#AddisAbaba
በቀድሞ የአርበኞች ግንቦት 7 አባል የነበሩት አቶ ጃንከበድ ዘሪሁን ረቡዕ ጠዋት ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ/ም አባዶ 'መስቀለኛ' አካባቢ ከመኖሪያ ቤታቸው በፓሊስ ወደ ሜክሲኮ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደው እስከ 8፡00 ቢቆዩም ከዚያ በኋላ ወዴት እንደተወሰዱ ባለማወቃቸው ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን ቤተሰቦቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የፓሊስ አባላት ' በወቅታዊ ጉዳይ ' ብለው እንደወሰዷቸው ያስረዱት የአቶ ጃንከበድ የቅርብ ቤተሰብ፣ "ቢያንስ ያሉበትን ማሳወቅ መቻል አለባቸው የመንግሥት አካል እንደመሆናቸው። ቤተሰብ የመጠየቅ፣ የመጎብኘት፣ ጠበቃ የማግኘት መብቱን አላከበሩም። ያለበትን ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደሉም " ሲሉ ወቅሰዋል።
ሌላኛው ቤተሰብ በበኩላቸው፣ ፓሊስ ጋ ካለ ' እኛ ጋ አለ ' እንዲሏቸው፣ የተጠረጠረበትን ጉዳይ በግልጽ እንዲያሳውቋቸው ጠይቀው፣ " ኮንፈርሜሽን ለእኛ ትልቅ ርሊፍ ነው። ለሕይወቱ በጣም ያስጋል " ብለዋል።
በተጨማሪም፤ ፍ/ቤት አልቀረበም። #የፈጸመው ወንጀል ስለመኖሩና ስለተጠረጠረበት በግልፅ #አልተነገረንም። እባካችሁ በመንግሥት ቁጥጥር ስር ከሆነ መረጃ ይሰጡን ዘንድ የሚመለከተውን አካል ጠይቁልን፤ የደረሰበትን ማወቅ አልቻልንም ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአቶ ጃንከበድ ቤተሰቦች ጥያቄ ይዞ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስን አነጋግሯል።
ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የሚሰሩት ዋና ኢንሰፔክተር ታደለ ፣ " በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለሆነ አንድ ሰው ብቻ አይደለም እዚህ ላይ ሀሳብ መስጠት ያለበት " ብለዋል።
" እዚህ ላይ እኔ የማውቀው፣ የሰማሁት ነገር የለም። መረጃው የለኝም። ስለዚህ ጉዳዩ እኛን የሚመለከት አይደለም " ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ፣ " በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ከሆነ፣ ይጠየቃል፣ ይጣራል ጉዳዩ ማለት ነው። በሕግ ሂደት የሚታይ ይሆናል " ብለዋል።
ታዲያ እዲህ ቢሆን እንኳ ተጠርጣሪዎች ያሉበትን ቦታ ማሳወቅ የለባችሁም ወይ ? ሌላ ጭንቀት ቤተሰብ ላይ ከሚፈጥር ተብሎ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኢንስፔተሩ፣ " የት ይሄዳል ያው ማቆያ ነው የሚሆኑት ሰው ሲያዝ፣ በወንጀል የተጠረጠረ ሰው ማቆያ ነው በሕግ እስኪወሰንበት ድረስ " ሲሉ አክለዋል።
ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር ኮማደር ማርቆስ ታደሰ በበኩላቸው፣ ስለጉዳዩ መረጃው እደሌላቸው፣ ማንኛውም የተጠረጠረ ሰው ሊያዝ እንደሚችል፣ ስለሆነም ተያዙ የሚባሉት ግለሰብ ምናልባት ተጠርጥረው በአድስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ተይዘው ከሆነም ሊቀመጡ የሚችሉት በተያዙበት ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ሊሆን እደሚችል ገልጸዋል።
አክለውም፣ ተያዙ የሚባሉት ግለሰብ እዛ ካሉ ቤተሰቦቻቸው ሂደው መጠየቅ እደሚችሉ፣ ከዚህ ባሻገርም ወደ ፖሊስ ኮሚሽኑን ሂደው መጠየቅ እደሚችሉ አስረድተዋል።
መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia