TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደመወዝ

" ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም የደመወዝ ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ለመንግስት ጥያቄ ቀርቧል " - ኢሠማኮ

የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት ይፋ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ይደረጋል በተባለው ልክ፣ ለግል ድርጅቶች ሠራተኞችም ማስተካከያ የሚደረግበት አቅጣጫ እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርቧል።

የኢሠማኮ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው አህመድ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፤  " በመንግሥት በጀት ለሚተዳደሩት የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ የግል ድርጅቶችና ተቋማት በራሳቸው በጀትና ትርፍ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑናቸው፣ በትርፋቸው ላይ ተመሥርተው ለሠራተኛ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ከመንግሥት አቅጣጫ እየተጠበቀ ነው " ብለዋል።

" የሠራተኞችና የደመወዝ ዝቅተኛው ወለል እንዲወጣ እየወተወትን ነው " ሲሉም ተናግረዋል።

የመንግሥት እና የግል ሠራተኞች አንዱ የተሻለ አንዱ የወደቀ የሚባል ክፍያ ሊኖር አይገባም ሲሉ አክለዋል።

" መንግሥት ይህን ጉዳይ ሊዘነጋው አይችልም የሚል እምነት ቢኖረንም፣ መሰል አገራዊ አጋጣሚዎችና ቀውሶች በሚኖሩበት ጊዜ ባለሀብቶችንና ተቋማትን የሚመለከቱ ማሻሻያዎች በማድረግና ውይይቶች በማካሄድ አቅጣጫዎች ሊሰጡበት ይገባል " ሲሉ ተናግረዋል።

" ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለአገርም አይጠቅምም፣ የኢንዱስትሪ ሰላም አይኖርም፣ ሠራተኛውም ተረጋግቶ ሥራውን ማከናወን አይችልም " ብለዋል።

አቶ አያሌው፣ " ጉዳዩ እጅግ በጣም አሳሳቢ ስለሆነ መንግሥት አቅጣጫ የማይሰጥበት ከሆነ ኢሠማኮ ጥያቄውን በጽሑፍ ለመንግሥት ያቀርባል " በማለት አስረድተዋል፡፡

" ሠራተኛው በከፍተኛ የኑሮ ውድነት ምክንያት በልቶ ማደር አልቻለም፣ የኑሮ ውድነቱን መቋቋም አልቻለም፣ ይህን ማንም ያውቀዋል ሚስጥር አይደለም፣ አሠሪዎቹ ለሚያሠሯቸው ዜጎች ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ መክፈል አለባቸው " ብለዋል፡፡

የሠራተኛ መብት መከበር እንዳለበት " የሚያረጋግጥ ወጥ የሆነ ሕግ ያስፈልጋል " ያሉት አቶ አያሌው፣ " የሠራተኞች ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልና ሌሎች የሠራተኞች መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን መንግሥት ለምን እንዳዘገያቸው አልገባኝም " ሲሉ ገልጸዋል።

" የዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ጉዳይ ላይ አሁንም መንግሥት የዘነጋው ይመስላል " ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ኢሠማኮ ተጨማሪ ጥያቄ ሊያቀርብ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

አክለው ፥ ከመንግሥት ተቋማት በተሻለ የሚያተርፉት የግል ተቋማት፣ ከመንግሥት የደመወዝ ጭማሪ ጋር እኩል ላለመጨመር ትልቁ ችግር የአስተሳሰብ ጉዳይ እንጂ፣ የገንዘብ እጥረት አይደለም በማለት ለዜጎች ማዘን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ለራስ ብቻ ከማግበስበስ ዕሳቤ በመውጣት ምርታማ ሠራተኛን ለማፍራት፣ አሁን  ተመጣጣኝ የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ ብዙ ነው የሚያሰኝ አለመሆኑን ገልጸዋል።

#EthiopianReporter #Salary #Ethiopia

@tikvahethiopia
" አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል " - ገንዘብ ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ከአሁን በኃባ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እንዲያስገቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ገንዘብ ሚኒስቴር ፥ የዲፕሎማሲና የቆንስላ አገልግሎት የሚሰጡ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት፣ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቧቸው ተሽከርካራች የኤሌክትሪክ ብቻ መሆን እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገል በምታደርገው ቁርጠኝነት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ማስገባት የተከለከለ እንደሆነ ነው ሚኒስቴሩ ያሳውቀው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ምን አሉ ?

" ይህንን ውሳኔ በርካታ የአውሮፓ አገሮች የሚደግፉት ሐሳብ ነው።

አገሮች የአስተናጋጅ አገርን ሕግ አክብረው እንዲንቀሳቀሱ ይጠበቃል።

ውሳኔው የዲፕሎማሲ ሥራን ለመሥራት የሚያውክና የአገሮችን ሉዓላዊነትን የሚጥስ ባለመሆኑ፣ እንደ እነዚህ ዓይነት ሕጎች ሲወጡ ዲፕሎማቶች ያንን ሕግ አክብረው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ "

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ 38 የገቢ ንግድ ምርቶች ዕግድ እንዲነሳላቸው ባሳለፈው ውሳኔ ቢያሳውቅም የገንዘብ ሚኒስቴር ግን በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ላይ ዕግዱ እንደማይነሳ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ #EthiopianReporter

@tikvahethiopia