#makeway
በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ የጤና ወጪ ውስጥ
ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የሚመደበው ገንዘብ ከጤና አገልግሎት ፍላጎት አንፃር እጅግ አነስተኛ መሆኑንና ከአጠቃላይ የጤና ወጪ ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የሚመደበው 12 በመቶ ብቻ መሆኑን የስነ ተዋልዶ ጤና ማኅበራት ጥምረት (CORHA) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የጥምረቱ የጤና እንክብካቤ ፋይናንሲንግ ቴክኒክ አማካሪ የሆኑት አቶ ሚደቅሳ አዱኛ ጤና ሚኒስቴር በየሁለት ዓመቱ የጤና ወጪ ጥናት እንደሚያወጣ አንስተዋል።
በፈረንጆቹ 2016 እስከ 2019 ያለውን ጊዜ በማካተት በተጠናው ጥናት መሰረትም ከሀገሪቱ አጠቃላይ የጤና ወጪ 12 በመቶ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው፤ ዘርፉ ካለበት ችግር አንፃር እጅግ አናሳ መሆኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የሥነ-ተዋልዶ ጤና ወጪ ከምስራቅ አፍሪካ አቻዎቿ ጋር፤ በተለይም ከብሩንዲና ኬንያ ጋር ሲነጻጸር አናሳ መሆኑን አቶ አዱኛ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቃለ-ምልልስ አንስተው፥ ሀገሪቱ በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ የምታፈሰው ኢንቨስትመንት የዘርፉን ችግር ያገናዘበ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ቪኤስኦ ኢትዮጵያ፣ ሪድም ዘጀነሬሽን እና የወጣት ሴቶች ክርስቲያን ማኅበር በጋራ " ሜክ ዌይ " የተባለ ፕሮግራም በመፍጠር በጋራ እየሰሩ ሲሆን በዓለም ለ32ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የሚታሰበውን ፀረ- ጾታዊ ጥቃት ቀንን አስመልክቶም በሥነ-ተዋልዶ ጤና ላይ የሚመክር መድረክ ከሰመኑ አሰናድተው ነበር።
በመድረኩ ላይ፤ በሀገሪቱ የሥነ-ተዋልዶ ጤናን ለመጠበቅ ከሚመድበው ገንዘብ ውስጥ #50_በመቶ የሚሆነው ሀብት ለአስተዳዳር ወጪ የሚወጣ እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን ይህም የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ተደራሽነት የሚገድብ እንደሆነ ተነስቷል።
የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት፥ 23.9 በመቶው የሚሆነው ወጪ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሸፈን ሲሆን 62.7 በመቶው ደግሞ መንግስት ይሸፍናል። ተጠቃሚዎች ደግሞ 12.3 በመቶ የሚሆነውን ያክል ድርሻ እንደሚያወጡና ቀሪው በሌሎች እንደሚሸፈን በጥናቱ ተመላክቷል።
መንግስት የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ዜጎች በነፃ እንዲያገኙ ቢያስቀምጥም ተጠቃሚዎች ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት 12.3 በመቶ የሚሆነውን ያክል ድርሻ እያወጡ በመሆኑ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት በሚፈልጉ ግለሰቦች ላይ ጫና አሳድሯል ተብሏል።
በምክክሩ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ሥራ መሰራት እንደሚኖርበት ሲገለፅ፥ የጾታዊ ለጥቃት ተጋላጮች ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም የፆታዊ ጥቃትን መከላከል የሚያስችል የተቀናጀ የሚዲያ ዘመቻ ማካሄድ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል።
'' መቼም የትም በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል '' በሚል መሪ ቃል የ16 ቀናት የፀረ-ጾታዊ ጥቃት ዘመቻ እየተደረገ መሆኑና በሚቀጥሉት ቀናትም ዘመቻው እንደሚቀጥል ተገልጿል።
@tikvahethiopia