሰዓት ደግሞ በኮምቦልቻ…
#Iftar

#Assosa #Kombolcha #AA #Harar #Metu #Tullubolo

ዛሬ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ላይ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በተለይም በታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ሀረር ከተማ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምዕመን በተገኘበት ነው የአፍጥር ስነ ስርኣቱ የተካሄደው።

በኮምቦልቻ ከተማ ፥ ዛሬ ሁለተኛው የጎዳና ላይ ኢፍጣር " ኑ አብረን እናፍጥር " በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል። በስነስርዓቱ ላይ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ባለፈ የሌሎች እምነት ተከታዮች የተገኙ ሲሆን ስነስርኣቱ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።

በመዲናችን አዲስ አበባ ደግሞ በነሲሓ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት አስተባባሪነት ዛሬ በ11 ጎዳናዎች ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዶ በሰላም መጠናቀቁን አዘጋጆች አሳውቀውናል።

በተጨማሪ ዛሬ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች መካከል አሶሳ አንዷ ስትሆን ፤ ስነ ስርዓቱ በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች አስተባባሪነት ነው የተካሄደው። በመርሃ ግብሩ ላይ ወላጅ አልባ እና አቅመ ደካሞች፣ አረጋዊያን እና ደጋፊ የሌላቸው ወገኖች ከከተማው ሙስሊም ህብረተሰብ ጋር በጋራ አፍጥረዋል።

በአፋር ክልል ዱብቲ ከተማም ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል ፤ " አንድነታችንን እያጠናከርን ኑ በጋራ እናፍጥር " በሚል መሪ ሀሳብ ነው የተካሄደው።

በመቱ እና በቱሉቦሎም ዛሬ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

@tikvahethiopia
#IFTAR

ዛሬ እና ትላንት በተለያዩ ከተሞች ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ታካሂዷል።

የኢፍጣር ስነስርዓት ከተካሄደባቸው ከተሞች አንዷ መዲናችን አዲስ አበባ ስትሆን በቤተል አደባባይ ታላቅ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

በደ/ወሎ ልጓማ ከተማ፣ ሶማሌ ክልል ቀብሪደሃር ከተማ ፣ በወራቤ ከተማ ፣ በአፋር ማንዳ ከተማ ፣ በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ፤ ኬራቴ ከተማ ፣ ሻሸመኔ ከተማ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

ትላንት ደግሞ ፤ በለገጣፎ ለገዳዲ ፣ በጅማ ዞን ኦማንዳ ወረዳ ፣ በኢሊአባቦር ዞን አልጌ ሰቺ ወረዳ ፣ ሰንዳፋ በኬ ፣ ቡራዩ ፣ ቢሾፍቱ ከተማ ፣ ጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ፣ በወልቃይት ሁመራ እና በወልቂጤ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

የሁሉንም የጎዳና ላይ ኢፍጣር ፎቶዎች ይመልከቱ ፦ https://telegra.ph/Iftar-04-22

@tikvahethiopia
#Iftar

ዛሬና ትላንት ቅዳሜ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዷል።

ዛሬ በአፋር ክልል መዲና ሰመራ ከተማ ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ስነስርዓት የተካሄደ ሲሆን በጅማ ከተማም እጅግ ከፍተኛ የሰው ቁጥር የተገኘበት የኢፍጣር ስነሥርዓት ታካሂዷል።

በተመሳሳይ ዛሬ በአጋሮ የኢፍጣር ስነስርዓት ተካሂዳል።

ትላንት በአፋር ኤሊደአር ፣ ስልጤ ዞን ቃዋቅቶ እና በቂልጦ ከተማ፣ ሰሜን ምዕራብ ሸዋ ጎሮ ወረዳ፣ በአርሲ ነጌሌ፣ ባሌጎባ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ ፥ የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 18 በአዳማ ከተማ፣ ረቡዕ ሚያዚያ 19 ደግሞ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጎዳና ላይ ኢፍጣር ስነስርዓት እንደሚካሄድ ታውቋል።

በተጨማሪ ከጥቂት ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚካሄደው ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

ፎቶዎች ፦ telegra.ph/Iftar-04-24

@tikvahethiopia