TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ስራ #ደመወዝ

° " ያለስራና ደመወዝ በመቆየታችን ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀናል " - የመንግስት ሰራተኞች

° " ጉዳዩን እናውቀዋለን እየተወያየንበት ነው ፥ በአጭር ቀናት መፍትሄ ይሰጣቸዋል " - የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለስልጣን

የደቡብ ክልል መበተኑን ተከትሎ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተመደቡ የ " ውሀ ስራዎች ኮንስትራክሽን ሰራተኞች " ከስራ እና ከደመወዝ ውጭ ሆነው ወራት እንደተቆጠሩ ገልጸዋል።

ሰራተኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ባቀረቡት ቅሬታ ፥ ክልሉ ከፈረሰ በኋላ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቢመደቡም እስካሁን ስራ አለመጀመራቸውን በዚህም ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል።

ከ2 ወር በፊት ዘግይቶ በተሰጣቸው ደብዳቤ ሆሳዕና ከተማ መመደባቸው እንደተነገራቸው ጠቁመዋል።

ቦታው ላይ ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም እንደሚሰጣቸውም ተገልጾላቸው ነበር።

በዚህም ግማሽ ሰራተኞች እቃቸውን በገንዘብ እጥረት ሽጠው እንዲሁም ቀሪውን በሌለ ገንዘብ ትራንስፖርት ከፍለው ቦታው ቢደርሱም አንድም የሚያስተናግዳቸው ሆነ የሚቀበላቸዉ አካል ማጣታቸውን አስረድተዋል።

በመሆኑም ያለደሞዝና ስራ በተመደቡበት ከተማ ለ2 ወራት መቆየታቸው ህይወትን ከባድ እንዳደረገባቸዉ ገልጸዋል።

በገንዘብ እጦት የምግብ መግዣ እንኳ እንስከማጣት መድረሳቸውን ከዚህም በላይ በቤት ኪራይ ችግር አብዛኛዉ ሰራተኛ ጎዳና ለመውጣት ጫፍ መድረሱን ተናግረዋል።

" ሆሳዕና የሚገኘው አዲሱ ቢሮ ስንሄድ #ጸሀፊ_ብቻ ነው የምናገኘው " የሚሉት ሰራተኞቹ " የሚመለከተው አካል ሌላዉ ቢቀር ጥያቄያችን ሊያደምጥ ይገባል " ሲሉ ቅሬታቸው ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞቹን ጥያቄ ይዞ ያናገራቸዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አማካሪ እና ልዩ ረዳት የሆኑትን አቶ ንጉሴ አስረስ ፥ ጉዳዩን እንደሚያውቁት በመግለጽ ችግሩ በቅርብ እንደሚፈታ ተናግረዋል።

ከሰሞኑ ሰራተኞችን በአካል አግኝተዋቸው ለማነጋገር እቅድ እንዳላቸውም የገለጹት አቶ ዘሪሁን " ለሁለት መቶ አስር ሰራተኞች ደሞዝ መክፈል ለክልሉ ቀላል ነው " ብለዋል።

በቅርቡ ችግሩ ላይ የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም ሌሎችም ተጨማሪ ጥያቄዎች ካሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሊያነጋግራቸው እንደሚችል ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa
#CentralEthiopiaRegion

@tikvahethiopia