TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ለጉምሩክ ሰራተኞች ' ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቃለሁ ' በሚል 1 ሚሊዮን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ ትራንዚተር እጅ ከፍንጅ ተይዟል " - ፌዴራል ፖሊስ " ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " ብሎ ከባለ ጉዳይ የ1 ሚሊየን ብር ቼክ ሲቀበል የነበረ አንድ ትራንዚተር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። " ጉቦ ሰጥቼ መኪኖችህን አስለቅቅልሃለሁ " ብሎ…
የጉምሩኩ ታንዚተር #ክስ ተመሰረተበት።

1 ሚሊየን ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል በተባለው የጉምሩክ ትራንዚተር (አስተላላፊ) ግዑሽ አዳነ ላይ የሙስና ወንጀል ክሥ ተመሰረተ።

ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

የሙስና ወንጀል ክሱ ዝርዝር ላይ ምን ይላል ?

- ተከሳሹ በሚሰራው የጉምሩክ አስተላላፊነት ስራ መሰረት ከቀረጥ ነጻ ለኢንቨስትመንት የገባን " ቶዮታ ሀይሉክስ " ተሽከርካሪ ነብዩ ቡሽራ ከተባለ የግል ተበዳይና 1ኛ የዓቃቢ ሕግ ምስክር ከሆነው ግለሰብ ጋር በመሆን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ለመፈፀም በመስማማት የግል ተበዳይን የ7 ዓመት የመኪናውን ቀረጥ እና ታክስ 1 ሚሊየን 511 ሺህ 356 ከ66 ሣንቲም እንዲከፍሉና ተሸከርካሪውን በአካል እንዲያቀርቡ ይናገራል።

- የግል ተበዳይ በኅዳር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ልዩ ቦታው " ሳሪስ አቦ "ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ሲቀርቡ ተከሳሹ ተሽከርካሪው ለጥያቄ እንደሚፈለግ እና መሿለኪያ ኃይሌ ይርጋ ሕንጻ ላይ በሚገኘው የጉምሩክ ዋና መሥሪያ ቤት መጠየቅ እንዳለባቸው ይገልጸል።

- በዚህም ተሽከርካሪው እንዲለቀቅ #ከጉምሩክ_ኮሚሽን_ኃላፊዎች ጋር #እንደሚያደራድራቸው ለግል ተበዳይ በመንገር እና መኪናውን ለመልቀቅ የግል ተበዳይ 1 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ #ኃላፊዎች_መግለፃቸውን በማሳወቅ በኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 7 ሠዓት ከ30 አካባቢ ቦሌ መድሃኒያለም አከባቢ ልዩ ቦታው " ኦኬዥን ካፌ " ውስጥ ከግል ተበዳይ ጋር በመገናኘት 1 ሚሊየን ብር በአቢሲኒያ ባንክ የተጻፈ ቼክ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ዐቃቢ ህግ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።

ዐቃቤ ሕግ ከክስ ዝርዝሩ ጋር የሰውና የሠነድ ማስረጃ አያይዞ አቅርቧል። ተከሳሹ ችሎት ቀርቦ ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የክስ ዝርዝሩ በችሎት በንባብ ተሰምቷል።

መረጃው የኤፍቢሲ ነው።

@tikvahethiopia