#AddisAbaba
የአዲስ አበባ ፖሊስ አንድን ወጣት አግተው 10 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።
አጋችና ታጋች የአንድ ወር ጓደኛሞች እንደነበሩም አሳውቋል።
የእገታ ወንጀል የተፈፀመበት ወጣት ልዑል መብራቱ ይባላል፡፡
ወጣቱ #በማህበራዊ_መገናኛ_አውታር (ማህበራዊ ሚዲያ) አማካኝነት ባንቴ ይድረስን የተባለውን ግለሰብ ይተዋወቃል፡፡
ትውውቃቸው አንድ ወር ከሞላ በኋላ ባንቴ ይድረስ የተባለው ወንጀል ፈፃሚ የወንድሜ ጓደኛ ቤት ላሳይህ በማለት ወጣቱን ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቁሊቲ መንደር 4 አካባቢ ይዞት ከሄደ በኋላ ከግብረ አበሩ ልዑል ጫላ ጋር በመሆን ያግቱታል፡፡
ወንጀል ፈፃሚዎች እጅግ ዘግናኝ ፊልሞችን እና ፎቶግራፎችን ለወላጆቹ በመላክ 10 ሚሊዩን ብር ካልተከፈላቸው ወጣቱን እንደሚገድሉት የማስፈራሪያ መልእክት ይልካሉ፡፡
የእገታ ወንጀል እንደተፈፀመ ሪፖርት የደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ጋር ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን በተፈፀመ በአራተኛው ቀን ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወጣቱን ከእገታው ነፃ እንዳወጣው አሳውቋል።
ሁለቱ ግለሰቦች ወንጀሉን ለመፈፀም በ5ሺ ብር ቤት መከራየታቸውንና የታጋቹ ወጣት ወላጅ አባት ውጭ ሀገር ይኖራሉ በሚል መረጃ ወንጀሉን መፈፀማቸውን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ፖሊስ ፤ በልዩ ልዩ ምክንያት የምንቀርባቸው ግለሰቦች ማንነታቸውን ጊዜ ወስደን ማረጋገጥ አለብን ብሏል።
በተለይ ሙሉ ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራዮችን ማንነትና ለምን እንደተከራዩ ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስቧል። ይህን ሳያደርጉ በሚፈጠር ችግር የህግ ተጠያቂ እንደሚሆኑ አስጠንቅቋል።
መረጃው ከአዲስ አበባ ፖሊስ የተገኘ ነው።
ፎቶ፦ አዲስ አበባ ፖሊስ
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ህይወቱ ያለፈው የዶ/ር እስራኤል ጥላሁን የስራ ባልደረባዎች እና ቤተሰቦቹ ዛሬ ምሽት ለዶ/ር እስራኤል የማስታወሻ ሻማ የማብራትና የፀሎት መርሃ ግብር አድርገዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በስፍራው ላይ ተገኝቶ ስነስርዓቱን ተካፍሏል።
ፍርድ ቤት ጉዳዩን በተመለከተ ከሰኞ ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚታሰብ የ20 ቀናት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የፍርድ ቤት ሂደቱን እየተከታተለ ያሳውቃል።

#IOM
" በቅርብ ከደርሱት #አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው " - የተመድ የስደተኞች ድርጅት
ስደተኞችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ ጀልባ በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ ሕፃናትና ሴቶችን ጨምሮ ከ60 ሰዎች በላይ መሞታቸውን የተመድ የስደተኞች ድርጅት አስታውቋል።
ቅዳሜ የደረሰው አደጋ፣ ወደ #አውሮፓ ለመሻገር በሚሹ ስደተኞች ላይ በሜዲትሬንያን ባሕር ላይ በቅርቡ ከደርሱት አስከፊ አደጋዎች አንዱ ነው ተብሏል።
የተመድ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) እንዳለው፣ 86 ሰዎችን ይዛ ስትጓዝ የነበረው ጀልባ፣ ከፍተኛ ማዕበል ገጥሟት በሊቢያ ምዕራባዊ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው " ዙዋካ " ከተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ስትገለበጥ 61 ሰዎች #ሰምጠዋል።
ድርርቱ ማዕከላዊው የሜዲትሬንያን ባሕር፣ ለፍልሰተኞች አደገኛ የጉዞ መሥመር መሆኑ ቀጥሏል ብሏል።
#ሊቢያ በጦርነት በመታመስ ላይ ያለች አገር ብትሆንም፣ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ #ሁከትን እና #ድህነት በመሸሽ ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች ተመራጭ መተላለፊያ ሆናለች፡፡
የስደተኞች ድርጅቱ እንደሚለው፣ በመጠናቀቅ ላይ ባለው የፈርንጆች 2023 ብቻ ከ2 ሺሕ 500 በላይ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በባሕር ላይ #ሕይወታቸውን_አጥተዋል።
መረጃው የቪኦኤ ነው።

በTecno Pop 8 ሁሉም እጥፍ ነው!
በየጊዜው እያዘመነ በሚያመርታቸው የሞባይል ስልኮች ተውዳጅነት እያፈራ ያለው ቴክኖ ሞባይል በአዲሱ Tecno Pop 8 ስልክ ሊያዘምኖ መጥቷል።
በማጂክ ስኪን 2.0 ለአያያዝ አመቺ እና ማራኪ በሆነ የቀለም አማራጭ የቀረበ ሲሆን ኩልል ያለ የድምጽ ጥራትን ከዱዋል ስፒከር ቴክኖሎጂ ጋር ይዞ ቀርቦሎታል።
8 + 8Gb ኤክስቴንድድ ራም እና 1ቴራ ባይት ኤክስቴንድድ ሚሞሪ ከ6.6 ኢንች ሰፊ ስክሪን ጋር በማጣመር የፈለጉተን ፋይል፣ ፊልም እና ጌም በስልኮ ጭነው መጠቀም ከማስቻሉ በተጨማሪ የረጅም የአገልግሎት ጊዜ የሚሰጠው 5000 mAh የባትሪ አቅም ያለው መሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።
ቴክኖ ሞባይል ኢትዮጵያ
#Pop8 #TecnoMobile #TecnoEthiopia

#መቐለ
" የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ዋነኛ የፀጥታ መደፍረስ መነሻና ለትራፊክ ወንጀል መቆጣጠር አስቸጋሪ ሆኖውብኛል " - የመቐለ ከተማ ትራፊክ ፓሊስ
የመቐለ ከተማ የትራፊክ ፓሊስ መምሪያ ሃላፊ ኢንስፔክተር ሃይለስላሴ ተኽሉ ለ104.4 የመቐለ ኤፍኤም ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች ዋነኛ የፀጥታ የትራፊክ አደጋ መፈጠር መነሻ ሆነዋል ብለዋል።
በአሁኑ ጊዜ ማንኛውም ተሸከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር ሳይኖረው እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድ መመሪያ መውጣቱ ተከትሎ ያለ ሰሌዳ ቁጥር የሚንቀሳቐሱ ተሸከርካሪዎች ቁጥራቸው የቀነሰ ቢሆንም ፤ በክልሉ ያለው የሰሌዳ ቁጥር የመስጠት እጥረት ችግሩ ሙሉ በሙሉ እንዳይቀረፍ እንቅፋት መፍጠሩን ገልፀዋል።
የሰሌዳ ቁጥር እያላቸው ሆን ብለው ሰሌዳቸው ፈትተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች እንዳሉና ፤ ለምንና እንዴት እንደዚህ እንደሚያደርጉ የመከታተልና የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ያሉት ኢንስፔክተሩ የሰሌዳ ቁጥር ሳይኖራቸው ወንጀልና የትራፊክ ጥሰት ሲፈፅሙ ተከታትሎ ለመያዝ አደጋች እንደሆነ አብራርተዋል።
የትራፊክ ደንብ ጥሰት የፈፀመ ተሽከርካሪ በተቆጣጣሪ የትራፊክ ፓሊስ ባለውና በተለመደው አሰራር የህግ ተገዢ የሚያደርግና የሚያስተምር ቅጣት ለመቅጣት አንድ እንጂ ሁለቱ ሰሌዳ ቁጥሮቹ አይፈቱም ያሉት ኢንስፔክተሩ ፤ ያለ ሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱ ተገኝተው ሲጠየቁ ትራፊክ ፈታብኝ ብለው የሚያመሃኙት ልክ እንዳልሆነ በመገንዘብ ህዝቡ በመቆጣጠርና ለሚመለከተው የህግ አካል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉ እንዲወጣ አሳስበዋል።
በከተማዋ ያለ መንጃ ፍቃድና በተጭበረበረ የሃሰት (ፎርጅድ) መንጃ ፍቃድ ማሽከርከር በዚህ ላይ ፍጥነት ተጨምሮበት ከጊዜ ወደ ጊዜ ከባድ የሆነ የትራፊክ አደጋ በመበራከት ላይ እንደሆነ የጠቀሱት ሃላፊው : ይህንን መልክ ለማስያዝ ህብረተሰብ ያሳተፈ ስራ በመሰራት ላይ ነው ማለታቸው የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ሬድዮ ጣቢያውን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

" ' አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው ' እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው " - የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን
በአዲስ አበባ ከተማ " አሮጌ ተሽከርካሪዎች ሊታገዱ ነው " እየተባለ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚሰራጩ መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ገልጿል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል ፤ ተሽከርካሪዎች የሚያወጡት በካይ ጋዞች (ጭሶች) አካባቢን እንዳይበክሉ ተቋሙ የልኬት ቁጥጥር ያደርጋል ሲል አሳውቋል።
በዚያ መሰረትም ማስተካከያ እንዲያደርጉ ይደረጋል ብሏል።
ለዚህ የቁጥጥር ስራ እንዲያመች ደግሞ ከተሽከርካሪዎች የሚወጡ በካይ ጋዞችን መቆጣጠር የሚያስችል መመሪያ እየተዘጋጀ እንደሆነ ጠቁሟል።
መመሪያው አሮጌ ተሽከርካሪዎችን ከመስመር ለማስወጣት ሳይሆን በካይ ጋዝ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎችን በመቆጣጠር ማስተካከያ እንዲያደርጉ የሚያስችል እንደሆነም ነው ባለስልጣን መ/ቤቱ ያስረዳው።
በዚህም ከዓመታዊ #የቦሎ_እድሳት ጋር የተሽከርካሪው የበካይ ጋዝ ምርመራ የማረጋገጫ ስራ አንዱ መሆኑ ተነግሯል።
የበጋይ ጋዝ / ጭስ ምርመራ ተደርጎ ችግር ያለባቸው እንዲያስተካክሉ ይደረጋል እንጂ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚወራው " አሮጌ መኪናዎች " ሊታገዱ ነው የሚለው ፍፁም ሀሰተኛ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ለኤፍ ቢ ሲ በሰጠው ቃል አስገንዝቧል።

" የተባረሩት መምህራን ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ " - ርዕሰ መምህር ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ
" መስተካከል ያለባቸው እጅግ ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ት/ቤቱ ከወላጅ ተወካዮች ጋር ለመስራት የገባውን ቃል ያክብር " - PTSA
የአንድነት ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት የወላጆችን ጥያቄ በማለባበስ ፣ አግባብ ባልሆነ መንገድ 4 መምህራንን እና 1ሌላ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛን አባርሯል በማለት የትምህርት ቤቱ መምህራን እና የተማሪ ወላጆች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።
መምህራን እና የተማሪ ወላጆች ምን አሉ ?
