TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሼህ አላሙዲ‼️

"ሼህ አላሙዲ ወደ #አዲስ_አበባ ይምጡ፤ #ሳዑዲ ይቆዩ #አናውቅም"- ጠበቃቸው
.
.
ላለፈው አንድ ዓመት ከሁለት ወር በሳዑዲ አረቢያ በእስር ላይ የቆዩት ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ከእስር #መፈታታቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ትውልደ ኢትዮጵያዊው ቱጃር ከእስር የተፈቱት ዛሬ ከሰዓት መሆኑን ጠበቃቸው አቶ ተካ አስፋው ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ገልጸዋል።

አቶ ተካ ሼህ አላሙዲንን #በስልክ ባይነጋግሯቸውም ከወንድማቸው ጋር አብረው እንዳሉ #አረጋግጩያለሁ ብለዋል። “ዛሬ ተፈትተዋል። አሁን ከሪያድ ወደ ጅዳ እየሄዱ ነው፤ ወደ ቤታቸው ማለት ነው። አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር ተገናኝተናል። አዲስ አበባ ይምጡ፣ እዚያው ይቆዩ የምናውቀው ነገር የለም። እኛ አሁን #በመፈታታቸው ብቻ ደስታ ላይ ነው ያለነው።”

ሼህ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በከፈተው የጸረ-ሙስና ዘመቻ ከሌሎች ቱጃሮች፣ ልዑላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለስልጣናት ጋር በጥቅምት ወር 2010 ዓ. ም. ነበር በቁጥጥር ስር የዋሉት። ከእርሳቸው ጋር ታስረው የነበሩ ቢሊየነሩ ልዑል አልዋሊድ ቢን ታላልን ጨምሮ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ከሳዑዲ አረቢያ መንግስት ጋር ድርድር ካደረጉ በኋላ እንደተፈቱ ሲገለጽ ቆይቷል። ሼህ አላሙዲ ስለተፈቱበት ሂደት የተጠየቁት ጠበቃቸው “ዝርዝሩን አላወቅንም። እኛ የምናውቀው መፈታታቸውን ብቻ ነው” ሲሉ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ምላሽ ሰጥተዋል።

ሳዑዲ አረቢያ በወጣቱ አልጋወራሽ ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን የሚመራ የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ካቋቋመች በኋላ 11 ልዑላንን ጨምሮ 200 ገደማ ባለስልጣናት እና ነጋዴዎችን አስራ ነበር። ልዑላኑ እና ቱጃሮቹ ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት በሪያድ በሚገኝ ባለአምስት ኮከቡ ቅንጡ ሆቴል እንዲታሰሩ መደረጉ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር ይታወሳል። ተጠርጣሪዎቹ ሆቴሉን እንዲለቅቁ ከተደረጉ በኋላ በታሰሩበት ስፍራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል የሚል ወቀሳ ሲሰማ ቆይቷል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia