TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዛሬ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በመግለጫው ምን አለ ?

አገልግሎቱ ለተገልጋዮች አዲስ አሰራርን ወደ ስራ ማስገባቱን አሳውቋል።

በበይነ መረብ አማካኝነት ፦
- የትምህርት መረጃ ማጣራት፣
- የትምህርት ማስረጃ ለሌላ ተቋማት መላክ ፣
- ድጋሚ የትምህርት ማስረጃ መውሰድ፣
- የትምህርት ማስረጃን ማረጋገጥ
- በምዝገባ ወቅት የሚያጋጥምን የስም ፊደላትን ጉድለት ማስተካከል ይቻላል ብሏል።

አገልግሎቱን ለማግኘት ተገልጋዮች በቴሌ ብር እና ንግድ ባንክ በኩል ክፍያ መፈፀም እንደሚኖርባቸው አመልክቷል።

ከዚህ በኋላ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ቅርንጫፎች እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ180 ሀገራት፣ በአካል እንዲሁም በውክልና ማግኘት እንደሚቻልም ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ #ከቀጣይ_ወር ጀምሮ ለ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ምዝገባ እንደሚጀመርም ይፋ ተደርጓል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia