TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" አጠቃላይ ሂደቱ ህግን የተከተለ ነበር " ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ትላንት ምሽት የአሜሪካ ጉዟቸውን ለማድረግ በአዲስ አበባ ኤርፖርት በተገኙበት ወቅት " ከቅዱስነታቸው ጋር ሕገ ወጥ ቅርስ ከሀገር ሊሸሽ ሲል ተያዘ " እየተባለ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑ ተገልጿል። ቅዱስነታቸው…
#ነገ_መግለጫ_ይሰጣል !

በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዞ ላይ በቦሌ ኤርፖርት በተፈፀመው አሳዛኝ ድርጊት ጋር ተያይዞ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነገው ዕለት ቀን 8:30 መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል።

ብፁዕነታቸው ስለተፈፀመው ድርጊት መረጃውን እንደሰሙትና እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ወጡ የተባሉት ጽላትና ንዋያተ ቅድሳት በሕጋዊ መንገድ መውጣታቸውንና ለዚህም ሕጋዊ ፍቃድ መያዛቸውን ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ይህ ለአዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትም ሆነ ድርብ ለሚፈልጉ አብያተ ክርስቲያናት በሀገረ ስብከታቸው ጥያቄ መሰረት በመንበረ ፓትርያርክ ፍቃድ የሚሰጥ አስቀድሞ የነበረ የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አሠራር ነው ብለዋል።

#EOTC_TV

@tikvahethiopia