#ኢትዮጵያ
" በድርቅና በረሃብ እየተጎዳ ካለ ሕዝብ አጀንዳ መሰብሰብና ተሳታፊ መየት አዳጋች ነው " - ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን በትግራይ ክልል ጦርነት ባይኖርም በሌሎች ምክንያቶች የተሳታፊ ልየታ እያደረገ አለመሆኑን አሳውቋል።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ምን አሉ ?
- በአሁን ወቅት በትግራይ ክልል ጦርነት ባይኖርም የተሳታፊ ልየታን እያደረግን አይደለም።
- በተመሳሳይ አማራ ክልል ባለፈው የፀጥታ ችግር የተሳታፊ ልየታ ማድረግ አልተቻለም።
" በአማራ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ተሳታፊዎችን ለመለየት መሰናክል ሆኗል " መባሉ አሳማኝ ቢሆንም በትግራይ ክልል ጦርነት ከቆመ ከአመት በላይ በማስቆጠሩ እንዴት እንደ ምክንያት ሊጠቀስ ይችላል ? በሚል ተጠይቀው ነበር።
አቶ ጥበቡ ታደሰ ፥ " ኮሚሽኑ ስራውን እንዳይሰራ የሚያስቸግረው የፀጥታ ችግሩ ብቻ አይደለም። ይልቁንም #በድርቅና በረሃብ እየተጎዳ ካለ ሕዝብ አጀንዳ መሰብሰብና ተሳታፊ መየት አዳጋች ነው። " ሲሉ መልሰዋል።
- በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለኮሚሽኑን ሥራ እንቅፋት እየሆነ ነው። ያላቸውን የሀሳብ ልዩነት በኃይል አመራጭ ተግባራዊ የሚያደርጉ ታጣቂ ወገኖች ኃይልን ለመጠቀም የመረጡት የሀሳብ ልዩነት ስላላቸው መሆኑን ኮሚሽኑ ይረዳል፤ የሀሳብ ልዩነታቸውንም በጠረንጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ኮሚሽኑ ይሰራል።
- ኮሚሽኑ የሀሳብ ልዩነት ያላቸውን አካላት በጠረንጴዛ ዙሪያ እንዲወያዩ የልዩነት መንስኤዎቻቸውን በተመለከተ አጀንዳ በመሰብሰብ ዘላቂ ሰላም የማምጣት እንጂ፣ በተሰጠው አዋጅ ኮሚሽኑ ጊዜያዊ ችግሮችን እየተዘዋወረ የመፍታት ኃላፊነት አልተሰጠውም።
በሌላ በኩል ፦
* በማረሚያ ቤት ያሉ ማህበረሰብ አንቂዎች፣ ምሁራን እንደ አንድ የህብሰተሰብ ክፍል በአገራዊ ምክክሩ አጀንዳ እንዲሰጡ ካልተደረገ ውጤታማ ሆነ አካታች መሆን እንዴት እንደሚቻል፤
* ኮሚሽኑ የተሰጠው ጊዜ 3 ዓመታት እንደሆነ፣ ይሁን እንጂ 1 ዓመት እንደቀረው፣ በመሆኑም በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ ሥራውን አጠናቆ ሰላም ለማምጣት እንዴት እንደሚችል ፤ ጊዜውን የማራዘም ሀሳብ እንዳለና እንደሌለ ... ኮሚሽኑ ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር።
የኮሚሽኑ ምላሽ ፦
° በማረሚያ ቤት የሚገኙ አካላትን ተሳታፊ ለማድረግ ጉዳዩን ትኩረት ይሰጠዋል።
° የጊዜ ገደቡን በተመለከተ ሰራሁ ለማለት ብቻ የይድረስ ሥራ ከመስራት ጊዜ ወስዶ አመርቂ ሥራ ማከናወን ተገቢ ነው።
° ኮሚሽኑ ከ700 በላይ በሚሆኑ ወረዳዎች የተሳታፊ ልየታ ሥራ እያከያከናወነ ነው። በ327 ወረዳዎች የአጀንዳ ሀሳብ የሚሰጡ ተወካዮች ተመርጧል። በከፍተኛ የትምህረት ተቋማት ከሚገኙ ምሁራን፣ ከዲያስፓራዎች ጋር ውይይት ይደረጋል። ይሁን እንጂ በትግራይና አማራ ክልሎች ተሳታፊ የመለየት ሥራ እየተሰራ አይደለም።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቅርቡ በአዳማ አዘጋጅቶት በነበረ አንድ መድረክ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ለሥራው ፈተና እንደሆነበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቶ እንደነበር ይታወሳል።
መረጃውን ታህሳስ 12 በኮሚሽኑ የተሰጠውን መግለጫ ዋቢ በማድረግ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia