TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA🇪🇹 #UAE🇦🇪

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) አየር ኃይል አባላት በጋራ ሆነው " ጥቁር አንበሳ " የተሰኘ የአየር ላይ ወታደራዊ ትርዒት አቀረቡ።

ትርዒቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ አየር ኃይል 88ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደ ስነስርዓት ላይ ነው።

በስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ " በኢትዮጵያና በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አየር ኃይሎች በጋራ የቀረበው ወታደራዊ የአየር ላይ ትርዒት በትብብር ከሠራን የምንደርስበትን ደረጃ ያሳየ ነው " ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የአየር ትርዒቱ ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢማራት በፖለቲካው እና በውትድርናው መስክ ያላቸውን መልካም ግንኙነት፣ ወዳጅነትና ትብብር ያሳየ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከተመሰረተ 88ኛ አመቱን የያዘ ሲሆን ካለፈው ህዳር 20 ጀምሮ የምስረታ በዓሉ እየተከበረ ነው።

Photo Credit - #PMOfficeEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አማራ

" ጥናቱ ባካለላቸው ወረዳዎች 36 ሰዎች በድርቅ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል " - ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ ደረጀ

የደባርቅ ዩኒቨርስቲ 8 አባላት ባሉት የጥናት ቡድን በመመደብ በሰሜን ጎንደር ዞን የተከሰተውን ድርቅ መጠንና ስፋት ያጠና ሲሆን ውጤቱንም ይፋ ማድረጉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

ይህንን በተመለከተ የጥናት ብድኑ ስብሳቢ ረዳት ፕሮፌሰር አምሳሉ ደረጀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጻ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

- ጥናቱ ከመስከረም 28 እስከ ህዳር 20 2016 ዓ.ም የተካሄደ ነው። ጥናቱ ድርቅ በጃናሞራ፣ በበየዳና በጠለምት ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎችን ላይ የተካሄደ ነው።

- ጥናቱ ድርቁ በእነዚህ አከባቢዎች (በሦስቱ ወረዳዎች) በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል። 73 ሺህ 387 የቤት እንስሳትም በዚሁ ምክንያት #መሞታቸውን አረጋግጧል።

- በበየዳና ጃናሞራ ወረዳ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው የሚኖሩ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ለማቋረጥ ተገደዋል። 16ሺ 650 ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል ተቸግረዋል። 292 ተማሪዎች አካባቢውን ለቀው ጠፍተዋል።

- ጥንቱ ባካለላቸው ወረዳዎች 36 ሰዎች በድርቅ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። የድርቁ ተጎጅዎች ድርቅን እንዲቋቋሙት ለማስቻል አስቸኳይ የምግብ የውኃ አቅርቦት ማቅረብ ይገባል።

ጥናቱ እንደመፍትሄ ምን አቀረበ ?

* የትክልትና ፍራፍሬ ዘር ማቅረብ፤
* የእንሰሳት መኖ ማቅረብ፤
* የእንሰሳት ክትባት  ማካሄድ፤
* የመድሂኒት ግዥና አቅርቦት፤
* የትምህርት ቤት ምግብ ፕሮግራም መጀመር፤
* የቤት ለቤት ልየታና ህክምና ማካሄድ
* የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን በአንድ አካባቢ እንዲማሩ መርዳት ይገኙበታል።

የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል  ፦

° በዞኑ በ6 ወረዳዎች በሚገኙ 83 ቀበሌዎች በተከሰተ የድርቅ አደጋ ከ 452 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ለድርቅ አደጋ ተጋልጠዋል።

° በሰብል የተሸፈነ 34 ሺህ ሄክታር መሬት በድርቅ ተጎድቷል።

° ለህብረተሰቡና ለእንሰሳት አግልግሎት የሚሰጡ የውኃ ተቋማት ደርቀዋል።

° ድርቁ በ100 የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ላሉ 54 ሺ 406 ተማሪዎች እንቅፋት ሆኗል።

