" ' አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው ' እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን
በአዲስ አበባ ከተማ " አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው " እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ገልጿል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል ፤ ተሽከርካሪዎች የሚያወጡት በካይ ጋዞች (ጭሶች) አካባቢን እንዳይበክሉ ተቋሙ የልኬት ቁጥጥር ያደርጋል ሲል አሳውቋል።
በዚያ መሰረትም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብሏል።
ለዚህ የቁጥጥር ስራ እንዲያመች ደግሞ ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነ ጠቁሟል።
መመሪያው አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ከመስመር ለማስወጣት ሳይሆን በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በመቆጣጠር ማስተካከያ እንዲያደርጉ የሚያስችል እንደሆነም ነው ባለስልጣን መ/ቤቱ ያስረዳው።
በዚህም ከዓመታዊ #የቦሎ_እድሳት ጋር የተሽከርካሪው የበካይ ጋዝ ምርመራ የማረጋገጫ ስራ አንዱ መሆኑ ተነግሯል።
የበጋይ ጋዝ / ጭስ ምርመራ ተደርጎ ችግር ያለባቸው እንዲያስተካክሉ ይደረጋል እንጂ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚወራው " አሮጌ መኪናዎች " ሊታገዱ ነው የሚለው ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል አስገንዝቧል።
@tikvahethiopia