- የተማሪ ወላጆች በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቱ " የመምህራኑን የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ እመልሳለሁ " በማለት ወላጆች ከፍተኛ ነው ያሉትን የ75 በመቶ የተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ጭማሪ ተደርጓል ብለዋል።
- ትምህርት ቤቱ #ለመምህራን ከ60 እስከ 100 % የደሞዝ ጭማሪ አደርጋለሁ በማለት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር ተስማምቶ ወላጆች የ75 በመቶ የክፍያ ጭማሪ ያድርጉ እንጂ ትምህርት ቤቱ ለወላጆች እና ለመምህራን የገባውን ቃል በማጠፍ በአማካይ ከ10 - 15 በመቶ ብቻ ጭማሪ ማደረጉ ቅሬታ ማሳደሩን ገልጸዋል።
- የትምህርት ቤቱ አስተዳደር የተከተለው አሰራር ልክ አይደለም ያሉት ወላጆች " ጥሩ መምህራን እንዳይለቁብን የደሞዝ ጭማሪ ይደረግላቸው፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ባለሙያ ይቀጠርላቸው፣ አስፈላጊ የትምህርት መማሪያ ግብአቶች ይቅረቡ " ተብሎ በተደጋጋሚ ለት/ ቤቱ ጥያቄ ቢቀርብም ትምህርት ቤቱ ምላሽ መንፈጉን ወላጅ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ ወ/ገብርኤል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
ይህንን ተከትሎ የተማሪ ወላጆች ፦
° ልጆቻችንን የመማሪያ መፅሃፍት በሌለበት ፣
° ጥያቄአችን ባልተመለሰበት ፣
° መምህራን አላግባብ እየተባረሩ ባለበት ሁኔታ ልጆቻችንን ወደ ት/ቤት የምንልክበት ምክንያት የለም በማለት ልጆቻቸውን ከታህሳስ 3/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ አድርገው ቆይተዋል።
የአንድነት ትምህርት ቤት የወላጅ የአስተማሪዎችና የተማሪዎች ማህበር (PTSA) ጉዳዩን ወደ ትምህርት ሚኒስቴር የወሰደው ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መሪነት በትምህርት ቤቱ እና በወላጅ የአስተማሪዎችና የተማሪዎች ማህበር ኮሚቴ መሃል ውይይት ተደርጓል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የአንድነት ኢንተርናሽናል ት/ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑትን ዶ/ር ወርቁ ነጋሽን አነጋግሯል።
ዶ/ር ወርቁ ምን አሉ ?
* በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተመራው ውይይት " #ፍሬያማ ነበር " ብለዋል።
* ከስራ የተሰናበቱት 4 መምህራን እና 1 ድጋፍ ሰጪ ሰራተኛ ወደስራ ገበታቸው እንዲመለሱ መወሰኑን ገልፀውልናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፦
> የመምህራን ደሞዝ ፣
> የወላጆች የተማሪና መምህራን መፅሃፍ ችግር ጥያቄ ላይ የተደረሰው ስምምነት ምን እንድነው ? ብሎ ርዕሰ መምህሩን ጠይቋል።
ርዕሰ መምህሩ ዶ/ር ወርቁ ፤ ስብሰባው ላይ አዲስ የወላጅ ተወካይ ተመርጦ በሚቀጥሉት ቀናት የትምህርት ሚኒስትሩ የመደቡት ተወካይ በሚገኙበት ድርድር እንዲደረግባቸው አቅጣጫ ተቀምጧል ብለዋል።
የተባረሩት መምህራን ወደስራቸው ሲመለሱ ፦
° በፋይላቸው ምንም አይነት መጥፎ ሪከርድ ሳይኖር፣
° የነበራቸው ጥቅማ ጥቅም እንደተጠበቀ ሆኖ