° የፌደራል መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 239 ሺህ 400 የድርቁ ተጎጅዎች የምግብ እህል ለማዳረስ እየሰራ ነው። እስካሁን ለ177ሺ 100 ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እህል ማድረስ ተችሏል።

° በክልል መንግስት 5 ሺህ 100 ኩንታል፤ በሌሎች ረጅ ድርጅቶች ደግሞ 7 ሺህ 73 ኩንታል እህል ድጋፍ ተደርጎል።

° ከተረጅው ብዛት አኳያና የድርቁ ተጎጅዎች መጠን እያደገ በመምጣቱ አሁንም ሰፊ ድጋፍ ያስፈልጋል።

° በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ ርብርብ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል። አሁንም መቀጠል ይገባል።

መረጃውን አዘጋጅቶ የላከው የጎንደር የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተስብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቲክቶክ ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ? ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል። ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት…
#USA #TikTok

" ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " - ግሌን ያንግኪን

በአሜሪካ የቨርጂኒያ ግዛት ገዥ ግሌን ያንግኪን ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች " ቲክቶክ "ን እንዳይጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳወቁ።

ያንግኪን ፤ " ቲክቶክ " የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ለህጻናት ልጆቻችን አእምሮአዊ ጤንነት እጅግ ጎጂ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሪፐብሊካኑ ሰው ወደዚህ እርምጃ እንደሚመጡ ያሳወቁት ባለፈው አመት ቲክቶክን ከማንኛውም የመንግስት ኤሌክትሪክ መሳሪያዎች እና ዋይፋይ #ካገዱ በኋላ ነው።

ያንግኪን ፤ በአጠቃላይ ማህበራዊ ሚዲያ በልጆቻችን ላይ ከባድ እና ቀጣይነት ያለው አሉታዊ ተጽእኖዎች እያሳደረ ነው ብለዋል።

ከነዚህም ውስጥ ፦
- የማህበራዊ ክህሎታቸው እንዲያጡ ፣
- በሳይበር አማካኝነት የማዋረድ፣ ስድብና ሌላም ጎጂ ድርጊት እንዲደርስ፤
- የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እንዲስፋፋ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ አመላክተዋል።

በመሆኑም " ወጣቶችን ቲክቶክ እንዳጠቀሙ የሚገድብ ረቂቅ ህግ እንደሚወጣ አሳውቃለሁ ... አለቀ !! " ሲሉ ገልጸዋል።

" ቲክቶክ " ን ልጆች እንዳይጠቀሙ ከሚያግደው ረቂቅ በተጨማሪ ልጆች ከማህበራዊ ሚዲያ ግብይት እና መረጃዎቻቸውን ከመጠቀም እና ከመሸጥ የሚከላከሉ ህጎች እንደሚያወጡ ገልጸዋል።

የቨርጂንያው ገዥ " ሱስ አስያዥ " ብለው ከጠሯቸው የማህበራዊ ሚዲያ የማርኬቲንግ ስልቶች ልጆችን እና ታዳጊዎችን ለመጠበቅ የሚረዱ ረቂቆችን ይፋ እንደሚያደርጉ የተናገሩ ቢሆንም " መቼ ? " የሚለውን አልገለፁም።

በአሜሪካ እንደ አጠቃላይ እስካሁን " ቲክቶክ " ባይታግደም፤ እንቅስቃሴዎች ስለመኖራቸው ግን ተደጋጋሞ ተነግሯል።

በተለይም በርካታ የሪፐብሊካን ዕጩዎች በቀጣይ ምርጫ አሸንፈው ፕሬዜዳንት መሆን ከቻሉ በአጭር ጊዜ መተግበሪያውን ለማገድ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በተለያዩ ግዛቶች ደግሞ ከደህንነት እንዲሁም ወጣቶችን ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ " ቲክቶክ " ከመንግሥት የኤሌክትሪክስ መሳሪያዎች ፣ ከዩኒቨርሲቲዎች፣ ኮሌጅ ካምፓሶች ዋይፋይ እንዲታገድ ተደርጓል።

" ቲክቶክ " ባለቤት የሆነው የቻይናው ባይትዳንስ ኩባንያ በተለያየ ጊዜ የሚነሳበትን ወቀሳ ውድቅ ሲያደርግ መቆየቱ እየሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እኔ እድሜዬን በሙሉ እንዲህ አይነት ድርቅ አይቼ አላውቅም " በትግራይ ክልል፤ የኢሮብና አፅቢ ወረዳ ነዋሪዎች አስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ቃላቸውን ለድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን የሰጡ ነዋሪዎች ምን አሉ ? አንድ አባት ፦ " ክረምት አልነበረም ማለት ይቻላል። በጣም ጥቂት ዝናብ ነው የዘነበው። እንኳን እህል የእንስሳት መኖ አልሰበሰብንም። አካባቢያችን ለከፍተኛ ችግር ተጋልጧል። በድርቁ…
#ትግራይ

በትግራይ ያለው ድርቅ . . .

" ከ1977 የባሰ ጊዜ መጣብን፤ ...መሬት እህል አላበቅል አለ  "

እናት #1፦ " ችግር በዛብኝ ፤ እራሴም እየዞረብኝ ነው። እግሬንም ማንቀሳቀስ አቅቶኛል። ልቤም እየደከመብኝ ነው። በረሃብ በችግር ምክንያት ነው እንዲህ የሆንኩት። "

እናት #2 ፦ " የዘራነው እህል ዝናብ ባለመኖሩ አሯል። በዚህ ምክንያት ተርበናል። እህቴም ሁለት ልጆቿን የምታበላቸው አጥታ ቆሎ ስታገኝ የእናት ነገር ሆኖባት ለራሷ ሳትበላ ለእነሱ እያካፈለች በረሃብ በቤቷ ደርቃ ነው የተገኘችው። እኔም አሁን የምበላው የለኝም ረሃብ ሲበረታብኝ ወደ ጎረቤት ሄጄ ቡናም ካገኘው እሱን ጠጥቼ ውላለሁ። "

እናት #3 ፦  " የ2 ዓመት ከ4 ወር መንታ ልጆችን ይዤ በረሃብ ተሰቃይቼ ነው ያለሁት። ለራሴ ተሰቃይቼ ልጆቹንም አሰቃየዋቸው። የምበላው አጥቼ ፆሜን ነው ተደፍቼ የማድረው። ለምኜ እንዳልበላ ልመናው የለም። ልጆቼ ጡቴን ሲጠቡኝ ልቤን ያንሰለስለኝና ያመኛል። ለሊቱን ሙሉ ሳቃስት ነው የማድረው። "

እናት #4 ፦ " ልጄ 8 አመቱ ነው ዘንድሮ ሁለተኛ ክፍል ጨርሶ ወደ 3ኛ ክፍል ያልፍ ነበር አሁን ግን ባጋጠመን ድርቅ ተቸግረን ትምህርቱን መማር አልቻለም። በጣም ተርበናል። ልጆቻንን ካገኙ ይበላሉ ካልሆነም ውሃ ጠጥተው ይውላሉ። በረሃብ ተሰቃየን። "

ድርቅ ባመጣው ረሃብ  ምክንያት ተማሪዎችም ከትምህርት ገበታቸው ቀርተዋል።

ተማሪዎች ደብተርና እስክሪብቶ የሚገዛላቸው ስላጡ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ አቁመዋል።

ወላጆች አይደለም ለእነሱ የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላትና ሊያስተምሯቸው ለሆዳቸውም መሆን አቅቷቸዋል። ከባድ ችግር ላይ ናቸው።

በድርቅ የተጠቁ ወገኖች ለረሃብ ማስታገሻ ከመሬት ስር እና ከእፀዋት ፍራፍሬ በመልቀም ህይወታቸውን ለማቆየት ሲጥሩም ተስተውሏል።

እናት ፦ " ልጆችን የማበላቸው አጥቼ ጨንቆኝ ለለቀማ ኑ እንሂድ ብያቸው በረሃብ ምክንያት ከትምህርት ቀርተዋል። ትንፋሻችንን ለማቆየት ኩዕንቲ እየለቀም ነው የምንበላው። መሬት እህል አላበቅል አለ፤ እንኳን እህል ኩዕንቲ አላበቅል አለ። ከ1977 የባሰ ጊዜ መጣብን፤ በረሃብ ምክንያት ልጆቼ ቤት ውስጥ ታጥፈው እየዋሉ ነው። "

እናት ፦ " ይህ መሬት ጤፍ ያበቅል ነበር አሁን ግን ጊዜ ከዳን "

እናት ፦ " ጠኔና ረሃብ ካጋጠመን በኃላ ከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያለነው። ኩዕንቲ እንኳን የሚለቅመው አይኑ በደንብ የሚያይ ነው። ይህን ለመብላትም ጥርስ ያስፈልጋል። "

ድርቁ ሰው ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ እንስሳት የሚበሉትን አጥተው እየሞቱ ነው።

በትግራይ ውስጥ የነበረው ደም አፋሳሽ አስከፊ ጦርነት ፣ በክረምቱ ዝናብ አለመኖር፣ ወቅቱን ያልጠበቀው ዝናብ፣ እንዲሁም የአንበጣ መንጋ ተዳምሮ ህዝቡን የከፋ ችግር ላይ ጥሎታል።

እንደ ክልሉ አስተዳደር መረጃ ከሆነ 2 ሚሊዮን ሰው ለረሃብ ተጋልጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነዋሪዎችን ቃል ያዳመጠው ከክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
የዘመኑን የክፍያ መንገድ ይቀላቀሉ!
********
ካርድዎን ወደ ስልክ ጠጋ
Tap to Phone (TTP)
********
ንክኪ አልባ ካርድዎን ወደ ክፍያ ተቀባዩ ስልክ ጠጋ በማድረግ ብቻ ክፍያ መፈፀም የሚያስችል!

አሁን በፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ባሶች ላይ አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡
#ፈጣን #ቀላል #አስተማማኝ
#CBE #VISA #TTP
#ሲዳማ_ክልል 

" 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል " - የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ

በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በቦታ ጥበትና ሌሎች መሰል ችግሮች ሥራ ለማቆም እየተገደዱ  መሆናቸውን ተደራጆቹ በተደጋጋሚ  ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣሉ። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሚነሱ ቅሬታዎች የሲዳማ ክልል ሥራ፣ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ቢሮ ምክችል ኃልፊ  እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደን ጠይቋል።

አቶ ከፍያለው ፤ " 26,000 ኢንተርፕራይዞች የከሰሙ መሆናቸውን አረጋጥጠናል። " ብለዋል።

" ከዛ ውጭ ያሉት 48 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ናቸው። ሌሎች ወደ 52 በመቶ አካባቢ የሚሆኑት የተሻለ ደረጃ ላይ ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢንተርፕራይዞቹ የከሰሙበት ችግር ምን እንደሆነ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ፦
- ድርቅ፣
- የፀጥታ ችግር
- ወደ ከተማ ያሉት ደግሞ በገበያ ማጣት፣
- በማኅበር እስከ 30 ድረስ የሚደራጁት እርስ በእርሳቸው ባለመስማማት
- ሌሎችም በግል ምክንያት
- በቂ ስልጠና እና አግኝተው ካለመግባታ ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በመሬት ጥበት ሥራ ለማቋረጥ እንደሚገደዱ ይገልፃሉ።

ሲዳማ ክልልም አዲስ ክልል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ብዙ ቅሬታዎች ሲነሱ ይደመጣልና በመሬት ጥበት ምክንያት ያለው ችግር ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቢሮው ጥያቄ አቅቧል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-12-17

@tikvahethiopia