° የተፈጠረው ስህተት ታምኖ #ከይቅርታ ደብዳቤ ጋር እንዲመለሱ የሚል ውሳኔ መወሰኑን ሰምቻለሁ ያሉት መ/ርት ብሩክታይት ፍቃዱ ነገር ግን በይፋ ወደ ት/ት ቤቱ መመለሳቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንዳልደረሳቸው ገልፀዋል።
ት/ቤቱ ያለአግባብ ከስራ ያሰናበታቸውን 5 ሰራተኞች ወደስራቸው ለመመለስ በመወሰኑና እንዲሁም ለሌሎች ጥያቄዎች መፍትሔ ለማምጣት እንዲቻል ለመወያየት ዝግጁነቱን በማሳየቱ ልጆችን በቤት ለማቆየት የተላለፈው ውሳኔ አብቅቶ ልጆቹ ወደ ት/ቤት እንዲሄዱ ማድረጋቸውን ያናገርናቸው ወላጆች ሲያስረዱ በዛሬው እለት ትምህርት መጀመሩን ርዕሰ መምህሩ አሳውቀውናል።
የትምህርት ቤቱ የወላጅ የአስተማሪዎችና የተማሪዎች ማህበር (PTSA) በት/ቤቱ ርዕሰ መምህር ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ የተወሰዱ የእርምት እርምጃዎች ይበል የሚያሰኝ መሆኑን ጠቁሞ ሆኖም መስተካከል ያለባቸው ብዙ ጉዳዮች ስላሉ ከወላጅ ተወካዮች ጋር ለመስራት የገቡትን ቃል #እንዲያከብሩ ጠይቋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለM-PESA እንመዝገብ ፣ በM-PESA እንገበያይ፣ እናሸንፍ!!
የM-PESA ሳፋሪኮምን መተግበሪያ በዚህ ሊንክ ያውርዱ https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia
#MPESASafaricom #TerekBeMPESA
#FurtherAheadTogether

#መምህራን✊ #ትግራይ
" ጥያቄያችን የመኖር ጥያቄ ነው ፤ መሰረታዊ የመምህራን ጥያቄ በአግባቡ ይመለስ ፤ እጅግ ተቸግረናል የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዛችን ይከፈለን " ሲሉ የእንዳ ስላሰ ሽረ ከተማና አከባቢዋ መምህራን በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።
መምህራኑ " መሰረታዊ ጥያቄዎቻችን " ያሉዋቸው እንዲመለሱላቸው ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል።
መነሻቸው ሽረ ስታድዮም በማድረግ በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች በመዞር ድምፃቸው ያሰሙ መምህራኑ ፤ ያጋጠማቸው ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ጊዜ አይሰጥም ብለዋል።
" ጥያቄያችን የመኖር እና ያለመኖር ጥያቄ ነው " ያሉት መምህራኑ የ2014 እና የ2015 ዓ.ም የደመወዝና የጋዎን ልብስ ክፍያ #እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል።
በተጨማሪ፦
- የስራ ግብር እንዲቀነስላቸው
- የደመወዝ እድገት እርከን እንዲሻሻልላቸው
- የቤት ኪራይ ክፍያ እንዲፈቀድላቸው የጠየቁት መምህራኑ ለደረሰባቸው ችግር #የሞራል_ካሳ እንዲሰጣቸው ጭምር በመፈክሮቻቸው ድምፃቸው አሰምተዋል።
መምህራኑ በሰልፋቸው ያሳለፉት ከባድ የጦርነት ወቅት ፤ የተከሰተው የኑሮ ወድነትን የዋጋ ንረት ታሳቢ በማድረግ ከደደቢት ማይክሮፋይናንስ የወሰዱት የብድር ወለድ #እንዲሰረዝላቸው ጨምረው ጠይቀዋል።
የእንዳስላሰ ሽረ ከአዲስ አበባ በ1100 ፤ ከመቐለ በ300 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ የትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ዋና ከተማ መሆንዋ የከተማዋ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት በመጥቀስ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።